ከ2 ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን በላይ የሆነ ምርት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታገደ

0
858

ባለፉት 9 ወራት የተቀመጠላቸውን የጥራት ደረጃ ያላሟሉ እና ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ  ምርቶች ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  ባካሄደው የጥራት ቁጥጥር ከጥራት ደረጃ በታች ሆነው ባገኛቸው  ከ2 ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸው ታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን  ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤  በቁጥጥሩ ከታገዱት የገቢ ምርቶች ውስጥ 2 ሺህ 304 ነጥብ 95 ሜትሪክ ቶን ጥቅል ብረት፣ 28 ነጥብ 7 ሜትሪክ ቶን የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ 180 ካርቶን ሳሙና፣ 142 ካርቶን በፀሐይ ብርሃን የሚሠራ የእጅ ባትሪ፣ 150 ካርቶን የኤሌክትሪክ ገመድ እና 43 ነጥብ 22 ሜቴሪክ ቶን የቆርቆሮ መስሪያ ጥሬ ዕቃ ይገኙበታል።

በተጨማሪም 272 ጥቅል የአርማታ ብረት፣ 19 ሺህ 770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት፣ 2 ሺህ 934 ፍሬ የውኃ ፓምፕ፣ 875 ካርቶን ባትሪ ድንጋይ፣ የታሸጉ ምግቦችና ሌሎችም የገቢ ምርቶች በቁጥጥሩ ወቅት ከጥራት መስፈርት በታቸ ሆነው በመገኘታቸው ወደ አገር ውስጥ ገበያ እንዳይገቡ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ምርቶቹ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ በመደረጉም ቢገቡ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የጤና፣ የደኅንነትና የጥቅም ጉዳት ማስቀረት መቻሉንም ተመላክቷል።

በተመሳሳይ በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ መሰረታዊ ሸቀጦች ለማህበረሰቡ በትክክል እንዲደርሱ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትር ሚኒስቴር አስውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ መንግስት ድጎማ በማድረግ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረባቸው ያሉ የዳቦ ስንዴ፣ ስኳር እና የምግብ ዘይት ለሚገባቸው አካላት ሙሉ በሙሉ እንዲደርሱ ለማድረግ በትኩረትእየሰራ እንደሚገኝም ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል።

በ2012 በጀት ዓመት 9 ወራት 5,198,202 ኩንታል ስንዴ ለማከፋፈል ታቅዶ 4,296,701 ኩንታል፣ 3,376,446 ኩንታል ስኳር ለማከፋፈል ታቅዶ 2,837,967 ኩንታል እንዲሁም 147,922,370 /የእቅዱን 41%/ ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ መሰራጨቱን ኢዜአ ከሚኒስቴሩ መስሪያ ቤቱ አገኘሁት በማለት በዘገበው መረጃ ላይ ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here