የድንበር ተሻገሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በቃሊቲ ጉሙሩክ ጣቢያ ተጀመረ

0
645

የድንበር አቋራጭ ከባድ የመኪና አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ለወረርሽኙ ካላቸው ተጋላጭነት አንጻር በወደቡ ገቢ ጭነት ሲያራግፉም ሆነ ወጪ ጭነት ሲጭኑ በሚኖረው ሂደት የዘመቻ ስራው በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሚገኝ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ፡፡

ከአሁን በፊትም በወደቡ የሰው ንክኪ በሚበዛባቸው አካባቢዎችና ገቢ ጭነት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ርጭት የማካሄድ፣ ማንኛውም አሽከርካሪና እና ረዳት ወደ ወደቡ ሲገባ እና ጭኖ ሲወጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የሙቀት ልኬት ማድረግ፡ አስገዳጅ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረትም ዛሬ ግንቦት 07ቀን 2012 ዓ/ም ከኢትዬጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በአሽከርካሪዎችና ረዳቶች ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተጀመረ መሆኑን ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here