10ቱ በአፍሪካ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚያንቀሳቅሱ የንግድ ከተሞች

Views: 266

አፍሪካን ዌልዝ ሪፖርት 2018 (እ.ኤ.አ)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግልፅ እየታየ የመጣው የአፍሪካ ከተሞች ፈጣን ፍጥነት እንደ ምክንያትነት ከሚተቀሱት ምክንያቶች መካከል ከውስን የኢኮኖሚ አማራጮች ይልቅ የተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እየተዋወቁ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ወደ አፍሪካ የሚደረጉ ፍልሰቶች የተሻለ የኢኮኖሚ አማራጮች እና አመቺ የኑሮ ሁኔታን ፍለጋ እንደሚጨምርም ምልከታዎች አሉ፡፡

አፍሪካን ዌልዝ ሪፖርት እ.ኤ.አ በ 2050 አፍሪካ አሁን ባላት የህዝብ ብዛት ላይ የ1.3 ቢሊዮን ጭማሪ ታሳለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህም 50 በመቶ የሚሆነው በከተሞች ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ሪፖርቱ አክሎም ባሳለፍነው አስር አመታት 19 ሺህ አዳዲስ ሚሊዮነሮች በአፍሪካ የተፈጠሩ ሲሆን የአሃጉሪቱ የሃብት መጠንም 2.3 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ እ.ኤአ በ2027 ይህ የአፍሪካ የሃብት መተን 3.1 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ደቡብ አፍሪካም አራቱን የአፍሪካን ሀብታም ከተሞች በመያዝ መሪነቱን የያዘች ሲሆን የንግድ ዋና ከተማዋ ጆሃንስ በርግ ቁንጮነቷን አረጋግጣለች፡፡ ምንም እንኳን በከፍተኛ እድገት ውስጥ የሚገኙት የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች በሪፖርቱ ባይጠቃለሉም አዲስ አበባን ጨምሮ ካምፓላ እና ዳሬሰላም በተለይም በለፉት አስር አመታታት ከፍተኛ እድገት አሳይተዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com