በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ተያይዞ ኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ የደረሰው ውድመት የመንግስት ይፋ አደረገ

0
782

ከድምታ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ኹከት እና ግርግር መድረሱን ተከትሎ የወደሙ ንብረቶችን በሚመለት መንግስት የውድመቱን መጠን ይፋ አድርጓል ።
በዚህም መሰረት እንደ መንግስት ሪፖርት ከሆኑ በክልሉ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት
1022 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ወይም ተሰባብረዋል፣ 227 ሆቴሎች ተቃጥለዋል፣ተሰባብረዋል፤ 6 ፋብሪካዎች ተቃጥለዋል፤104 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወድመዋል፤ 20 የመንግስት እና 273 የግል መኪናዎች ተቃጥለዋል ፣ ተሰባብረዋል፤ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቦታቸው ተፈናቅለዋል ሲል አስታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በጉዳቱ ዕጃቸው አለበት የተባሉ 7126 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው 500 ክሶች ተከፍተዋል።
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሻሸመኔ እዲሁም የምዕራብ አርሲ 10 ወረዳዎች፣ ዝዋይ፣ መቱ ፣ ጅማ ፣አርሲ ነገሌ ከፍተኛው ውድመት የታየባቸው ናቸው። በጥፋቱ ተሳትፈዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ከተከሳሾቹ ውስጥ የከተማ ከንቲባን ጨምሮ የወረዳ አመራሮች እና የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበትም ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 90 ሐምሌ 18 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here