ለሶስት አመት የሚቆይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጀመረ

Views: 251

በበአሜሪካኑ እውቅ ዩኒቨስረሲቲ ሃርቫርድ እና በተራድኦ ድርጅቱ ዩኤስ ኤድ የሚደገፍ በማክሮ እና ገንዘብ ፖሊሲ ላይ የሚያተኩር አዲስ ፕሮጅክት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ነሐሴ 17/2011 ይፋ ተደረገ፡፡

በአራት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት የኮኖሚያዊ አማራጮች ማብዛትን አላማው ያደረገ እንደሆነ እና በተለይም በስራ ዕድለ ፈጠራ፣ ድህነት ቅነሳ፣ የገንዘብ አሰባሰብ እና አያያዝ ላይ ሚያተኩር እና በገንዘብ ተቋማቱ ውስጥም ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዙ ፖሊሲዎችን እና ሙያዊ አስተያየቶችን የሚያሰናዳ ይሆናል ተብሏል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ባለፉት 16 አመታት ትልቅ ኢኮኖሚ መሻሻሎችን አሳይታለች›› ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ‹‹ነገር ገን እንደ ውጪ ምንዛሬ እጥረት ያሉ ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ መፋለሶችንም ያየንበት ወቅት ነው፣ ይህንንም በመጪው ጥቂት አመታት ማስተካከል ያስፈልጋል›› በማለት የፕሮጀክቱን አስፈለጊነት ገልጸዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com