የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የንጹኀን ግድያ አወገዙ፤ ሁሉን አካታች የፖለቲካ ንግግር እንዲደረግም ጥሪ አቀረቡ

0
959

የአፍረካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐመት ዛሬ፣ ጥቅምት 24/2013 ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ በአጽንዖት አውግዘዋል። ለሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጥልቅ የሆነ ሐዘናቸውን የገለጹት ሊቀ መንበሩ፥ ለቆሰሉት ፈጥኖ መሻልን ተመኝተዋል። ይህንን ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል የፈጸሙትን መንግሥትን ተከታትሎ በመያዝ ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሩ ሁሉም ወገኖች ግጭቶችንን ከማባባስ እንዲቆጠቡና ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጥሪ ከማቅረብ በተጨማሪ ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ንግግር በፖለቲከኞች መካከል በመካሄድ ቀልፍ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ ስምምነት መድረስ ይገባል ብለዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በቀጠናው ላይ ጭምር ያስከትላል ሲሉ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላምና ደኅንነት ለማስፈን እየወሰደ ያለውን ማሻሻያ እንደሚደግፍ በድጋሜ በማረጋገጥ ሊቀ-መንበሩ መግለጫቸውን ደምድመዋል።

መሉውን መግለጫ ማስፈንጠሪያውን በመንካት ማንበብ ይችላሉ

https://au.int/en/pressreleases/20201103/statement-auc-chairperson-situation-ethiopia?fbclid=IwAR2DyyEp11fyjYP-513Yx2NUSl7uSFFBdlj5mR_Xl6BdQV4wJgKUrTE0oyM

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here