ዳሰሳ ዘማለዳ ረቡዕ ነሐሴ29/2012

Views: 376

1- በቀጣዩ ዓመት 2012 የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስን) ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ እና በተመጣጣኝ  ዋጋ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ እየሰሩ እንደሆነ የጤና ሚንስትሩ ዶ/ር አሚር አማን አስታወቀዋል። እንደማንኛውም የሕክምና ዕቃ እና መድኃኒት ተመርቶ እንዲከፋፈል እንደሚደረግ ተገልጿል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………

2 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት የሚወሰነው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተወሰዱ አራት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ፈተናዎችም እንግሊዝኛ፣ አፕቲቲውድ፣ ሂሳብ፣  እና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሲሆን፥ ፊዚክስ ቀርቶ ጂኦግራፊ የተካተተበት ደግሞ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መሆኑ ይፋ ተደርጓል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

3- የሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፓል ካጋሜን ጨምሮ ሦስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች በደቡብ አፍሪካ እየተካሔደ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚክ ጉባኤ ላይ ባለመሳተፍ በደቡብ አፍሪካ የሚፈፀመውን የመጤ ጠል ጥቃት አውግዘዋል። የዲሞክራቲክ ኮንጎ እና የማላዊ ፕሬዘዳንቶች በጉባኤው ላይ ያልተገኙ አፍሪካዊያን መሪዎች ናቸው። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………..

4- በአማራ ክልል ባለፉት ሦስት ዓመታት 400 ሽሕ የንብ መንጋ መቀነሱ ተገለፀ። ያጋጠመውን የንብ መንጋ መቀነስ ተከትሎም በየዓመቱ 15 ሽሕ ቶን የማር ምርት ሳይገኝ ቀርቷል። (አብመድ)

……………………………………………………

5- የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከካናዳው አግሪቲም ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በማዕድን ዘርፍ ላይ ያተኮረ ትምህርትን በመተመለከተ እንዲሁም በቴክኒክ እና በሙያ ዘርፍ ድጋፍ ዙሪያ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………..

6-ኢትዮጵያ በቅርቡ ከምታመጥቀው የመረጃ ሳተላይት በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት የሚያስችላትን የመረጃ መቀበያ ማዕከል(ሪሲቨር ስቴሽን) ግንባታ እያካሄደች ነው።ግንባታዉ ባሳለፍነዉ ሰኔ 2011 የተጀመረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 2012 ድረስ ተጠናቆ ስራ ይጀምራል። (ፋና ብሮድካስትንግ)

………………………………………………………………

7-  የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከመድኃኒትና ከሕክምና መሳሪያዎች የማዕቀፍ ግዢ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ማትረፍ ችሏል። ኤጀንሲው ለግዢ የሚያወጣቸውን የጨረታ ቁጥር ከ110 ወደ 45 የቀነሰ ሲሆን የሚወስደውንም ጊዜ ከአንድ ዓመት ወደ ስድስት ወራት ዝቅ አድርጓል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

8- የደቡብ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ ኃላፊዎች ላይ የቀረበውን ዋስትና ዕግድ አፀና። ፍርድ ቤቱ የ50 ሽሕ ብር ዋስ ፈቅዶ እንደነበርና ፖሊስ የምርመራ ጊዜውን እንዳልጨረሰ በመጥቀስ እንዲታገድ ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። (ዶቼ ቬለ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com