የንጉሡ ጥላሁን ሹመት

0
412

በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በተለይም ፌስቡክ አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካካል አንዱ የንጉሡ ጥላሁን የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሪታሪ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ነው፡፡ በአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር እያሉ በብዙዎች ዘንድ እውቅናን ያተረፉት ንጉሡ ከወር በፊት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን ማስነሳቱ ይታወሳል።
ይሁንና አሁን ላይ የፕሬስ ሴክሪታሪው ኃላፊ መሆናቸው ‹‹ትክክለኛ ቦታቸውን አግኝተዋል›› በሚል በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ውዳሴን እያስቸራቸው ነው። ከእነዚህም ውስጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የስራ ኃላፊው አዲሱ አረጋ ‹‹ወንድሜና የትግል ጓዴ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ሆነህ በመሾምህ እንኳን ደስ አለህ። የተሰጠህን ሀገራዊ ሃላፊነት በከፍተኛ ብቃት እንደምትወጣ ምንም ጥርጥር የለኝም!›› በሚል በፌስ ብኩ ገጻቸው ያሰፈሩት መልእክት በአንድ ቀን ብቻ ከ2500 በላይ ተጠቃሚዎች ተጋርተውታል፡፡
በሌላ በኩል የንጉሡንመሾም የሚገልጸው የጠቅላይ ሚንስትሩ ደብዳቤ ታኅሣሥ 25 ወጪ ቢደረግም ሹመቱ ከጥር 22 ጀምሮ እነደሆነ መገለጹ ለብዙዎች ጥያቄ ሆኖ እየተነሳ ነው፡፡ ብዙዎቹም ቀኑን ስህተት እንደሆነ በመጥቀስ የፈገግታ ምንጭ አድርገውታል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here