ዐቃቤ ሕግ በእነሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ በሶስት መዝገቦች ክስ መሰረተ

0
883

ዐቃቤ ሕግ በሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው፣ በኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ በቸርነት ዳና እና ረመዳን ሙሳ ላይ በአጠቃላይ በሦስት መዝገቦች ክስ መመሥረቱ ታወቀ። ክሶቹም፡-

1) አባይ ወንዝና አቢዮት የተባሉ ሁለት መርከቦች ያለ አግባብ ለግዥ፣ ለጥገና፣ ለአስተዳደራዊ ወጪና ለሽያጭ በሚል 545 ሚሊየን 483 ሺህ 103 ብር ያለ አግባብ እንዲወጣ በማድረግና አገር ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል ነው።

2) ከሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴልና ፒ ቪ ሲ ፕሮፋይል ማምረቻ ግዥ ሲፈጸም ከግዥ መመሪያ ውጭ ግዥው እንዲፈጸም ትዕዛዝ በመስጠት ያለ አግባብ 202 ሚሊየን 882 ሺህ 885 ብር እንዲባክን በማድረግ እና

3) የኢምፔሪያል ሆቴል ግዥ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በመስጠት ለሆቴሉ ግዥና ጥገና በሚል ያለ አግባብ 103 ሚሊየን 809 ሺህ 755 ብር እንዲባክን ማድረግን በሚል ተመልክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here