ዳሰሳ ዘማለዳ ማክሰኞ መስከረም 13/2012

Views: 348
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድና ዲኤች ኤል አብረው በጋራ የሚሰሩበትን ሁኔታ ያሻሻሉ ሲሆን ሦስት አዳዲስ ቅርንጫፎችን በሐዋሳ ኢንዲሰትሪ ፓርክ፣ በቦሌ ለሚ፣ እና በአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ያደራጁ ሲሆን አራተኛውን በቀጣዩ ወራት እንደሚጀምሩም አስታውቀዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………….

  • በእስራኤል አገር የሚገኝ አንድ መዋዕለ ሕፃናት ኢትዮጵያዊያን ዝርያ ያላቸውን ሕፃናት ተማሪዎች ላይ ማግለል በመፈፀሙ ተዘጋ። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

  • በ2012 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ አዲስ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ውል መፈረም እንዳለባቸው ሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………..

  • በኢትዮጵያ ምስራቃዊ ክፍል ሱማሌ ክልል ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ የድርቅ ስጋት እንዳጋጠመ ታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………….

  • በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአገሪቱ የሚገኙት የትምህርት ተቋማት 143 ሽሕ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን አስታወቁ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………….

  • ለኹለት ቀናት የሚካሔደው የሚካሔደው የአፍሪካ ሆቴሎች ፎረም በአዲስ አበባ ተጀምሯል። በፎረሙ ከ52 አገራት የተወጣጡ በሆቴል ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ተገኝተዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………

  • በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃ ዞን ደምበጫ ወረዳ በትናንትናው ዕለት በደረሰ የመኪና አደጋ የሟቾች ቁጥር 23 ደረሰ። (አብመድ)

…………………………………………………………………………

  • ከ30 በላይ የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አሽከርካሪዎችና ሰራተኞች ስራ የማቆም አድማ በማድረጋቸው ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን አስታወቀ (ሸገር)
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com