የእለት ዜና

ዳሰሳ ዘማለዳ ዓርብ መስከረም 16/2012

Views: 477

 

  • በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ትግበራ ይገባል። ትራንስፎርሜሽኑን በሚመለከትም የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም ለኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ገልፀዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………….

  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ለመስቀል ደመራ የሚካሔድበትን የመስቀል አደባባይ አካባቢ ከተለያዩ የኃይማኖት ተከታዮች እና የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን አፅድተዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

  • ቱርክ በኢትዮጵያ ለ19 ሽሕ ተማሪዎች ሙሉ ትምህርት መሳሪያዎችን ለገሰች። ልገሳው የተከናወነው ኢትዮጵያ በሚገኘው የቱርክ ኢምባሲ እና በባቡር ሐዲድ ግንባታ ላይ በተሰማራው ያፒ ማርኪዝ አስተባባሪነት ነው ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………………………………………

  • የቦይንግ ኩባንያ በፈረንጆች 2018 ጥቅምት ላይ የኢንዶኒዥያ አየር መንገድ በሆነው እና 189 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የላየን ኤር ቦይንግ 737 ማክስ 8 አደጋ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው። በኢትዮጵያ ለደረሰው ተመሳሳይ አደጋ 144ሽሕ 500 ዶላር እንደሚከፍል አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………….

  • የኤደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሐምሌ 1 /2010 እስከ ሰኔ 30/2011 ድረስ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ 4597 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። ባጋጠሙት አደጋዎች 7754 ከባድ ጉዳት እና 7775 ቀላል ጉዳት መመዝገቡንም አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………….

  • የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞችን እና ደንበኞችን ጤንነት ለመጠበቅ በማሰብ አዲስ የሬዲዮ ግንኙነት ስርዓት ስራ ላይ አዋለ። የሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን ፕሮጀክቱ የተፈረመው በኢትዬጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ሞቶሮላ ሶሉሽን በተሰኘው የእስራኤል ኩባንያ መካከል ነው፡፡ (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………….

  • የአዲ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ጥራቱ ያልተጠበቀ እና ከየት እንደተቀዳ የማይታወቅ ውሃ በመኪና እናቀርባለን የሚሊ ግለሰቦችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………

  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለኹሉን አቀፍ ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት ትግበራ የሚውል የ18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ (አዲስ ማለዳ)
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com