የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሰኞ ይከፈታል

Views: 347

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ሰኞ መስከረም 26/2012 ይካሔዳል። አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ይጀመራል።

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በ2011 በጀት ዓመት በዋና ኦዲተር አማካኝነት ኦዲት ግኝት የታየባቸውን ድርጅቶች የተጓደሉ ስርኣቶችን ፈትሾ በማስተካከል አገራዊ ሀብቱ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በትኩረትእየተሰራ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ምክር ቤቱ በአራተኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መንገድ በበርካታ ተቃውሞ እና ድምፅ ተኣቅቦ ውሳኔዎች መፅደቃቸው የዲሞክራሲ ስርኣቱ እየጎለበተ የመምጣቱ ማሳያ እንደሆነ አፈጉባኤው ገልፀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com