ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የኮሪያ ዘማቾች መርጃ ማዕከል ገነባች

Views: 363

በ1940ዎቹ በኮሪያ ልሳነ ምድር ይተካሄደውን ጦርነት ተከትሎወደ ስፍራው በማቅናት ከደቡብ ኮሪያ ጦር ጎን ለተዋደቁት የኢትዮጵያ የእግረኛ ጦር መርጃ የሚውል የዕርዳታ ማዕከል በደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ ተገንብቶ ተመረቀ። መርጃ ማዕከሉ በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ እና ባለኹለት ፎቅ እንደሆነም ታውቋል። በደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ የመርጃ ማዕከል ሲገነባ በዓይነቱ ይህ ሦስተኛው ሲሆን የመጀመሪያው በፈረንጆች 2014 በታይላንድ ባንኮክ የተገነባው ሲሆን ኹለተኛው ደግሞ በኮሎምቢያ ቦጎታ በፈረንጆች 2017 ተገንብቷል።

ደቡብ ኮሪያ በ1940ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከሰሜን ኮሪያ የተቃጣባትን ወረራ ለመመከት ከኢትዮጵያ 3500 እግረኛ ጦር መላኩን እና 122 የሚሆኑት እዛው በኮሪያ ልሳነ ምድር መሰዋታቸውን እና 536 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ተወስቷል። ለሦስት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ከተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 150 የሚሆኑት በህይወት መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በእርስ በርስ ጦርነቱ 2 ሚሊዮን ገደማ የተባበሩት መንግስታት ጦርም ወደ ስፍራው ተልኮ እንደነበርም ታሪክ ያወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com