አሰብ ወደብን ከኢትዮጵያ የሚያገናኘው መንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ

Views: 747

አሰብ ወደብን ከኢትዮጵያ የሚያገናኘው 71 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገለጸ። ከአሰብ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ የድንበር ከተማ ቡሬ ድረስ የተዘረጋው የ71 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለሚኖራት የንግድ ግንኙነት አመቺ ሁኔታን ከመፍጠርም ባለፈ በኢትዮጵያ በኩል ለሚኖረው የወጪ ንግድ አማራጭ ወደብ አገልግሎት እንደሚኖረውም ይጠበቃል።

አሰብ ወደብ ከአዲስ አበባ 882 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚርቅ ሲሆን 811 የሚሆነው በኢትዮጵያ በኩል የሚገኝ ሲሆን ቀሪው 71 ኪሎ ሜትር ደግ በኤርትራ በኩል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ግንባታው ተቸረሰው መንገድ በኹለቱ አገራት መካከል የተካሔደውን ጦርነት ተከትሎ ለ20 ዓመታት ተዘግቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በኹለቱ አገራት የነበረውን አለመግባባት በዕርቅ በመፍታት ግንኙነቱ እንዲጀምር በመደረጉ መንገዱምንም ወደ አገልግሎት ለመመለስ እንደተገነባ ታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com