ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 4/2012

Views: 179

1-‹‹የኢትዮጵያ ኤምባሲ ናይሮቢ ከተማ ከሚገኘው ከተባበሩት መንግስታት ስድተኞች ኮሚሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ስድተኞችን ካለፍላጎታቸው ወደ አገር ቤት ለማስመለስ ህዳር 03/2012 በናይሮቢ ከተማ ኢስሊ አካባቢ የውይይት ፕሮግራም አዘጋጅተዋል›› በማለት በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መልዕክት የተሳሳተ መሆኑን ኤምባሲው አስታውቋል።ኤምባሲው ከተባበሩት መንግስታት ስድተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ኢትዮጵያውያንን ከሙሉ ፍላጎታቸው ውጭ አንድም ሰው ቢሆን ለመመለስ የማይሰራና የማይተባበር መሆኑ አሰታውቋል።(አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………
2-በህዳር ወር በተወሰኑ የሰሜን፣ የምስራቅና የመካከለኛው የሀገሪቱ ተፋሰሶች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።የኤጀንሲው ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አደራጀው አድማሱ እንዳስታወቁት በአብዛኛው ገናሌ ዳዋ፣ ዋቤ ሸበሌ፣ ኦጋዴን፣ የመካከለኛውና የታችኛው ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞ ጊቤ፣የአባይ ደቡባዊ ክፍል እና በአብዛኛው ባሮ አኮቦ ተፋሰሶች ከመደበኛው የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል ብለዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ሰብሎች በመሰብሰብ ላይ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሚኖረው እርጥበት ጉዳት እንዳያደርስ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
……………………………………………………………………
3-ኢትዮጵያ ዘመናዊ የጤና መረጃ አያያዝ (Digital Health Activity) የተሰኘ የ63 ሚሊዮን ዶላር ፕሮግራም ይፋ አደረገች።ከአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት USAID በተገኝ የ 63 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ፕሮጅክቱ በአምስት አመት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።የገንዘብ ድጋፍ ለሐኪሞች ፣ ለነርሶች ፣ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ እና ለፖሊሲ አውጪዎች የጤና መረጃ ልውውጥን በቴክኖሎጂ የታገዘ እንደሚያደርግ የጤና ሚንስትሩ ዶክተር አሚር አማን ፕሮጅክቱ ይፋ ባደረጉበት ሰዓት ተናግሯል።(አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………
4-ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌግራም፣ ዋትስ አፕ እና መሰል ኩባንያዎች የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት ጥናት መጀመሩን አስታወቀ።እንደ ቫይበር፣ ዋትስ አፕ፣ ቴሌግራም ያሉ እና ሌሎችም የስልክ መተግበሪያዎች ያሏቸው ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጥሰውን ገብተው ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ቢገኙም የሚያገኙትን ጥቅም ለማጋራት የሚያስችል አሰራር እንደሌለው ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
……………………………………………………………………
5-የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (CAF) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር የሚያደርገውን ጨዋታ ከመቀሌ ወደ ባሕር ዳር እንዲያዛውር በደብዳቤ አሳሰበ።ኢትዮጵያ የስታዲየሞቿን የጥራት ደረጃ ዝቅተኛውን መስፈርት ካላሻሻለች ቀጣይ ጨዋታዎችን መስፈርቱን በሚያሟሉ የኮንፌዴሬሽኑ አባል ሃገራት ውስጥ ለማከናወን እንደምትጠየቅ ካፍ አስጠንቅቋል።(ዶቼ ቬሌ)
……………………………………………………………………
6-በጎንደር ዩንቨርሲቲ አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በሌላ ሰዉ መታወቂያ ወደ ግቢ ሊገባ ሲል በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የዩንቨርሲቲዉ የአለም አቀፍ ግንኙነት ቡድን መሪ በላይ መስፍን አስታወቀ። በጊቢዉ የሚገኙ ተማሪዎች ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት የተወሰኑ ተማሪዎች ድንጋይ በመወርወራቸዉ በወንጀሉ የተሳተፉ ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ገልጿል።(ለኢትዮ ኤፍ ኤም)
……………………………………………………………………
7-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 4/2012 ባካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅን አፅድቋል።(ኢቢሲ)
……………………………………………………………………

8- ‹‹መንግስት ዜጎችን ከጥቃት ለመታደግ የሚያሳየውን ትዕግስት ልክና ገደብ ሊኖረው ይገባ›› ሲሉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች አሳሰቡ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን በዜጎች መካከል የነበረውን የአብሮ የመኖር ፣የመተሳሰብ እና የመቻቻል እሴቶች ለማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ሚና ለወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com