ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 9/2012

Views: 253

1-ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የሚያገናኟትን የመንገድ ግንባታ እና ጥገና መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳምሶን ወንድሙ ቡሬ አሰብ ፤ ራማ መረብ እና አዲግራት ዛላምበሳ መንገዶች ጥገናቸዉ በመጠናቀቁ የትራንስፖርቱ አገልግሎቱ ካለ መንገዶቹ ዝግጁ መሆናቸዉን በመግለጽ ባለስልጣኑም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣቱን ተናግረዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
……………………………………………………………………
2-ኢትዮጵያ በኮርያ መንግስት የሚደገፈው ኮይካ እና ‬ቲ ኤንድ ሲ የኮርያ ድርጅት ጋር የ‬ፀሐይ ኃይልን ለመብራትነት ለመጠቀምና የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፓኬጆችን በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ለማዘጋጀት አብሮ ለመስራት ተስማማች።በተጨማሪም ኮይካ /KOICA/ በጤና ሚኒስቴር የዘለቄታዊ የልማት ግቦች አጋዥ ድርጅቶች 13ተኛ አባል በመሆን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በማኅበራዊ ገፃቸው ላይ አስታዉቀዋል።(ዋልታ)
……………………………………………………………………
3-በአዲስ አበባ ከተማ በኹለት ስፍራዎች በተከሰተ እሳት አደጋ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙ የከተማዋ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ አሰታዉቋል።አደጋው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ሽሮሜዳ አካባቢ በሚገኝው ልዩ ስሙ ቁስቃም የታቦት ማደርያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ አንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው።በአደጋውም 200ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን አምስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ተገልጿል።ሁለተኛው የእሳት አደጋ የደረሰው ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስራ ሶስት ልዩ ስሙ ፊጋ መብራት ኃይል አካባቢ በሚገኘው የብሎኬት ማምረቻ ቤት ላይ የደረሰ እሳት አዳጋ ሲሆን አደጋ ምክንያት አንድ ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ለውድመት የተዳረገ ሲሆን አምስት ሚሊየን ብር የሚሆን ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ስለሺ ተስፋዬ ተናግረዋል።(ኤትዮ ኤፍ ኤም107.8)
……………………………………………………………………
4-በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ ወደ ውጭ አገር ከተላኩ 102 ሺሕ 916 ነጥብ 50 ቶን የቡና፣ሻይና ቅመም ምርቶች 287 ነጥብ 59 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን አስታወቋል።የቡና አፈጻጸምም ከታቀደው አንጻር በመጠን 103 ነጥብ75 በመቶ እንዲሁም በገቢ 83 ነጥብ 59 በመቶ የታየበት ገልጿል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
……………………………………………………………………
5-የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ኹለት የግል ኮሌጆች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፏል።በመመሪያ ጥሰት ምክንያት የመዘጋት ውሳኔ የተላለፈባቸዉ ኮሌጆችም ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ (አዳማ ካምፓስ ) እና ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ (አድዋ ካምፓስ) መሆናቸው ናቸው አስታውቋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………………
6-የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተቋሙን ማቋቋሚያ አዋጅ ገለልተኛነት እና ነፃነት የሚፈትሽ አደረጃጀት እየዘረጋ መሆኑን አስታወቀ።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሕዝቡ የሚጠብቀውን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ አገልግሎችን ለመስጠት የሚያስችለው የለውጥ ሥራዎች እየሠራ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።(ኢቢሲ)
……………………………………………………………………
7-የኢትዮጵያ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ኢትዮጵያን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትደርስ የሚያስችል ቢሆንም ከፍተኛ ሁኔታ የአፈፃፀም ችግር እንዳለበት ተገልጿ። የመናበብ ችግር፣ በቅንጅት ያለመስራት፣ ቴክኖሎጂ ከመማርና መጠቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች፣ የኢኖቬሽን ስርዓት ያለመጠናከር ችግሮች እንዳሉ የኢኖቬሽን ምርምርና ሽልማት ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል አብረሃም ደበበ (ዶ/ር) ተናግሯል።(አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………
8-በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የምርት ብክነትን መቀነስ የሚያስችል በጸረ ተባይ ኬሚካል የታከመ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ ነው።በአማራ ክልል አባይ ማዶ 1 ነጥብ 5 ሔክታር መሬት እና በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ ገላን ከተማ 2 ነጥብ 5 ሔክታር መሬት እንደተሰጠው በመግለፀ ግንባታው በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚጀምር መሆኑን በእድሜአለም እጅጉ ቢዝነስ ግሩፕ አስታውቋል።ግንባታው ከ2 እስከ 3 ዓመት ባለው ጊዜው ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ግንባታው ሲጠናቀቅም የሰብል ብክነትን መቀነስ የሚያስችል 500 ሺሕ በፀረ-ተባይ ኬሚካል የታከመ የእህል መያዣ ከርጢት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com