ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኹለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

Views: 135

ኢትዩጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኢመሬቶች በኹለቱ አገራት ጥቅም ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ እና በተባበሩት ዐረብ ኢመሬቶች የመከላከያ ሚንስትር ዲኤታ መሐመድ ቢን አሕመድ አል ቦዋርዲ መካከል ተፈርሟል።

ኢትዮጵያ በኹለቱ አገራት ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ በተመለከተ  ያላትን ቁርጠኝነት ለማ የገለፁ ሲሆን፤ መሐመድ ቢን አሕመድ በበኩላቸው ስምምነቱ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር የምታደርገው ስምምነት አካል እንደሆነም አስታውቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com