የአማራ ክልል ጽንፈኛ ያላቸውን ሚዲያዎችን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ

Views: 352

የአማራ ክልል መንግሥትከሚዲያ ስነ ምግባር ባፈነገጠ መንገድ ሰርተዋል ያላቸውን የሚዲያ ተቋማት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አቅርቦ ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ጌትነት ይርሳው እንዳስታወቁት በአማራ ክልል በቅማንት ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ችግር በመመርኮዝ ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨት አስበው የሰሩ የሚዲያ አካላት እንዳሉ ጠቁመዋል።

ይህንም በማስመልከት የክልሉ መንግሥት በዚህ እኩይ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን አራት የሚዲያ ተቋማት ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ከማስረጃ ጋር በማቅረብ ሒደቱን እየተከታተለው እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በቀጣይም በጽንፈኛ ሚዲያዎች አማካኝነት በክልሉ ህዝብ ላይ የሚቃጡ የስነ-ልቦና ጥቃቶችን በማስረጃ ላይ ተመስርቶ በመታገል በኩል የኮሙዩኒኬሽን መዋቅሩ በትኩረት መስራት እንደሚገባውም አቶ ጌትነት አክለው ገልጸዋል፡፡

የመጀመሪያው ሩብ ዓመቱን ግምገማ ያካሔደው የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አመራሩና ባለሙያው ተናቦ በመስራት ተቋሙ የጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ በማስገንዘብ አጠናቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com