ሕብረት ባንክ 979 ሚሊዮን ብር በላይ ከግብር በፊት ማትረፉን አስታወቀ

Views: 195

ሕብረት ባንክ አክሲዮን ማኅበር የዳሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው ዓመታዊ ሪፖርት ከፈረንጆች ሐምሌ 1/ 2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ ባለው አንድ ዓመት 979 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ከትርፍ ግብር በፊት ማትረፉን አስታወቀ። ባንኩ በዚህ ዓመት ያስመዘገበው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 38 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የጠቆመው የዳሬክተሮች ቦርድ አምና ከትርፍ ግብር በፊት ከተመዘገበው የ272 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ልዩነት ያለው ትርፍ ማስመዝገቡንም አስታውሷል።

የባንኩ 22ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ በተካሔደበት ወቅት በቀረበው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው፤ ሕብረት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ከሐምሌ 1/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ባለው ጊዜ ውስጥ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱም ተጠቅሷል። ይህም የገቢ መጠን ከቀዳሚው ኣመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 1 ነጥብ 02 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም በመቶኛ ሲሰላ 36 ነጥብ 5 በመቶ እንደሆነ ተጠቁሟል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com