ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 12/2012

Views: 318

1-ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ታህሳስ 7/2012 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ላይ ወደ ህዋ እንደምታመጥቅ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አስታወቋል።72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው የመጀመሪያዋ ሳተላይት ወደ ህዋ እንደምትመጥቅ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር(ዶ/ር) ጌታሁን ተናግረዋል።ሳተላይቷ ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኝ የማስወንጨፊያ ጣቢያ ላይ ትገኛለች።ሳተላይቷ በመጀመሪያው ክፍል ወደ ህዋ በማምጠቅ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ማስቀመጥ ይሆናል።2ኛው ተግባር ደግሞ እንጦጦ በተገነባው የኢትዮጲያ ስፔስ ሳይንስ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በኢትዮጲያውያን ቁጥጥር ይደረግባታል መረጃዎችም ይሰበሰቡባታል ብለዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 )
……………………………………………………………………………….
2-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ንግድ ባንኮች ለተበዳሪዎች ከሚያቀርቡት እያንዳንዱ የብድር ገንዘብ ውስጥ የ27 በመቶውን አስልተው ቦንድ እንዲገዙ የሚያዝዘውን መመሪያ ማንሳቱን አስታወቀ።ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የ27 በመቶ አስገዳጅ ቦንድ መመርያ ባንኩ አሁን ላይ ማንሳት እንዳስፈለገው አምኜበታለሁ ብሏል።(ፋናብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………………………….
3-ኢትዮጵያ በቅርቡ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት መሰረተ ልማትን ልታስተዋውቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ አስታወቁ።መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓቱን ለማዘመን እየሰራ እንደሆነ ገልጸው መሰረተ-ልማት አቅርቦትን ለማስፋፋትና በዘርፉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………………………….
4-በኢትዮጵያ የቆዳ ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ በ12 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ የቆዳ ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ 34 ሚሊዮን አሜሪካን ዶላር ገቢ ብታገኝም ከዓመናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ12 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳያቱን ኢንስቲቲዩቱ አስታውቋል።በዘርፉ 27 የቆዳ ፋብሪካዎች፣ 23 የጫማ ፋብሪካዎች ፣4 የጓንት ፋብሪካዎች፣ 13 የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች የሚያመርቱ እንዲሁም ከ40 በላይ አነስተኛና መካከለኛ ፋብሪካዎች አንደሚገኙ የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርሃኑ ሥርጀቦ ተናግረዋል። (ኢቢሲ)
……………………………………………………………………………….
5-የኢትዮጵያ መደኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለስኳር በሽታ የሚውሉ Insulin Isophane Human 100.Iu/ml in 10 ml injection ወደ አገር ውስጥ ማስገባቱን አስታወቀ።በኤጀንሲው የመደበኛ መድኃኒት ግዥ ባለሞያ ሜቲ ገመቹ እንዳሉት መድኃኒቶቹ 61 ፓሌት እንደሆኑና በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ዋናው መስሪያቤት መጋዘን 3 እና አዲስ አበባ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ መጋዘን ገብተዋል።መድኃኒቶቹ ከ325 ሺሕ ዶላር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ባለሙያዋ ጠቁመው ጤና ተቋማት መድኃኒቶቹን ማግኘት እንደሚችሉም ተናግረዋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
……………………………………………………………………………….
6-በሶማሌ ክልል እና በሌሎችም አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ የሚገባዉ የአንበጣ መንጋ ባለመቆሙ ተጨማሪ ኹለት አዉሮፕላኖች መመደባቸዉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።በሚኒስቴር የእጸዋት ጥበቃ ዳይሬክተር ዘብዲዮስ ሰላቶ እንደገለጹት ከዉጭ የሚገባዉን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል በአራት አዉሮፕላኖች የታገዘ የመከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
……………………………………………………………………………….
7-በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት በተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ሳቢያ የ132 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ከ500 በላይ ሰዎችን ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አብዛኛው አደጋ የተከሰተው ከማሽከርከር ብቃትና ስነ-ምግባር እንዲሁም ከመንገደኞች ጥንቃቄ ጉድለት ጋር በተያያዘ መሆኑም ተገልጿል።(ኢዜአ)
……………………………………………………………………………….
8-ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ሒደት ውስጥ የድንገተኛ አደጋ እና ዝግጁነት ፖሊሲ መኖር አንዱ መስፈርት መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ ብሔራዊ ፓርኮች ላይ ባጋጠመው የቃጠሎ አደጋ 10 ሺሕ ሔክታር መውደሙን፣ ከእነዚም መካከል ቃፍታ ሑመራ፣ አሰቦት፣ ነጭ ሳር፣ ኦሞ እና ሰሜን ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ ቦታዎች የሸፈነ ቃጠሎ አጋጥሟቸው እንደነበር በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለሥልጣን የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጌትነት ይግዛው ገልጸዋል።(ኢቢሲ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com