ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ግለሰቦች የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ

Views: 260

በተያያዘ ዜና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን )የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስትያን ታደለ ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል። ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ “ሕገ መንግስትን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ክስ መስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በማረፊያ ቤት የደህንነት ስጋት አለብን በሚልም ለችሎቱ ያቀረቡ ሲሆን በምርመራ ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶች እንዲመለሱላቸው መጠየቃቸውን ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ተከሳሾቹ ለቀረበባቸው ክስ የመቃወሚያ ምላሻቸውን ለታህሳስ 1/2012 እንዲያቀርቡ ችሎቱ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ከደህንነት ጋር ላነሱት ጉዳይ በማረሚያ ቤት ሆነው ጥብቅ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አዟል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com