የእንግሊዝ ኤምባሲ ለሰራተኞቹ ግጭት በተከሰተባቸው የኢትዮጵያ አከባቢዎች ሲጓዙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ

Views: 340

በኢትዮጵያ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ለሰራተኞቹ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ባለው ግጭት ምክንያት የጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰቧል። በተለይ በሶማሊያ እና በኦሮምያ ድንበር መካከል በምስራቅ እና በምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች እና በኬንያ ድንበር ላይ ያሉ አከባቢዎች ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የብዙ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጿል። ኢምባሲው በመግለጫው እንዳካተተው የውጭ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ባይፈጠርም በውጭ ዜጎች በተደጋጋሚ የሚጎበኙ ቦታዎች ላይ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ የሚችሉ አሸባሪዎች መኖራቸውንም አሳስቧል። በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው ግጭት ምክንያት የመንገድ መዘጋት፣ ለአከባቢያዊ ንግድ እና መጓጓዣ መቋረጥ እያስከተለ መሆኑ ያሳወቀው ኤምባሲው እነዚህ ክስተቶች በቆዩ ቁጥር አከባቢው እተጎዳ መሆኑን ገልጿል። ግጭቱ በሚኖርባቸው ቦታዎች የሚወስደውን ማንኛውንም ጉዞ ዕቀድ እንዲመለከቱና ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ እንዳይጓዙ አሳስቧል ። በየዓመቱ 20,000 እንግሊዛዊያን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እንደሚመጡ ኤምባሲው ያስታወቀ ሲሆን አብዛኞቹ ጉብኝቶች ከችግር ነፃ እንደነበሩም አስታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com