ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በፍሬህይወት ቁጥር አንድ የአፀደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ

Views: 259

ትናንት ኅዳር 17/2012 ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፍሬህይወት ቁጥር አንድ የአፀደ ሕጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ ተማሪዎች የጤና መታወክ ያጋጠማቸው ሲሆን ዛሬ ኅዳር 18/2012 ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ  በመገኘት የመማር ማስተማር ሂደቱን ጎብኝተዋል። ምክትል ከንቲባው ብጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የተከሰተው የጤና መታወክ ከምግብ መመረዝ ጋር ግንኙነት እንደሌለው እና ተማሪዎቹ በመልካም ጤንነት እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ፍሬህይወት ቁጥር አንድ የአፀደ ሕጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ኅዳር 17/2012 ጠዋት ላይ 25 ተማሪዎች እና 5 አስተማሪዎች ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች ተወስደው ሕክምና  ተደርጎላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ፍርህይወት አዳል ለአዲስ ማለዳ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።

በቦታው የተገኙት አዲስ አበባ ጤና ቢሮ  ባለሞያዎች ተማሪዎች ጠዋት የተመገቡት ምግብ ለምርመራ ናሙና መውሰዳቸውን የገለፁ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ የሆነው የምገባ ፕሮግራሙን ተቋማዊ ለማድረግ በከተማው ምክር ቤት በአዋጅ እንደሚፀድቅ እና ተቋሟዊ በሆነ መልኩ የምገባ መርሃ-ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታከለ ኡማ  ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት አስታውቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com