የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የመረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ

Views: 440

ኢትዮጵያ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ በእንጦጦ ኦብዘረቫቶሪና ምርምር ማዕከል ውስጥ እየገነባች ሲሆን የመሬት ምልከታ ሳተላይት መቀበያ አንቴናም ዛሬ ኅዳር 19/2012 ተገንብቶ ተጠናቋል። የኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ ቴክሎጂ ኢኒስቲቲዩት እንዳስታወቀውተገንብቶ የተጠናቀቀው ሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና በመጪው ወር ታኅሳስ 1/2012 ወደ ህዋ ኢትዮጵያ የምታመጥቀውን ሳተላይት መረጃ ለመቀበል እንደሚረዳ አስረድቷል።

 

ጣቢያው መረጃዎችን ከመቀበል ባለፈ ሳተላይቶች በአግባቡ ተልዕኳቸውን መፈፀማቸውን ክትትል የሚደረግበት፣ የሳተላይቶች ደህንነትና እንቅስቃሴንም ቁጥጥር የሚደረግበት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የእንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ ፕሮጀክት ከተለያዩ ሳተላይቶች መረጃ መቀበል የሚያሥችል አንቴናና መረጃዎች የሚተነተኑበት የመረጃ ማዕከል ግንባታም እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃ ፍላጎቷን በከፍተኛ ወጪ የምታገኝ ሲሆን ፤ ይህንን በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለግዢ የሚወጣ የአገር ሃብት ለማዳን ያስችላል፡፡

የጣቢያው መገንባት በአገር ውስጥና በአጎራባች አገራት ለሚገኙ የሳተላይት መረጃ ተጠቃሚዎች የመረጃ አገልግሎቱን በመሸጥ ገቢ ማስገኘትም እንደሚያስችል ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com