10ቱ ከጥቅል ምርት አንጻር ከፍተኛ ዕዳ ያለባቸው አገራት

Views: 88

አገራት ቀዳዳቸውን ለመድፈን በየደረጃቸው ገንዘብ ይበደራሉ። ብዙውን ጊዜ ብድር የሚወስዱ አገራት ከአፍሪካ እንደሆኑ ብዙዎች የሚገምቱ ቢሆንም፤ አድገዋል የተባሉ አገራትም ቀላል የማይባል ብድር ተበድረዋል፤ ቀላል የማይባል ዕዳም አለባቸው።
ታድያ ከፍተኛ እዳ ካለባቸው አገራት ተርታ የምትገኘው ጃፓን ናት። ጃፓን ከ9 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ዕዳ ተሸክማ ያለች አገር ናት።
ይህ ዕዳዋ ከዓመታዊ ምርቷ አንጻር ሲታይም 237.54 በመቶ ነው። ዕዳው በገንዘብ ተቆጥሮ የተቀመጠ እንደሆነ ኹለተኛ ከፍተኛ ዕዳ ያለባት አገር ግሪክ ናት፤ ይህም 379 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ነው። ከዓመታዊ ጠቅላላ ምርት አንጻር ግን የግሪክ ዕዳ 174.15 በመቶኛ ሆኖ፣ ከአስርቱ ተርታ አራኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
የዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ድርጅት /IMF world/ን ጠቅሶ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው ባስነበበው ዘገባ፣ በአስርቱ ዝርዝር ከአፍሪካ አገራት መካከል ኤርትራ በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ኢትዮጵያ ጠቅላላ ዕዳዋ ከጥቅል ዓመታዊ ምርት አንጻር 57.43 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 59 ታኅሣሥ 11 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com