በቢሾፍቱ በሚገኘው ኢስት አፍሪካ ታይገር ብራንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሳሙና ፋብሪካ ላይ ጥር 23 የተነሳ የእሳት አደጋ ለኹለት ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡
በአደጋው ስድስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረትም ወድሟል። በአንጻሩ 200 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡
አደጋው ቀኑ 10፡00 አካባቢ ቢነሳም ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እስከ ምሽቱ 3፡30 ድረስ ጊዜ ወስዷል ተብሏል፡፡ የአደጋው መንስኤም እየተጣራ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ 59 ባለሙያዎችና 10 የአደጋ መቆጣጠሪያ ተሸከርካሪዎች ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከኦሮሚያ ፖሊስና ከቢሾፍቱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጋር መተባበራቸው ተነግሯል፡፡
በፋብሪካው ያሉ ግብዓቶች ተቀጣጣይነትና የቦታው ርቀት እሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ረዘም ያለ ሰዓት እንዲወሰድ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011