በአፍሪከ ኅብረት ቅጥር ግቢ የቆመው የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ኃውልት የኅብረቱ መሪዎች ኃይለሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ኃውልት እንዲቆምላቸው በወሰኑት መሰረት የተሰራ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳለው ኃውልቱ የመሪዎቹ ጉባኤ በሚካሄድበት ዕለት የካቲት 3/2011 በይፋ ይመረቃል።
በጉባኤው ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካዊያን አርቲስቶች የሚካፈሉበት የሙዚቃ ዝግጅት ይካሄዳል።
መጪው 32ኛ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በተለያዩ ደረጃዎች በሚካሔዱ ስብሰባዎች ከጥር 30 እስከ የካቲት 4 የሚቆይ ነው።
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011