መንግሥት የግል ትምህርት ቤቶችን ጥራት የሚከታተልለት ተቋም ሊመሰርት ነው

0
839

በግል ትምህርት ቤቶች ላይ ከትምህርት ጥራት ጋር ተያይዞ የሚታዩና በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ያግዛል የተባለ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ሊያቋቁም እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ኤጀንሲው የግል ትምህርት ተቋማት መንግሥት ባወጣው የትምህርት ስርዓት ማዕቀፍ ብቻ እንዲመሩ የሚስገድድና የሚቆጣጠር ነው።

ተማሪዎቻቸው አማርኛ ቋንቋን እንዳይናገሩ ጫና እስከመፍጠር የሚደርሱ የግል ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ለተወካዮች ምከር ቤት የገለጹት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) ለመቋቋም በዝግጅት ላይ የሚገኘው ኤጀንሲ በስርዓተ ትምህርቱ አሰጣጥ ላይ መስፈርት እንዲወጣ ያግዛል ብለዋል።

መንግሥት የግል ትምህርት ቤቶች የማለውቀውን የትምህርት ዓይነት እየቀረጹ ያስተምራሉ ሲል፣ ወላጆች በበኩላቸው ለማይታወቁት ትምህርት ዓይነቶች ጭምር በሚዘጋጁ በርካታ መጻሕፍት ክፍያ እየተማረሩ እንደሆነ ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡

ሚኒስቴሩ ከግል የትምህርት ተቋማት ማኅበር ጋር በመሆንም ለግል ትምህርት ተቋማቱ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ አክለዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here