ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥር 6/2012

Views: 997

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስተዳደር የሚያደርስባቸው የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ሠራተኞች ተናገሩ::  ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በበኩሉ ተቋሙ በጥብቅ ሥነ-ምግባር በመመራቱ የተቋሙን ገጽታ ለማጠልሸት ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኞች ወቀሳ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል። (ኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ)

……………………………………………………………………..

ኢትዮ-ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ
22 ነጥብ 04 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ። ይህም የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካት የቻለ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ከዓምናው
ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 32 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታወቁ። (ኢትዮጵያ
ፕሬስ ኤጀንሲ)

……………………………………………………….

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የታችኛው እርከን ላይ
ለውጥ ባለመኖሩ ጥርጣሬ እንደፈጠረባቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) ተናገሩ። (ኢትዮ
ኤፍ ኤም)

…………………………………………………….

ዛሬ ጥር 6/2012 ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ
በአረዳ ክፍል ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሰባት ሱቆች ላይ በደረሰ እሳት አደጋ ኹለት ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ።
(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………………..

ሰላምን በመስበክ ወደ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ
የሚደረገው የጎዞ መርሃ ግብር ዛሬ ጥር 6/2012 በጋሞ አባቶች ከአርባ ምንጭ ተጀምሯል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………….

የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል በሚል አዲስ የተረቀቀው አዋጅ በህገ መንግስቱ መጠነኛ ገደቦች ተጥለውበት ለዜጎች የተፈቀደውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን ሊገድብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ። (ሸገር)

…………………………………………………………………….

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት 121 ወረዳዎች ውስጥ 95 ያህል የሚሆኑት
ዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ለተገልጋዮች መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኹነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።
(ኢቢሲ)

…………………………………………………………..

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com