ዩኤስ ኤይድ እና አዋሽ ባንክ የ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

Views: 962

የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ እና አዋሽ
ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን አነስተኛ ገንዘብ ተቋማት፣ እነዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የግብርና እንቅስቃሴዎችን
በገንዘብ ለመደገፍ የ6ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ጋራ ስምምነት ተፈራረሙ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግብርና አሰራር ለማዘመን
እንዲሁም አርሶ አደሮች ዘንድ የሚኖረውን የገንዘብ ፍላጎት ይደግፋል የተባለው ይኸው ስምምነት በዩኤስ አይድ ልማትና ብድር ባለስልጣን
በኩል እንደሚከወን ታውቋል።

የግብርና ሴክተሩን ለማጎልበት በአዋሽ ባንክ
በኩል ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑ የጠቀሱት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፀሐይ ሽፈራው አዋሽ ባንክ ከግብርና ጋር በተያያዘ
ለሚሰጡ ብድሮች ላይ የሚጥለውን ወለድ በተጨባጭ የሚታይ ቅናሽ ማድረጉንም ጨምረው አስታውቀዋል።

በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ታቅፈው ውጤታማ ለሆኑ
አርሶ አደሮች ገንዘብ የሚያገኙበትን መንገድ ለመጨመር አካባቢያዊ የገንዘብ ተቋማት ማበደር አቅማቸው መጠናከር እንዳለበትና ለዚህም
የግል የገንዘብ ተቋማት ወሳኝ መሆናቸው ተጠቁሟል።  

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com