ዳሰሳ ዘ ማለዳ (ጥር 7፤ 2012)

Views: 1015

የአውሮፓ ህብረት መጪውን
ምርጫ እንዲታዘብ ከኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ ቀረበለት። ህብረቱ በቀረበለት ጥሪ መሰረትና የምርጫ ሰሌዳውን ከግምት ውስጥ በማስገባት
ውሳኔውን ያሳውቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ሰሌዳው ረቂቅ ይፋ በሆነበት ወቅት ተናግረዋል።
የምርጫ ታዛቢዎችን የሚመለከተው መመሪያ ሲፀድቅ የሚያስቀምጠውን መስፈርት በሟሟላት ምርጫውን ሊታዘቡ እንደሚችሉም ሰብቢዋ ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የትራፊክ ህግ ጥሰት ክፍያ ላይ ተቃውሞ አለን ያሉ የታክሲ ሹፌሮች ዛሬ ጥር 7/2012 የስራ ማቆም አድማ አካሂደዋል።
ሹፌሮቹ አዲስ የተተገበረው የክስ ሪከርድ አያያዝ የቅጣቱን መጠን አንሮብናል፣ ሪከርዱም በምን ላይ ተመስርቶ እንደሚያዝ በተደጋጋሚ
ብንጠይቅም ማብራሪያውን የሚሠጠን አካል ባለመኖሩ ለከፍተኛ ወጪ እና እንግልት እየተዳረግን  ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ምርጫ ነክ ክርክሮችን
በልዩ ሁኔታ ለመዳኘት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
መዓዛ አሸናፊ ከሶስቱም ፌደራል ፍርድ ቤቶች የበላይ አመራሮችና የምድብ ችሎት አስተባባሪዎች ጋር የምርጫና ሌሎች ተያያዥ ህጎችን
በተመለከተ ምክክር አድርገዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ግብርና ሚኒስቴር ብሔራዊ
የገጠር መሬት አስተዳደር መረጃ ስርአት አያያዝን ይፋ አደረገ። ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የቆየው የመሬት ይዞታ ባህላዊ፣ መረጃው በወረቀት
ላይ ብቻ የሚቀመጥ፣ አቅጣጫን ብቻ የሚጠቁምና የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት የማያሳይ ነበር ተብሏል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
የስነ ምግባር ጉድለት ተገኝቶባቸዋል ባላቸው 52 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታቋል። ከዚህ ቀደም የመማር ማስተማሩን ሂደት
አስተጓጉለዋል የተባሉ 69 ተማሪዎች ጥፋተኝነታቸው ተጣርቶ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልጾ ነበር። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

አዋጭነት ጥናት ሳይደረግባቸው
በ240 ቢሊየን ብር የተጀመሩ 16 የመንግስት ፕሮጀክቶች ከተጀመሩ በኋላ መቋረጣቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል። ፕሮጀክቶቹ
የተሟላ የጥናት ሰነድ ቅድመ ዝግጅት እና የዲዛይን ጥናት ሳይኖራቸው ወደ ግንባታ መገባቱ ለመቋረጣቸው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
(ኢትዮ ኤፍኤም)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ጅቡቲ በዶራሌሕ የኮንቴነር
ወደብ ጉዳይ ዱባይ ወርልድ ከተባለው ዓለም አቀፍ የወደቦች አስተዳዳሪ ኩባንያ በገባችበት እሰጥ አገባ በግልግል ፍርድ ቤት የተላለፈውን
ውሳኔ እንደማትቀበል አስታወቀች። ወደቡን ለ30 አመታት ለማስተዳደር የገባው ውል በፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ መንግሥት የፈረሰበት
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኩባንያ መቀመጫውን በለንደን ባደረገ ፍርድ ቤት በጀመረው ሙግት እንደተፈረደለት ገልጾ ነበር። (ዶቼ
ቬለ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com