የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን የካቲት አምስት ሊያካሄድ ነው

Views: 446

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 5/2012  አስቸኳይ ጉባኤውን የሚያደርግ ሲሆን  ምክር ቤቱም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡

እሁድ ከየካቲት 1/2012 ጀምሮ  የአንድ ወር እረፍት የነበሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከአራት ቀን በኋላ ለአስቸኳይ ጉባኤ የተጠሩ ሲሆን በጉባኤው ላይም በ10 አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣  የኤክሳይዝ ታክስ፣ የፌደራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት፣ በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቀቅ አዋጆችን ያጸድቃሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com