የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመናዊ የድሮን መሳሪያ ሙከራ ላይ ሊውል ነው

Views: 326

በምስራቅ አፍሪካ በኢትዮጵያ፣ሶማሊያ እና ኬኒያ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ኬሚካል በመርጨት ለመከላከል እንዲሁም ለመቆጣጠር የሚያስችል  ዘመናዊ የድሮን መሳሪያ  ወደ ሙከራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታትም በክፍለ ዘመኑ እንዲህ ዓይነት ችግር አጋጥሞ እንደማያውቅ በመግለጽ ጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ኡጋንዳም የአንበጣ መንጋው እንደተከሰተባቸው አስታውቋል፡፡

እንደ ሪሊፍዌድ ዘገባ ከሆነም የአገራቱ ባለስልናት የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ቢገልፁም ባለሙያዎች ግን ኬሚካል የመርጨቱ ስራ በተለይም በረሃማ አካባቢዎች ላይ ኬሚካሉን ለመርጨት እንደተቸከሩ እንዲሁም በቀን እስከ 150 ኪሎሜትር ለመጓዝ እንዳስገደዳቸው ጠቅሷል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት የአንበጣ ትንበያ ባለሙያው  ኬትዝ ክሬስማን በበኩላቸው  ድሮኑ አንበጣዎችን በመለየት በፍጥነት እና ከፍታ ላይ በመውጣት  ኬሚካሉን የመርጨት ሥራ ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በመጠቆም  ውጤማነቱ ግን  ከዙህ በፊት ተጠቅመንበት ስለማናውቅ ለመገልፅ አዳጋች ነው ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com