የግብርናውን ስራ የሚያዘምኑ 624 ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተፈቀደ

Views: 602

 

የግብርና ስራ ለማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ የግብርና ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነጻ ማስገባት መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር ለአዲሰ ማለዳ ገለጸ፡፡

ቁጥራቸው ወደ 624 ከሚጠጉ የግብርና ማሽነሪዎች መካከል ትራክተር ከነ ሙሉ ዕቃው፣ የመስኖ መሳሪያ ፓምፖች፣ የላቦራቶሪ እቃዎች ይገኙበታል ሲሉ የሚኒስቴሩ የግብርና ኤክስቴንሽን ዋና ዳይሬክተር ገርማሜ ገሩማ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል ፡፡

ይህም ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚባክነው አጠቃላይ የግብርና ምርት ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዘመናዊ መንገድ በታገዘ መልኩ በፍጥነት ለመሥራት ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማሻሻያው የተደረገው ገበሬዎች ያለን ውስን ኃይል ስለሆነ በዚህ ሁኔታ መቀጠል አንችልም ብለው በመጠየቃቸው እንደሆነም ገርማሜ አስታውሰዋል፡፡

ለግብርና ተብለው የሚገቡ ማሽነሪዎች ከቀረጥ ነጻ መሆናችውን ተከትሎም ለሌላ ጥቅም እንዳይውሉ  መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ማሽነሪዎቹ ከቀረፅ ነጻ ሆነው ይገባሉ ተብሎ ከተነገረ በኋላ የገቡ ማሽነሪዎች ባይኖሩም ገርማሜ በመንግስት በኩል ያለው ሥራ ተጠናቋል ሲሉም አክለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com