ከሕግ ውጪ ሲያስተምሩ የተገኙ ስድስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘጉ

Views: 229

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በ25 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ጉብኝት የእውቅና ፍቃድ ሳያገኙ እና ከተፈቀደላቸው የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብለው ሲያስተምሩ የተገኙ ስድስት የግል ከፍተኛ ተቋማት መዘጋታቸውን አስታወቀ፡፡
ከተዘጉት ተቋማት መካከል ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ካምፓስ፣ ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ አድዋ ካምፓስ እና በጋምቤላ ከተማ ፤ ላትጆር ኮሌጅ፣ዌስተርን መካኢየሱስ ኮሌጅ፣ ሾውቤል ኮሌጅ እና ሉተራን ካቶሊክ ኮሌጅ ይገኙበታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 67 የካቲት 7 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com