በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የውጭ እዳ ጫና ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መክፈሏ ታውቋል።
መንግሥት አገሪቱ ካለባት 26 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እዳ በተያዘው በጀት ዓመት 22 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የመክፈል እቅድ አለው።
ከአጠቃላይ እዳው 57 ነጥብ ሦስት በመቶው የማዕከላዊ መንግሥቱ የተበደረው ነው።
በሌላ በኩል ከሐምሌ 2010 ጀምሮ ባሉት አምስት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 977 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑ የአገሪቱ የእዳ ጫና ቶሎ እንዳይቃለል ማድረጉ ተነግሯል።
መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ምርት እንዲገቡና እዳውን እንዲያቃልሉለት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በፍጥነት ወደ ምርት ለማይገቡ ፕሮጀክቶች ብድር አለመውሰድ እና ከቻይና ጋር እንደተደረገው የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምለት መደራደርን እንዲመርጥም ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ቅጽ 1 ቁጥር 13 የካቲት 2 ቀን 2011