ኢትዮጰያ ለኤርትራዊያን ስትሰጥ የቆየችውን የቡድን ጥገኝነት አቆመች

Views: 651

የኢትዮጵያ መንግሰት ላለፉት ሶስት አመታት ከኤርትራ ድንበር አቋርጠው ለሚመጡ ኤርትራዊያን የቡድን እውቅናን መሰረት በማድረግ ጥገኝነት በመስጠት ስታስተናድ ብትቆይም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን ይህንን ማቆሟን አስታወቀች፡፡

ይህም ከተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ወቀሳ እያስነሳ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት የስተደተኞችን ስምምነት የጣሰ ነው ተብሏል፡፡

የወል ጥገኝነት ማለት የአንድ አገር መንግስት ወይም የተባበሩት መንግሰታት የስደተኞች ኮሚሽን ስደተኞች ከሚሰደዱበት አገር ባለ ሁኔታ፣ አገር አልባ ከሆኑ እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች በግል ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያበቃ ምክንያት እንዳላቸው ሳይጠየቁ የዛ አገር ዜጋ ወይም የዛ ቡድን አባል ከሆኑ ብቻ የሚሰጥ የጥገኝነት አይነት ነው፡፡

በእንግሊዘኛው ፕሪማ ፋሼ ተብሎ የሚታወቀው ይህ የወል ጥገኝነት በአለማችን ላለፉት 60 አመታት በመተግበር ላይ ያለ ሲሆን አንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ከሆነም በአለም ላይ ያሉ አብዛኞቹ ስደተኞች በወል በሚሰጥ ወይም በፕሪማ ፋሼ መሰረት ጥገኝነት ያገኙ ናቸው፡፡

አዲስ ማለዳ በዚህ ጉዳይ በኤርትራ ካሉ ነዋሪዎች በስልክ ለመረዳት እንደቻለችው ሱዳን አስገድዳ የመለሰቻቸው ስደተኞች ላይ የኤርትራ መንግስት ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም የሚለ መረጃዎች ተሰምተዋል፡፡

በባድመ ድንበር ዙሪያ ‹‹መገፋፋት እና ውጥረት›› እንዳለ እደሚሰሙ እና ከዛ ውጪ ባሉ ድንበሮች በኩል ግን ምንም ነገር ያለመስማታቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ኤርትራ ከዚህ ወዲ የጦር መሳሪያ ጦርነት ውስጥ አትገባም ይለቁንም ኢኮነሚ ጦርነት እንጂ ማለታቸው በአስመራ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበተንም ይናገራሉ፡፡

በባድመ በኩል ያለው ውጥረት ኢሳያስ እስከዛሬ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ስጋት አለ በማለት የቆዩትን በትረ መንግሰታቸውን አሁንም ሌላ ስጋት በመፍጠር የሚያደርጉት ነው ብሎ ነው አብዛኛው ህዝብ የሚያምነው›› ሲሉም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ ‹‹አቢይ አህመድም ለኤርራዊያን ሳይሆን ከኤርትራ በሚገኝ ወደብ መገንባት በሚፈልገው የባሃር ሃይል ነው ፍላጎታቸው የሚል እምነት አለ›› ብለዋል፡፡ ዐቢይ በኤርትራውያን ዘንድ ያላቸው ተወዳጅነት እና ተቀባይነትም ማሽቆልቆሉን ይናገራሉ፡፡

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2012 የበጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የቀረበ ሪፖርት እንደሚያሳየው በየቀኑ እስከ 400 የሚጠጉ ኤርትራዊያን የኢትየጵያን ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡ መግለፁ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ከ መስከረም 6 እስከ 1/1969 በተደረገ ውይይት በመጨረሻው ቀነ የፀደቀው የአፍሪካ ህብረት የስደተኞች ኮንቬንሽን አንቀፅ ሁለት ንኡስ ቁጥር ሶስት ማንም የህብረቱ አባል አገር ማንኛውንም ሰው ለህይወቱ ወደ ሚያሰጋው አገር መልሶ መላክ አይችልም፡፡ ማንኛወም ሰው በድንበር ላይ ሳለ የጥገኝነት ጥያቀው ውድቅ ሊደረግ አይገባውም የሚለው ይህ የአዲስ አበባ ስምምነት ከአካላዊ ደህንነት ባሻገር ጥገኝነት ጠያቂው ሰው ነፃነቱን ወደ ሚያጣበት አካባቢ ተመልሶ እንዲሄድ መደረግ እንደሌለበትም ያትታል፡፡

አንድ አገር ጥገኝነት ለመስጠት የሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ ብትገባ እንኳን በህብረቱ በኩል ከሌላ አገር በአፍሪካዊ አንድነት ድጋፍ መጠየቅ እንምትችልም ብኡስ ስር ያስቀምጣል፡፡ አሳይለሙን የሚሰጡ አገራትም የድንነት ስጋት ካለ ስደተኞቹን ከተሰደዱበት አገር ከድንበር አርቆ የማስፈር ስራ መስራት እንዳለበትም ይሄው ኮንቬንሽን ይደነግጋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 67 የካቲት 7 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com