የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በገንዘብ እጥረት ተቀዛቅዟል

0
914

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን በቻይና ኩባንያ ግንባታው በ2009 የተጀመረው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በገንዘብ እጥረት እየተጓተተ መሆኑን አረጋግጧል።

በቀን 24 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል የተባለው ፋብሪካ በገጠመው ግንባታ በጀት እጥረት መቀዛቀዙን ሥራ አስኪጁ ተናግረዋል።
ቀድሞ በ70 ቻይናዊያንና ከ500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ይሳተፉበት የነበረው ፋብሪካ ግንባታ መቀዝቀዝም አሁን ላይ በ11 ቻናዊያንና ከ65 በማይበልጡ ኢትጵያዊያን እንዲሰራ ተገዷል።

የበጀት ዕጥረት ያጋጠመው ስኳር ኮርፖሬሽን ለአበዳሪው የቻይና ልማት ባንክ የግዴታ ክፍያና ወለድ በድምሩ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ባለመከፈሉና ባንኩ ገንዘቡን በመያዙ ነው ተብሏል።

ቋሚ ኮሚቴው ክፍያዎች ላይ ያለው መጓተት በፍጥነት እንዲፈታና ግንባታው እንዲፋጠን አሳስቧል።

ቅጽ 1 ቁጥር 13 የካቲት 2 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here