የታሰሩት የሲአን አመራሮች ተፈቱ

Views: 203

 

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) የካቲት 14/2012 በሐዋሳ የሚያደርገውን ስብሰባ አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ አራት አመራሮች ታስረው የነበረ ሲሆን ትላንት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ መፈታታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ፡፡

ስብሰባውን እንዳናከናውን በክልሉ መንግስት በኩል ጫና ደርሶብናል የሚሉት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዱካለ ላሚሶ፣ ዛሬ የካቲት 13/2012 የተደረገውን የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ታስተጓጉላላችሁ ተብለን መንግስት እግልት ፈጽሞብናል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በነገው ዕለት የ2012 አገራዊ ምርጫን በተመለከተ ከደጋፊዎቻችን እና ከአባላቶቻችን ጋር እንመክራን ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የሲዳማን ክልልነት የሥልጣን ርክክብ በተመለከተም የደቡብ ክልል መንግሥት ላይ ጫና እናደርጋለን ያሉት ዱካለ እስካሁን መዘግየቱም አግባብነት የለውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ይህንን የሥልጣን ርክክብ ማድረጉን ወደ ኋላ በመተው የብልጽግና ፓርቲን ለመደገፍ መቀስቀሱም የክልሉን ሰው ትዕግስት እየተፈታተነው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com