መዝገብ

Author: ኤፍራታ አሰፋ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በወልዲያ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጥቅምት 29/2012 በወልዲያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመዉን የግድያ ወንጀል እና ድብደባ አወገዘ። ኦፌኮ ‹‹የነገን ወጣት ትውልድ በመግደል ደም በማፍሰስ እና ሕዝብን አጋጭቶ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገው ሩጫ ይቁም!›› ሲል ባወጣው መግለጫ፤ ‹‹በሕገ ወጦች የተፈጸመውን የተማሪዎች ድብደባ እና…

የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት ወር ብቻ 32 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት ወር ብቻ 32 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 97 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካቱን አስታወቀ። ይህ አፈፃፀም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የገቢዎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በቅንነት፤…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 1/2012

1-ከሰባት ወር በፊት በጊቤ ሸለቆ የሞቱት ከ30 በላይ ጉማሬዎች በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘው መገደላቸው በጥናት ተረጋገጠ። ሚያዝያ ወር 2011 ዓ.ም በጊቤ ሸለቆ ከ30 በላይ የሚሆኑ ጉማሬዎች መሞታቸዉን ያስታወሰው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘዉ እንደተገደሉ በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል። በተጨማሪም በካፍታ ሽራሮ ብሔራዊ…

“መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ ያወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ

በገቢዎች ሚኒስቴር ድረ ገጽ ላይ ጥቅምት 29/2012 ግብር ከፋዮችን ከቅጣት ለማዳን “መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ የወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ ። የበዓሉ ቀን መሥሪያ ቤቱ ዝግ እንደነበር በድረ ገጹ ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ነገር ግን…

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኹለት ተማሪዎችን ሕይወት በቀጠፈው በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ። በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር መግለጫ መሰረት፣ በግጭቱ ላይ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሔደባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በተረጋጋ ሁኔታ ላይ…

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ምርመራ መጠናቀቁ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ አስታወቀ

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ‹‹ታስቦበት፣ ክህደት የተፈጸመበትና ለስልጣን ጥም የታሰበ ነው›› ሲሉ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር የወንጀል ምርመራ መጠናቀቁን ባሳወቁበት ወቅት ተናገሩ። በተፈፀመው ጥቃት  ሰለባ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች መካከል የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት አምባቸው መኮንን(…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 28/2012

1-የትዊተር መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የአፍሪካ አገራትን በዚህ የህዳር ወር እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።ጉብኝታቸውንም በናይጄሪያ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ በማምራት ከሥራ ፈጣሪዎች ጋር እንደሚወያዩም በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።ከኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ የሥራ ፈጣሪ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 26/2012

1- የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላን ተደጋጋሚ ብልሽት እያጋጠመው መሆኑ አንበጣን ለመከላከል እንቅፋት እንደሆነበት የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የእድገት ደረጃውን ጨርሶ እንቁላል ለመጣል በሚያስችለው ደረጃ የደረሰውን አንበጣ ለመከላከል የሚከናወነውን ሥራ ፈታኝ ካደረጉት መካከል አንበጣው ያረፈባቸው አካባቢዎች በአውሮፕላን ርጭት ለማድረግ አመቺ አለመሆናቸውም ጭምር…

በደቡብ አፍሪካ ሕክምና ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ የኩላሊት ታማሚ የገቢ ማሰባሰቢያ ሊደረግ ነዉ

በደቡብ አፍሪካ የኩላሊት ሕክምና እንዳታደርግ ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ ዓለም ኤርሴሎ፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሦስት ቀን ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምረዋል። ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላት ኢትዮጵያዊቷ ዓለም በደረሰባት የኩላሊት ሕመም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበረግ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ስታገኝ የነበረ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ዜግነትም…

የኢትዮጵያን የጦር ኃይል በማጠናከር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ውይይት ተካሔደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ዕዝ አዣዥ ከሆኑት ከጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ ጋር ዛሬ በቢሯቸው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ወታደራዊ ኃይልን ከማጠናከር አንጻር የነበረውን የረዥም ጊዜ የትብብር ግንኙነት በማስታወስ፣ የአገሪቱን ጦር ሠራዊት አቅም ለመገንባት የአጭር…

የሶማሌ ክልል ፓርቲዎች አብሮ ለመሥራት ውይይት አደረጉ

በሶማሌ ክልል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ጥቅምት 25/2012 ውይይት ማድረጋቸው ታወቀ። ድርጅቶቹ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት በቀጣይ በጋራ የሚሠሩባቸውን ጉዳዮች በጹሑፍ የሚያዘጋጁ አምስት አባላት መሰየማቸውን የሶማሌ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ አስታውቋል።…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 24/2012

1- ከጥቅምት12 እስከ 24/2012 ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ 14 ያህል ነጥቦችን ያካተተ መግለጫ አውጥቷል።በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተለያዬ ቋንቋ ተናጋሪዎች በብዛት እንደሚገኙ ያመለከተው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ “የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታዮች በቋንቋቸው ማስተማርና ማገልገል እንዲቻል በየአሕጉረ ስብከቶቹ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 21/2012

1-በአዲስ አበባ ከተማ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በ69 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ከ20 ሺሕ 504 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ጥቅምት 22/2012 እንደሚጀመር ተገለጸ።ለቤቶቹ ግንባታ ከ55 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበ ሲሆን ወጪው በከተማ አስተዳደሩ እና በባንክ ብድር ይሸፈናል።በ20/80…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 20/2012

1- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እያደረጉት በሚገኘው ውይይት ላይ “እንዳንሳተፍ ተደርገናል” በሚል የአምቦ ከተማ ወጣቶች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ውይይቱ እየተካሄደ ባለበት ወቅት በአምቦ ዋና አውራ ጎዳና ላይ የተሰባሰቡ ወጣቶች ተቃውሟቸውን በግልጽ ሲያሰሙ ተደምጠዋል። “ቄሮዎች በስብሰባው ላይ መሳተፍ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 17/2012

1 ከሰሞኑ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ በአማራ ክልል በሰብል ላይ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለማድረሱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። (ቢቢሲ) ……………………………………………………………….. 2- ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በብሔራዊ ደረጃ ባካሔደው የደም ልገሳ መርሓ ግብር ለመሰብሰብ አቅዶት ከነበረው…

ዳሰሳ ዘ ማለዳማክሰኞ ጥቅምት 11/2012

1-ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ለከፍተኛ ጎርፍ እና ዝናብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል። በተለይም አገራቱ ከባድ ዝናብና የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲፈራረቅባቸው ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያና የሱዳን ደቡባዊ ክፍሎች፣ ኡጋንዳ፣ የታንዛንያ ሰሜን ክፍል እንዲሁም ኬንያ ለጎርፍ ተጋላጭ…

በሲጋራ መለኮሻ ላይተር የተነሳ ነፍስ ያጠፋው ግለሰብ እስራት ተፈረደበት

የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ስጠኝ በሚል በተነሳ ጥል የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት ተፈረደበት። ተከሳሽ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ሰኔ 19/2011 ከቀኑ 11:00 ሰዓት የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ስጠኝ በሚል ከሌላ ግለሰብ ጋር በተነሳ ጥል…

ዳሰሳዘ ማለዳ ሐሙስ ጥቅምት 6/2012

1-  የመስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ታላቁ የህዳሴ ግድብ የማመንጨት ኃይል ከ6 ሺሕ 500 ሜጋ ዋት ወደ 5 ሺሕ 150 ሜጋ ዋት እንዲቀነስ መደረጉን አምነዋል። ይህንን የተናገሩት ዛሬ ለሚኒስትሮች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ሲሆን በተርባይን ቅነሳው ላይ የግብፅ ፕሮፖዛል…

ዘምዘም ባንክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን ሸጠ

በምስረታ ከሚገኙት የኢስላሚክ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነዉ ዘምዘም ባንክ  1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ መሸጡን አስታወቀ። ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር የሚያወጣው አክሲዮን የተከፈለ ሲሆን ቀሪው በቅርቡ ይከፈላል ተብሎ ይጠበቃል። በጉዳዩ ላይ ዛሬ ጥቅምት 6/2012…

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በጎንደር የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ጥቅምት 6/2012 ተመርቀ። በ20 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባው ትምህርት ቤቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በይፋ በከፈቱበት ወቅት፤ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል የትምህርት…

ኢትዮ ቴሌኮም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 10 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 10 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል። ዛሬ ጥቅምት 6/2012 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃጸም በተመለከተ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ረቡዕ ጥቅምት 5/2012

1-   የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ODP) ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲው የውስጥ አንድነትን በተመለከተ ውይይት መጀመሩን አስታውቋል። በውይይቱ ወቅት ለአገራዊ ለውጡ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው የመፍትሔ አቅጣጫ እንደሚቀመጥላቸው የተገለፀ ሲሆን ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ ፓርቲ ያለውን አፈጻጸምን በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጉዳዮችን ለይቶ እንደሚወያይ ታውቋል።…

የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች በሙስና ክስ ተመሰረተባቸው

 ከወር በፊት በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ላይ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ። የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕግ ማሰከበር ኃላፊ አህመድ መሐመድ እና ምክትል ኃላፊያቸው…

የቡና ገለፈት ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት የሚቀይረው ፕሮጀክት ተመረቀ

የቡና ገለፈት ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት የሚቀይረው የምርምር ፕሮጀክት በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ተመረቀ። የምርምር ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የስራ ኃላፊዎች ፣የደብረ ብረሃንና የዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የፋብሪካ ተወካዮች እና የአካባቢው አርብቶ አደሮች በተገኙበት ተመርቆ ርክክብ ተደርጓል። በኢትዮጵያ በባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት…

ኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን ዶላር የቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ‹‹ልታገኝ ትችላለች››

ኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን ዶላር የቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ከአለም ባንክ ማግኘቷ እርግጥ እንደሆነ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ይናገር ደሴ ከብሉም በርግ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አስታውቀዋል። ባለፈዉ በጀት አመት 1ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ኢትዮጵያ ማግኘቷ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱም…

ኖኪያ የ4G እና 5G ቴሌኮም አገልግሎት ለመዘርጋት አስቧል

ኖኪያ ከአዲስ አበባ ሳይንስና የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የዲጂታል ክህሎትንና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት እና በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርሟል። የ4G እና 5G የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን የገለፀው ኩባንያው ለሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ አለም…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2012

1- የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔው የሚከናወንበት ቀን በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ባወጣው መግለጫው፥ የደቡብ ክልል ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ምክር ቤት ህዝበ ውሳኔው የሚካሄድባቸው ቀበሌዎችን ዝርዝር ለመስከረም 2 ቀን 2012…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ አርብ ጳጉሜ 1/2011

1-  መንግስት የተቋረጠውን ፈሳሽ የምግብ ዘይት ላይ የሚደረገውን ድጎማ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀምር ተገለፀ። በተጨማሪ ለአዲስ ዓመት በዓል 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት፣ 120 ሺህ ኩንታል ስኳር፣ 165 ሺህ ኩንታል ስንዴ፣ 100 ሺህ ኩንታል ጤፍ ለሸማቾች መዘጋጀቱን አዲስ አበባ ከተማ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com