መዝገብ

Author: ሊድያ ተስፋዬ

መታጠፊያው መንገድ

የ2012 አገራዊ ምርጫ ቀኑ ተወስኗል። ከወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ እንዲሁም ምርጫው ይደረግበታል ከተባለው ሰሞን የአየር ጸባይ ጋር በተገናኘ፣ የፖለቲካ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ ነበር። ሆነም ቀረ፣ ያም ሆነ ይህ ምርጫው መካሄዱ እንደማይቀር ቁርጥ ሆኗል። ይህም እንደ አገር ለኢትዮጵያ፣ እንደ ዜጋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ…

አምስቱ የመከራ ዘመን – በየካቲት 12 መነጽር

በጋዜጠኝነት አገልግሎቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ኞኞ የተለያዩ የታሪክ መጻሕፍትንም ለአንባብያን አድርሷል። «የኢትዮጵያና የጣልያን ጦርነት» የተሰኘው መጽሐፉ አንዱ ነው። ይህ መጽሐፍ ጣልያን ኢትዮጵያን ዳግም ለመውረር ተጠቃሽ ሰበብ የሆናትን የወልወል ግጭት ጉዳይን ያነሳል። «ማንኛውም የጣልያን ወታደር የረገጠው መሬት ሁሉ የጣልያን ቅኝ ግዛት መሆን…

ከየት እንጀምር?

ባለፈው ሳምንት የወለደች እህታችንን ለመጠየቅ ወደ የካቲት ሆስፒታል አቅንተን ነበር። በዛን ቀን የተወለዱትን ያህል ልጆች በየአንዳንዱ ሆስፒታልና በየአንዳንዱ ቀን የሚወለዱ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከታሰበው ጊዜ ፈጥኖ ራሱን እጥፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጠረጠርኩ። ጥርጣሬዬ ወደ ጎን ይቀመጥና፣ ትዝብቴን ላኑር። ኢትዮጵያ አሁን…

እውቀትን ፍለጋ

ሕይወት አንድም ሰዎች ባከበሩት ፍላጎታቸው መሠረት የሚሄዱት ጉዞ ነው፤ ከሕልማቸው ለመድረስ። የኑሮ ሁኔታ ግድ ብሎ ባልፈለጉት መስክ ቢሰማሩ እንኳ፣ የሚፈልጉትን በማሰብ ውስጥ ጉዞው መኖሩ አይቀርም። አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው ባይሆንም በሌሎች ሕይወት ውስጥ ጉዞውን በማየት የሐሳብ ሸክማቸውን ያቀላሉ። እንዲህ ያለ የሕይወት…

አይበቃም?

ከሰሞኑ በሴቶች ላይ የደረሱ ጥቃቶች ብሶባቸው ታይተዋል። በተለይም በቤት ውስጥ ጥቃት ‹ባል ሚስቱን ገደለ› የሚል ዘግናኝ ዜና ሰምተናል። ከማውገዝ፣ ደጋግሞ ከመናገርና ከማሳሰብ ውጪ ምን ይደረግ ይሆን? እንደተለመደው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንጩኽ ይሆን? ስድብ ይሻላል? እህቶቻችን እንደ ቅጠል ሲረግፉ እየተከተልን በሰልፍ…

የተዘነጋው የሕጻናት ዓለም – በጉዲፈቻ መነጽር

ምርጫ ካርድ ወስደው ለፓርቲዎች ድምጽ የመስጠት እድሜ ላይ አልደረሱም። እንደ ብሔር ‹ተጨቁነናል› ብሎ የሚሟገትላቸው፣ እንደ ጾታ ‹መብታችን ይከበር› ብሎ የሚጮኽላቸው አክቲቪስት ነን ባይ ተወካይ የላቸውም። የጣሏቸው አዋቂዎች ሆነው ድምጽ እንዲያሰሙላቸው የሚጠበቁትም እነዛው አዋቂ የተባሉ ሰዎች ናቸው። መንግሥትም፣ ማኅበረሰብና አገርም የሕጻናትን…

ይልመድባችሁ!

ከአንድ/ኹለት ወር በፊት ጀምሮ ታገቱ የተባሉ ሴት ተማሪዎች ነገር ብዙዎቻችንን እንዳሳሰብን ግልጽ ነው። በሐሳባችን ላይ የቤተሰቦቻቸው ሐዘን እና እንባ ተጨምሮ እንደ ሰው ከሚያስበው ውጪ ፖለቲከኞችም ለየገዛ ፍላጎታቸው ግብዓትና መሣሪያ እንዳደረጉትም ይታያል። ግን እንደው ይሄ የፖለቲካ ሆነ እንጂ! የሴቶች መታገት አዲስ…

ጌዴኦ – በደራሮ የደመቁ መልኮቿ

ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ነው ጌዴኦ ዞን ዘልቀን ዲላ ከተማ ያረፍነው። ከመንገድና ከሙቀት ድካም ያተረፈውን ሰውነታችንን አረፍ ከማድረጋችን ካረፍንበት ሕንጻ አልፎ ጩኸትና ጫጫታ እንዲሁም ጭስ አካባቢውን ሸፈነው። በኋላ ስንረዳ ዲላ በመላዋን በጭስ ታጠነች፣ ጩኸት ሞላት፣ የመኪና ጡሩንባ አጥለቀለቃት። ምክንያቱ ለብዙዎቻችን በቶሎ…

ፈንድቃ – የነገ ባህል ማእከል

ካዛንችስ አካባቢ ጥቂት የማይባሉ የአዝማሪ ቤቶች ይገኙ ነበር። ሆኖም በአካባቢው መልሶ ማልማትና መሰል ምክንያቶች በርካቶቹ ሲፈርሱና ቦታውን ለቀው ሲሄዱ፣ ጸንቶ በቦታው ሊቀር የቻለው አንዱ የባህል ቤት ፈንድቃ ነው። ስምረት ሺፈራው እንደ ፈንድቃ ባሉ የባህል ቤቶች ውስጥ የባህል ሙዚቃዎችን ከጓደኞቿ ጋር…

ደኅንነት ይሰማሻል?

የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት። እህቴ ስለሆነችና በቅርበት ስለማውቃት፣ ከተማሪነቷ ላይ ጎበዝ፣ በራስ መተማመን ያላትና ደፋር መሆኗን አውቃለሁ። ገና ተማሪ ስለሆነችና ዋናውን የሕይወት ሩጫ ባለመጀመሯ፣ አላት ብዬ የማምነው ጥንካሬ እንዳላት የምታውቅ አይመስለኝም። በቀደም ግን ከማይባት ጥንካሬ ውስጥ ሌላ ዓለም…

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ዕድገት – ሀብት ወይስ ስጋት?

መንገዶች፣ የገበያ ቦታዎች፣ ከከተማው ውጪ ጉዞ የሚደረግባቸው የአውቶብስ መናኽሪያዎች፣ የእምነት ተቋማት ወዘተ ከእለት እለት የሚንቀሳቀሱባቸው ሰዎች ብዛት እየጨመረ ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ከተሞችም ፍልሰትን የሚያስተናግዱ በመሆኑ፣ ግርግሩና መጨናነቁ ሕዝብ እየበዛ ለመሆኑ ማሳያ ሆነዋል። ባለሙያዎች በሰጡት ትንበያ መሠረት ደግሞ…

‹‹መንገድ ላይ መሰንቆ ይዞ መሄድ ፋሽን የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል››

ትውልድን እድገቱ አዲስ አበባ ነው። ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ ከሆነው ማሲንቆ ጋር የሚገርም መግባባት አላቸው። የማሲንቆን አቅም በሚገባ እንደተረዳ ያስታውቃል፤ ያሻውን ሙዚቃ፤ የአገር ቤቱን ምት ይሁን የባህር ማዶ ዘመናዊ መሣሪያ የሠራውን ዜማ በማሲንቆው መጫወት ያውቅበታል። ሀዲስ ዓለማየሁ ይባላል፤ በቅጽል ሥሙ ሀዲንቆ።…

‹‹የኔ ዜማ›› – ጥበበኞችን ያገናኘ የባለዜማው አልበም

አበበ ብርሃኔ፣ ይልማ ገብረአብ፣ አማኑኤል ይልማ፣ አብርሃም ወልዴ፣ አበጋዝ ክብሮም፣ አቤል ጳውሎስ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ፀጋዬ ደቦጭ፣ አየለ ማሞ እና ሰለሞን ሳህለ እንዲሁም ናትናኤል ግርማቸውና ሌሎችም፤ በሙዚቃው አንጋፋ ከሆኑ እስከ ጀማሪዎቹ ድረስ የተሳተፉበት ነው፤ ‹የኔ ዜማ› አልበም። እንዲህ ያሉ በርካታ የሙዚቃ…

ከማይዳሰሱ ቅርሶች ምዝገባ በስተጀርባ – ያልተዘመረላቸው ባለሙያ

ከነገ ጥር 10/2012 ከተራ ጀምሮ በማግስቱ የጥምቀት በዓል የጊዙ ዑደቱን ጠብቀው ደርሰዋል። የዘንድሮው ጥምቀት ታድያ ከወትሮው ለየት የሚያደርገው አንድ ጉዳይ አለ፤ ይህም በዓሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኒስኮ ላይ በሰው ልጆች ወካይ ዓለማቀፍ ቅርስነት መመዝገቡ ነው። ዩኔስኮ…

የወጥ ቤት ችሎታ!

እንዲህ ሆነ፤ እድሜያቸው ሰማንያውን እየጨረሰ እንደሆነ አኳኋናቸው የሚያሳብቅ፤ ቁመታቸው አጠር ያለ፤ እንደው እንዲህ ነው ብለው የማይገልጹት ግን አለ ቢባል ሁሉም ሊስማማበት የሚችል ደርባባነት የሚታይባቸው እናት ናቸው። በለጋ እድሜ የትዳር አጋራቸው በሞት ከተለይዋቸው በኋላ ብዙውን የሕይወት ፈተና ለብቻቸው ተጋፍጠው ልጆቻቸውን ከቁምነገር…

ስዕልና ማሳያ ስፍራው

የስዕል ጥበብ ለኢትዮጵያውያን እንግዳ አይደለም። ዘመናዊ የአሳሳል ጥበብ የሚባለው ሳይተዋወቅ አስቀድሞ፣ ሰዓልያኑ ቀለምን ከቅጠላ ቅጠል አዘጋጅተው፣ በግድግዳዎችና በብራና ላይ ሲጠበቡ ኖረዋል። ስዕልን መተረኪያ፣ የጽሑፎቻቸው ማብራሪያና ማድመቂያም አድርገው ተገልግለውባቸዋል። ዛሬስ? ዛሬ ላይ ዓለም በምትሄድበት ፍጥነት አይደለ፣ በእጅጉ እያዘገመም ቢሆን የኢትዮያ የስዕል…

‹‹ስለወጣቶች እያወራን እንጂ ወጣቶችን እያወራናቸው አይደለም››

‹‹ባልንጀራዬ›› ይሰኛል፤ በማኅበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ ‹‹ባልንጀራዬ /Balinjeraye›› በሚል ሥያሜ ይገኛል። ሌላውን እንደራስ የመውደድ እንቅስቃሴ ነው። በአሜሪካዊው አንድሪው ዴኮርት (ዶ/ር) የተመሠረተ እንቅስቃሴ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፋካሊቲ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ረዳት ፕሮፌሰር ተካልኝ ነጋ ምሥረታው ላይ አሉበት። ሰላምና…

በዓለ ልደት – በቅዱስ ላሊበላ

‹‹የልደት ደሃ የለውም›› ይላሉ፤ የገና ወይም በዓለ ልደት በተለያዩ ቦታዎች ሲከበር በድምቀት እንደሆነ ሲያስረዱ። በጎንደር የመንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም የድጓ መምህር የሆኑት ቀለመወርቅ ደምሌ፤ ‹ገበገባኒ› በተሰኘ መጽሐፋቸው፣ ስለ ገና በዓልና አከባበሩ ባተቱበት የመጽሐፉ የመጨረሻ ምዕራፍ፤ ‹የልደት ሰሞን አዝመራ ወደ ቤት…

በመጻሕፍቱ ቃል አትታበይ!

ከቅርብ የሥራ ባልደረቦች ጋር ከሚነሱ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሴቶች ጉዳይ እንዲሁም ‹ፌሚኒዝም› ነው። በቀደም ታድያ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተጠቅሶ ክርክር ወይም ምልልስ ተጀመረ። እናት አባትን ማክበርን ከሚጠቅሰው የቅዱስ መጽሐፍም ሆነ የቁርዓን ክፍል ይልቅ ብዙዎች መርጠው የሚያውቁት ‹ሴት ለወንድ ትገዛ› ዓይነት…

ከባድ ሴት?

ዛሬም በአንድ ገጠመኝ ልነሳ። ለሥራ ጉዳይ ከከተማ መውጣት ኖሮብኝ ማለዳ የተሳፈርኩት አሽከርካሪ ሾፌር ጋር በጨዋታ መካከል ስለሚሠራበት ተቋም ባለቤት አለቃው ተነሳ። ሴት ናት። በብዙ ተቃውሞዎችና በብዙ ድጋፎች መካከል ሳይሞቃት ሳይበርዳት ሥራዋን የምትሠራ። ‹‹ሥራ እንዴት እየሆነላት ነው?›› ስል ጠየቅሁ። ‹‹ኧረ እሷ…

‹‹አእምሮን በተገደበ ነፃነት ውስጥ ማንቀሳቀስ ትርፉ ባርነት ነው››

‹‹ጉንጉን›› እንዲሁም ‹‹የወዲያነሽ›› በተሰኙ መጻሕፍቱ ይታወቃል፤ ኃይለመለኮት መዋዕል። እርሱ ዋናው ሥራዬ መምህርነት ነው፤ ደስታና ክብር የሚሰማኝ በመምህርነቴ ስጠራ ነው ቢልም፤ እነዚህ መጻሕፈቱ ዘመን ተሸጋሪ ደራሲ አሰኝተውታል። ሰሜን ሸዋ ማጀቴ ከተማ 1943 ነው ትውልዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ወሎ ኮምቦልቻ የተማረ ሲሆን፣…

የአምቦ ጎጆዎች

አለፍ አለፍ ብሎ የልዩ ኃይል መለዩ የለበሱና መሣሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ይታያሉ። ጠበብ ያለ መንገዷ በርከት ያሉ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ውር ውር ይላሉ፤ የተወሰኑ የጭነት መኪናዎችም ዳር ዳር መንገድ ይዘው ያታያሉ። ጭር አላለችም፤ ነዋሪዎቿ ማልደው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ብዙ ጊዜ ስሟ…

የባለ አሻራ ትውልዶች ጥያቄ

‹‹እስከ ምሽት 5፡30 ድረስ ፊልም እያየሁ ነበር። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ግን ዐይኔ ማየት አቁሞ ነበር።›› አለ። በአንዲት ጀንበር ልዩነት የሕይወቱ አቅጣጫ፣ መንገድ እና አካሔዱ የተቀየረበት ጋዜጠኛው ሰለሞን ታምሩ። ገፍቶ ሊያልፍ ያልቻለውን ተራራ ሌላ መንገድ ፈልጎ የማለፍ ጽናትና ጥንካሬ ያለው ወጣት…

ነፍሰጡር ሚስቱን በጭካኔ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

መስከረም 21/2010 ምሽት 4 ሰዓት በተፈጠረ ጊዜያዊ ጸብ ከሦስት እስከ አራት ወር የሚሆን ጽንስ በሆዷ የነበረውን ሕጋዊ የትዳር አጋሩን በጭካኔ የገደለው ግለሰብ በ16 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ። በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በተለምዶ ሐያት ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት ጥንዶች…

‹‹ባምር ጠላሁ!››ን ማሸነፍ!

ዝንጀሮን ‹‹አታምሪም አታምሪም›› ሲሏት፤ ‹‹ባምር ጠላሁ!›› አለች ይላሉ። አንዳንዴ ሳንፈልግ ቀርተን ሳይሆን በተለያዩ በቂ [አሳማኝ ላይሆኑ ይችላሉ] ምክንያቶች መሆን ያለብንን ሳንሆን እንቀራለን። ተመልካችም ‹‹እንዲህ ማድረግ አለባችሁ! እንዲህ መሆን አለባችሁ!›› ሲል፤ ‹ባምር ጠላሁ አለች ዝንጀሮ› እንላለን። ይህ በዚህ ይቆየንና አንድ ገጠመኜን…

መጻሕፍት – ከብረት አጥሮቹ መካከል

ለአንድ ዓመት ያህል በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ቆይቶ በነጻ የተፈታው ፍቅሩ አማረ (ስሙ የተቀየረ) ከመታሰሩ በፊትም ሆነ በኋላ ከንባብ የለያየው አልነበረም። ይልቁንም በእስር ቆይታው ቤተዘመዱ ጥየቃ ሲሔድ መጻሕፍት ሲወስድለት ደስተኛ ይሆን ነበር። መጻሕፍት ለእርሱ ጓደኞቹ ስለሆኑ። ታድያ በማረሚያ ቤቱ ቤተ…

ጦብያ ግጥምን በጃዝ – ከ100 መድረኮች በኋላ

በየወሩ የመጀመሪያው ረቡዕ ከቀኑ ዐስር ሰዓት ሲቃረብ ጀምሮ ራስ ሆቴል በር ላይ ረዘም ያለ ሰልፍ ማየት የተለመደ ነው። በራስ ሆቴል ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚቀርበውን መሰናዶ መቀመጫ ወንበር ይዞ ከተቻለም ወደፊት ተቀምጦ ለመከታተል ቀድሞ መገኘቱን በቻለ መጠን እውን ያደርጋል፤ ታዳሚ።…

በምን እንግባባ?

‹‹አንድ ሰው ‹እንቢ!› ካለ አልፈልግም፤ ‹እሺ› ካለ እስማማለሁ ማለቱ ነው›› የሚል መሠረታዊ ትምህርት ይሰጥ ይሆን? በምን እንግባባ? ሴቶች በተለያየ አጋጣሚ ከወንድ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የተሰማቸውን መልስ ቢሰጡም ወንዶቹ (ብዙውን ጊዜ) የሚገባቸው በአንጻሩ/በተቃራኒው ነው። የተፈጥሮ ጉዳይ ከሆነ የሚያስረዳኝ ሰው እፈልጋለሁ። ግን አንዲት…

ቴአትር – በብዝኀነት እይታ

የተለያዩ ባህሎች ባሉበት አገር፣ ጥበብ ባለ ብዙ አማራጭና ባለ ብዙ ቀለም መሆኗ አይቀሬ ነው። ይህም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት ከውስጥ እንዲሁም ከውጪ ገቢ ለማግኘት ምቹ አጋጣሚም ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ከምንም በላይ ግን በሕዝቦች መካከል ትውውቅና ትስስር እንዲፈጠር፣ ሰዎች ራሳቸውን የሚያዩበት…

ምላሽ የናፈቀው የብሔር ጥያቄ

የፊታችን ሰኞ፣ ኅዳር 29 የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ታስቦ/ተከብሮ ይውላል። ዋለልኝ መኮንን የብሔር ጥያቄን በይፋ ካነሳም ግማሽ ምዕተ ዓመታት ማስቆጠሩን መነሻ በማድረግ በቅርቡ በሸራተን ሆቴል ውይይት መደረጉ ይታወሰል፤ ምንም እንኳን ከዛ በፊት አንዳንድ የብሔር እንቅስቃሴዎች በተደራጀ መልኩ ይደረጉ እንደነበር ቢነገርም።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com