የእለት ዜና
መዝገብ

Author: ሰላማዊት መንገሻ

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ከመሬት ውስጥ እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ፕሮጀክት ሲሆን፣ የሀይል ማመንጫ ግንባታውን ለማካሄድ መታቀዱን በቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ድርጅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ነዚፍ ጀማል ገልጸዋል። ነዚፍ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ይህንን ግንባታ ለማካሄድ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት…

የኮቪድ-19 ክትባት አንከተብም የሚሉ መምህራን

ወቅቱ አብዛኛው የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የ2014 ትምህርት የሚጀምሩበት ነው፡፡ መምህራን ለማስተማር በሚመጡበት ወቅት መከተብ እንደሚገባቸው በጤና ሚኒስትር አስገዳጅ ሆኖ መመሪያው እንዲተገበር ተደርጓል፡፡ ይህ አስገዳጅ የኮቪድ-19 ክትባት ለመምህራን የሰራ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ክትባቱን ለመውሰድ በርካታ መምህራን ፍላጎት እንደሌላቸውና የግለሰብ መብታችንን…

ኢቢሲ በ20 ሚሊዮን ብር 5 መኪና ለኃላፊዎቹ መግዛቱን አረጋገጠ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ከሠራተኛ ደሞዝ የቆረጥኩት 15 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ለተቋሙ ኃላፊዎች የገዛሁት 5 መኪና በ20 ሚሊዮን ብር ነው ሲል አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ የሕግ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ኃላፊ ሞላልኝ መለሰ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በ12 ወራት ውስጥ የሚቆረጥ የአንድ ወር…

በመስቀል አደባባይ የመጀመሪያው የአውቶሞቲቭ ንግድ ትርዒት ሊዘጋጅ ነው

የትርዒቱ ተሳታፊዎች ለሚጠቀሙበት ቦታ በካሬ ሜትር አንድ ሺሕ ብር ይከፍላሉ ተብሏል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የመጀመሪያውን ግልጽ የሆነ የአውቶሞቲቭ ንግድ ትርዒት ሊያዘጋጅ መሆኑን የምክር ቤቱ ‹የሞተር ሾው ኤቨንት› ከፍተኛ የገበያ ባለሙያ መቅደስ መላኩ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። በንግድ…

የብሔራዊ ባንክ መመሪያ አክስሮናል ሲሉ የሪልስቴት አልሚዎች ቅሬታ አቀረቡ

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በግዥና በሽያጭ ማስተላለፍ መከልከሉ የንግድ እንቅስቃሴያችንን እየጎዳ ኪሳራ ውስጥ ከቶናል ሲሉ የሪል ስቴት አልሚዎች እና የቤት ገዢዎች ቅሬታ አቀረቡ። የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በተለይም ቤትን በግዢና ሽያጭ ማስተላለፍ አለመቻሉ፣ ገዢዎች ለማንኛውም አገልግሎት ቤት መግዛት በሚፈልጉበት ጊዜ የግድ ካርታ በሥማቸው እንዲኖር…

የዴልታ ቫይረስ ወረርሺኝ መስፋፋት

ከኹለት ዓመት በፊት አንድ ብሎ በኢትዮጵያ የመግባቱ ነገር የተሰማው ኮቪድ 19 ወረርሺኝ፣ ከ340 ሺሕ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። በመካከል ቀንሶ የነበረው የሞት መጠንም አሁን ሦስተኛ በተባለው የወረርሺኙ ማዕበል ከ40 እያለፈ ሲሆን፣ በትንሽ በትንሹ እየጨመረ እንደ ዋዛ ከአምስት ሺሕ በላይ ሰዎች ሕይወት…

‹‹የአገር ዐቀፍ የካርታ መረጃ ለኹሉም ተቋማት ግዴታ ነው››

ቴዎድሮስ ካሳሁን በኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንሰቲትዩት የካርታ ሥራ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ካሳሁን ይባላሉ። በቀድሞው የካርታ ሥራዎች ድርጅት፣ በአሁኑ የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንሰቲትዩት ውስጥ የካርታ ሥራ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ናቸው። ከስድስት ዓመት በፊት ተቋሙን የተቀላቀሉት ቴዎድሮስ፣ ከዛ በፊት ለሦስት ዓመት የመጀመሪያ ደረጃ…

የኢሬቻ በዓል ሌላው ገጽታ

ኢሬቻ የምስጋና ቀን ነው። ይህ በዓል በኹለት ቦታዎች እንደሚከበር ስርዓቱን የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። የሚከበርባቸው ቦታዎቹም በሐይቆችና ወንዞች እንዲሁም በተራራዎች ላይ ነው። አንደኛው በክረምቱ መግቢያ ወቅት ላይ ሲሆን፣ ክረምቱን በሰላም አሻግረን፣ ውኃ እና እርጥቡን አትንሳን ተብሎ ፈጣሪን የሚለማመኑበት፣ በተራሮች አናት ላይ…

የአገር ውስጥ ዘይት አምራቾች ለአስመጪዎች ቀረጥ መነሳቱ ችግር ሆኖብናል አሉ

ከውጭ በሚገባ የምግብ ዘይት ላይ ማንኛውም ቀረጥና ታክስ በመነሳቱ በገበያው ለመወዳደር አስቸጋሪ ሆኖብናል ሲሉ የኢትዮጵያ ምግብ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አዲሴ ጋርካቦ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ነሐሴ 28/2013 ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ የምግብ ዘይት ምርት…

በነሐሴ ወር ለሕዳሴ ግድብ የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት በ55 ሚሊዮን ብር መቀነሱ ተገለጸ

ከፍተኛ ገቢ የተገኘው ከዳያስፖራው ነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በነሐሴ 2013 በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች የተሰበሰበው ብር ካለፈው 2012 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ55 ሚሊዮን ብር መቀነሱ ተገለጸ። በነሐሴ 2013 በአጠቃላይ 96.7 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት…

ፒያሳ ለሚገኙ የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ዕድሳትም ሆነ ምዝገባ ተከለከለ

በአራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ፒያሳ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለሚገኙ የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ዕድሳትም ሆነ አዲስ ምዝገባ መከልከሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አከበረኝ ወጋገን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በአካባቢው የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን…

የሸገር ባስ ትራንስፖርት ድርጅት የክሬን አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የሸገር ባስ ትራንስፖርት ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልል ከተሞች ተደራሽ የሚሆን የክሬን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለጸ። ድርጅቱ ከሚሰጠው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ፣ በመዲናዋ አዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚያጋጥሙ የመኪና ብልሽቶች አገልግሎት መስጠት የሚችል የመኪና ማንሻ ወይም የክሬን አገልግሎት…

ብልጽግና ፓርቲ ብቻውን የሚወዳደርበት የሱማሌ ክልል ምርጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ሰኔ 14/2013 ያስፈጸመ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተነሳ ሰኔ ላይ ምርጫ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ኹለተኛወ ዙር ምርጫ ለመስከረም 20/2014 ቀጠሮ ተይዞለታል። በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሙሉ በሙሉ ካልተካታቱ ክልሎች መካከል የሱማሌ ክልል አንዱ ሲሆን፣…

የመስቀል በዓል እና የቱሪስት ፍሰት

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ በጣም አስደሳች ከሆኑት አውደ ዓመቶች አንዱ ነው። በዓሉ በርካታ ችቦዎች በአንድ ላይ ተደምረው የሚበሩበት በዓል ነው። የመስቀል በዓል የተለያዩ የባህር ማዶ ጎብኚዎች መጥተው የሚጎበኙት ከበርካታ የአገሪቱ የማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም የተለየ የቀን መቁጠሪያ ያላት…

እየጨመረ የመጣው የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ወላጆችን አስመርሯል

ደምሴ አብዲሳ (ስማቸው የተቀየረ) በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው። ደምሴ የኹለት ልጆች አባት ናቸው። ባለቤታቸውን በሞት ከተነጠቁ በኋላ ልጆቻቸውን የማሳደግ ኃላፊነት የእርሳቸው ሆኗል። ልጆቹ በሥነ-ምግባር እና በዕውቀት ልቀው እንዲገኙ የሚፈልጉት ደምሴ፣ ከፍተኛ የትምህርት ክፍያ በመክፈል ቅዱስ…

የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የወደብ ላይ ግብይት ለማሳለጥ የጋራ ማዕከል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ሞያሌ ወደብ ላይ በኬኒያ እና በኢትዮጵያ ድንበር መካከል በሚደረገው ግብይት የምንዛሬ ልዩነት በመኖሩ ምክንያት በዶላር መገበያየት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም የጋራ ድንበር አገልግሎት ማዕከል መጀመር አለበት ተብሏል። የኬንያ አጓጓዦች ማኅበር ጸኃፊ ሜርሲ ኢሪሪ መስከረም 15 ቀን የኬንያ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ…

በ25 ሚሊዮን ብር 5 መኪና ለኃላፊዎቹ የገዛው ኢቢሲ ከሠራተኞቹ 40 ሚሊዮን ብር ቆረጠ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደሞዝ መለገስ ግዴታችሁ ነው መባላቸው ቅሬታን አስነስቷል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት ከሆነ የዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮችን ባላገናዘበ መልኩ የአንድ ወር ደሞዝ ሊወሰድ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። “የኛን የደሀዎቹን ደሞዝ ከሚወስዱ ለአመራሮች…

የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ ሊመዘገብ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ መዘጋጀቱን አስታወቀ። በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ናቃቸው ብርሌው እንደተናገሩት፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በአገራችን ካሉ ትላልቅ ፓርኮች በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገና በርካታ ብዝኃ ሕይወት ያለበት በመሆኑ በዩኔስኮ ለማስመዘገብ…

ኹለት አዳዲስ የብረታብረት አምራች ድርጅቶች ወደ ገበያ መግባታቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ

የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ኹለት አዳዲስ የብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ገበያ መግባታቸውን አስታወቀ። ኢትዮጵያዊ የሆኑት ኹለቱ ግዙፍ ተቋማት የመሠረታዊ ብረታብረትና የመኪና መለዋወጫ ምርት ማምረት የሚያስችሉ መሆናቸውን በኢንስትቲዩቱ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ፌጤ በቀለ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የኢንቨስትመንት ዘርፉን የተቀላቀሉት…

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ለምዝገባ 600 ብር መከፈላቸው ቅሬታ አስነሳ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማስተር እና ፒኤችዲ ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች ለምዝገባ የሚከፍሉት 600 ብር ከመጠን በላይ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። ቅሬታችን ክፍያ ብቻ አይደለም የሚሉት ፈተናውን የወሰዱት ጌትነት ታደሰ፣ የፈተና ውጤት አሠራሩ ትክክል አይደለም ብለዋል። የአንድ ሰው የማስተር ማለፊያ ነጥብ 30…

ኮሚሽኑ በተለያዩ ከተሞች ያገኛቸውን 200 ቶን ኬሚካሎች ሊያስወግድ ነው

የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በ739 ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ የሕግ ተከባሪነት ክትትል እና ቁጥጥር ካደረገ በኋላ 200 ቶን ኬሚካል ሊየስወግድ መሆኑ ተገለጸ። አዲስ ማለዳ ከኮሚሽኑ ያገኘችው መረጃ እንደሚያሳየው በአገር ውሰጥ የሚመረትን እና ከውጪ የሚገባውን ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ኬሚካል…

አዲስ ዓመት እና የበዓል ገበያ

ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ወራትና ቀናትን ቀንንና ወርን እየወለዱ አዲስ ዓመት ገብተናል። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዘመን መለወጫ መስከረም አንድ ይከብራል። ይህ መስከረም አንድ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ ሥያሜ ያለው ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ዘመነ ማትዮስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ተብለው…

ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረጋቸው መመሪያዎች ለባንኮች ሥጋት መሆናቸው ተገለጸ

ብሔራዊ ባንክ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ካደረጋቸው አራት መመሪዎች ውስጥ አብዛኞቹ ባንኮች ጋር ያለውን ተቀማጭ የገንዘብ እና የዶላር መጠን ወደ መንግሥት የሚያስገቡ ናቸው ሲሉ የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር እየሱስወርቅ ዛፉ ገለጹ። በመመሪያው መሠረት የአገልግሎት እና የዕቃ አስመጪዎች ይዘውት ከሚመጡት የዶላር…

ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስትቲዩት “ላይዳር” የተባለ አዲስ ቴክኖሎጂ በ80 ሚሊዮን ብር ገዛ

የቀድሞው የካርታ ሥራዎች ድርጅት የአሁኑ የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንሰትቲዩት በ80 ሚሊዮን ብር አዲስ ቴክኖሎጂ በመግዛት ወደ ሥራ ሊያገባው መሆኑን አስታወቀ። የኢንስትቲዩቱ የጂኦስፓሻልና ኢኖቬሽን አናሊስቲክ ማዕከል ኃላፊ ሙሉአለም የሺጥላ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ኢንስትቱዩቱ “ላይዳር” የተባለ አዲስ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂን በመግዛት ወደ ሥራ…

የኮቪድ ክትባት በኢትዮጵያ

ክትባት በሽታን የማስቀረት የቅድመ መከላከል ተግባር ያለው ሲሆን፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከገባ በኋላ ክትባቶቹን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ነበር። ክትባቶቹ ከተገኙ በኋላም ሰዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የሚመለከታቸው ተቋማት እንደ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንና የዓለም የጤና ድርጅት ፈቃድ መስጠት አለባቸው የሚሉት…

የደሴ ከተማ አስተዳደር ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ መቸገሩን ገለጸ

ወደ ከተማው በቀን እስከ ኹለት መቶ የሚደርሱ ተፈናቃዮች ይገባሉ ከአዲስ አበባ በ400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ደሴ ከተማ የሚገቡ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰብዓዊ ድጋፎች ለማድረግ ተችግሬያለሁ ሲል የከተማው አስተዳደር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። የደሴ ከተማ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ…

የተሻሻለው የታሪፍ ደንብ የጦር መሣሪያዎችን በነጻ ማስገባት የሚፈቅድ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ የተሻሻለው የታሪፍ ደንብ የወታደራዊ (ሚሊተሪ) ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ማለትም እንደ ጠመንጃ፣ ሮኬት፣ ላውንቸር እና እሳት የሚተፉ መሣሪያዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የሚፈቅድ መሆኑ ተገለጸ። የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የሕዝብ ደሕንነት ተቋሞች ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያና የሕዝብ…

በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጹ

በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የመቐለ፣ አክሱም፣ የዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርስቲ መምህራን ከኹለት እስከ ሦስት ወር ደሞዝ ባለመከፈላቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጹ። በአራቱ ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩት መምህራን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ የደሞዝ ክፍያው የተዛባው ከጥቅምት 2013 ጀምሮ…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ40 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶች ሊሠራ መሆኑን ገለጸ

በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የውኃ፣ የሶላር፣ የንፋስና የጂኦተርማል ማመንጫዎችን በ40 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት መታቀዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬሽን ፕላኒንግ ሥራ አስፈጻሚ አንዱአለም ሲዓ ገልጸዋል። እነዚህ አዳዲስ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች የኮይሻ እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማሟላት ያልቻሉትን ኃይል ለማሟላት…

የጀማሪ የቢዝነስ ሐሳቦችን የሚመራ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ

የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር የጀማሪ ቢዝነስ ሐሳቦችን የሚመራ አዋጅ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዲኤታ አህመድ መሐመድ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ይህ አዋጅ የጀማሪ ቢዝነስ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ ነው ብለዋል። በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተወያይተውበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ…

error: Content is protected !!