የእለት ዜና
መዝገብ

Category: የአክንባሎ ጋጣ

“እኔን ይወክለኛል”

በማኅበራዊ ኑሮ የተፈጠረውን የማዕረግ ተዋረድ ወንዶችን ከበላይ ሴቶችን ከታች አስቀምጧል። ይህም በዘመናት ሒደት የተገነባው የተዋረድ ስርዓት ከላይ ላለው ያለድካም ሲያደላ፤ ከታች ላስቀመጠው በአንጻሩ የሚነፍግ፤ በጥቅሉ የተዛባ የኃይል ሚዛን ፈጥሯል። ‹‹እኔን ይወክለኛል›› የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፣ በራስ ጥረት ሳይሆን በማዕረግ ተዋረዱ ተጠቃሚ…

“እኔን አይወክለኝም”

ውክልና ከማኅበረሰቡ አካል ሆኖ በመውጣት የሚገኝ አይደለም የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፤ የውክልና አረዳዳችን ትክክለኛም ሆነ አግባብ እንዳልሆነ ያነሳሉ። በዚህም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የተባሉና የሆኑ ክስተቶችን እንደማሳያ አስቀምጠው፤ የውክልና ነገር በፖለቲካው እንዲሁም በማኅበራዊ ኑሮ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ያብራራሉ። አንድ ድርጊት አድራጊውን ብቻ…

የብዙኀን አምባገነንነት በሥመ ፌዴራሊዝም

በግርድፉ ሙገሳና ትችት የሚነሳበት የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም፣ ስላስመዘገበው ጠንካራና ደካማ ጎን ብዙ አልተወራለትም። ስርዓቱ መፍትሔ ያመጣለታል የተባለውን የኢትዮጵያን ችግር በተለየ አቀራረብ መልሶ እንዳመጣ የሚጠቅሱት በፍቃዱ ኃይሉ፤ ያደረገው አስተዋጽኦ ቢኖርም የተለያዩ ግጭቶች እንዲነሱ መንስዔ ሆኗልም ይላሉ። የቡድን መብቶችም አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ቡድኖች…

ግጭት አስወጋጅ ዘጋቢነት

በፍቃዱ ኃይሉ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ኹኔታ ታሳቢ አድርገው እና ሮስ ሀዋርድ የፃፉት ‘ግጭት አስወጋጅ አዘጋገብ መመሪያ’ የሚል ጽሑፍ ተንተርሰው ፥ የግጭት አስወጋጅ ዘገባ ምንነትን እንዲሁም በዘገባ ወቅት መደረግ ስላለባቸው እና ስለሌለባቸው መሰረታዊ ነጥቦችን ዘርዝረው አብራርተዋል።   “ለዘጋቢዎች ለውጥ ዜና ነው። እናም…

ነጻነትም፣ ስርዓትም ማጣት!

ሁሉም ሰው የራሱን ጥቅም ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ግጭት እንዳይፈጥር በነጻነትና በስርዓት መካከል እርቅና ሚዛን ያስፈልጋል የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፣ በአብዛኛው ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም ሰብኣዊ ነጻነትን ከተገቢው ስርዓት ጋር ሚዛን አስጠብቀው መዝለቅ የቻሉት ናቸው ይላሉ። ይሁንና ይህንን የነጻነት እና ስርዓትን ሚዛን ጠብቆ የሚጓዝ…

የኹለት ሰልፎች ወግ!

በለንደን ከተማ በነበራቸው ቆይታ የተመለከቱትን ሰልፍ በማንሳት የሚጀምሩት በፍቃዱ ኃይሉ፥ ሰልፉን በተመሳሳይ ሰሞን ጥቅምት 2 ቀን 2012 በአዲስ አበባ ይካሔዳል ተብሎ ሲጠበቅ አንድ ቀን በማይሞላ የሰዓት ልዩነት እንደማይደረግ ከተገለጸው ሰልፍ ጋር አነጻጽረው ያሳያሉ። በኹለቱ ሰልፎች መካከል በሰልፉ ጠሪዎች እንዲሁም በመንግሥትና…

ድኅረ እውነት

የድኅረ እውነትን ምንነት በመበየን የሚንደረደሩት በፍቃዱ ኃይሉ፥ ተጨባጭ ነው ያሉትን አንድ ድርጊት እንደ አብነት በመጥቀስ ሰዎች በጥሬ ሐቅ ላይ ተመስርተው ሳይሆን የሰሙት ነገር የፈጠረባቸውን ስሜት ተከትለው ይወስናሉ ይላሉ። የዚህ መዘዙ አገር እስከማፍረስ ይደርሳል በማለት የሚያስጠነቅቁት በፍቃዱ፥ መፍትሔው በዋነኛነት የመንግሥት ግልጽነት…

“የተዋልደናል” ትርክት አሳሳችነት…

በፍቃዱ ኃይሉ የኢትዮጵያን አንድነት አስፈላጊነት ለማስረዳት በተለይ የፖለቲካ ልኂቃን “ተዋልደናል” የሚለውን ትርክት በማጠየቅ ለመላው ኢትዮጵያ ይሠራል ብሎ ማሰብ ችግር አለበት በማለት መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። በርግጥ እንደሚታሰበው “የዘር ጥራት” አለ ማለት እንዳልሆነ በመጥቀስ “የዘር ጥራት” የሚባለው አስተሳሰብ በራሱ ዘረኝነት እንደሆነ የጠቆሙት በፍቃዱ፥…

ቱሪዝም፡ “በእጅ ያለ ወርቅ…”

አዲስ ዓመት በመስከረም ወር እነሆኝ ብሎ ብቅ ከማለቱ እንደወትሮው ሁሉ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ክብረ በዓላት በአጀብ ተቀብለውታል። ዛሬ፣ መስከረም 17 በመላው ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና…

የታሪክ እስረኞች

ታሪክን እንደታሪክ ለታሪክ ጸሐፊዎች ብቻ መተው መቻል አለብን የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፥ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተጫኗቸው ታሪክ አጻጻፎች ስለሚበዙ እውነቱ ላይ መድረስ አስቸጋሪ ነው በማለት ተጨባጭ ያሏቸውን ማሳያዎች ጠቅሰዋል። የወደፊት ዕጣ ፈንታችንን ለመወሰን ባለፈው ታሪካችን ላይ የግድ መስማማት አይጠበቅብንም ሲሉ መፍትሔ…

ማዕከላዊን እንደ ቱሪስት

ከዓመታት በፊት ሦስት ወራትን ሊደፍኑ ስድስት ቀናት እስከቀራቸው ድረስ በማዕከላዊ እስር ቤት በስቅየት ያሳለፉት በፍቃዱ ኃይሉ፣ ጳጉሜን 6 የተከበረውን የፍትሕ ቀን ምክንያት በማድረግ ከጳግሜን 1 እስከ 6 ለጎብኚዎች ክፍት የተደረገውን ማዕከላዊ እስር ቤት ድሮና ዘንድሮ ያስቃኙናል።   ያ በሥም የሚያስፈራራውን፣…

የፈሪ ትግል

ባሕላችን፣ ትውልዶችን ጭካኔ እያስተማረ በማሳደግ ላይ የተመሠረተ ነው የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፥ ተጨባጭ ያሏቸውን ማሳያዎች በማስረጃነት አቅርበዋል። ዴሞክራሲን ለመኖር ጭካኔን የሚቃወሙ፣ ጭካኔያዊ ጀብደኝነትን የሚሸሹ፣ ተደራድረው የሚያድሩ ትውልዶችን ኮትኩቶ ማሳደግ ይገባል ሲሉ ምክረ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል።   አንዲት ቬጋን ጓደኛዬን ለምን ቬጋን (አትክልት…

የማኅበራዊ ሚዲያ ምፅዓት

የማኅበራዊ ሚዲያን አደገኛ ጎን ለመቀነስ ኹነኛው መፍትሔ ማገድ አይደለም የሚሉት በፍቃዱ ኃይሉ፥ በዚህ የመረጃ ዘመን ዴሞክራቶችና አሪስቶክራቶች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ አተያይን ተመሳሳይነት እና ተቃርኖ ቃኝተውታል።     ምሁራን አሁን ያለንበትን ዘመን ‘የመረጃ ዘመን’ ይሉታል። ይሁንና የመረጃ ፍሰቱ ፍጥነት መንግሥታትም ይሁኑ…

“ሁሉም ከዘመዱ ሲባል፥ አክንባሎ ጋጣ ገባ”

“የአክንባሎ ጋጣ” ብዬ የምጠራው አምድ ላይ ብዕሬን የማሾለው ለትችት ሲሆን ነው፤ መወድሰ መንግሥት፣ መወድሰ እምነት፣ መወድሰ ባሕል፣ መወድሰ ወግ እና ወዘተ. መሥማት የሚፈልጉ ሰዎች ላይመርጡት ይችላሉ። ለፍትሐዊ እና ርትዓዊ የእርስ በርስ ግንኙትነት የራስን ምቾት አሳልፎ እስከ መስጠት ለቆረጡት ግን እንደሚመቻቸው…

error: Content is protected !!