መዝገብ

Category: ሕይወትና ጥበብ

አውታር ያመጣው ለውጥ?

እጅግ ፈታኝ ከሚባሉ እና የሙዚቃው ኢንደስትሪ እንዳያድግ እንቅፋት ሆኗል – ስርቆት ። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሆነም 80 በመቶ የሚሆኑ የሙዚቃ ስራዎች በሕገወጥ ነጋዴዎች ይቸበቻበሉ። ታዲያ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ጥቁት የሚባሉ አርቲስቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዲሁም ኢንርኔትን በመጠቀም የሚሰራ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን )…

ኮቪድ 19 እና የፎቶግራፍ ጥበብ

የተወለደው አዲስ አበባ ካሳንችስ አካባቢ ነው። ከጅማ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ድግሪው ማግኘት ችሏል። በአሁን ወቅት ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ኹለተኛ ድግሪው ለማግኘት በመማር ላይ ይገኛል። ባሳለፈውነ ሳምንት ደግሞ ማስተር ካርድ ፋውዴሽን ከቦቢ ፓውል ፎቶግራፊ ባዘጋጀው ‹አፍሪካን ኢን ኮንቴክስት› ተብሎ በተሰየመው የፎቶግራፍ…

ስጦታ – በገና በዓል

ከወደ ምሥራቅ አገር በኮከብ ብርሃን ተመርተው የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ ምክንያት በማድረግ ወደ ቤተልሔም መጡ – የጥበብ ሰዎች፤ ሰብአ ሰገል። ወርቅ፣ እጣን እና ከርቤም አምጥተው ስጦታ አበረከቱለት። ሰብአ ሰገል እነማን ናቸው ከተባለ ከሥማቸው ትርጓሜ አንስቶ የጥበብ ሰዎች ይባላሉ። ጠቢባን እንደሆኑና ጠብቢነታቸውም…

የባሕል አምባሳደሩ የፈንድቃ ሽልማት አንድምታ

መላኩ በላይ የፈንድቃ ባህል ማዕከል መሥራችነው፡፤ በሙያው ተወዛዋዥ ሲሆን ከሦስት ሳምንታት በፊት የዘንድሮውን የኔዘርላዱን የፕሪንስ ክላውስ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል። ከዓለማችን 84 አገራት መካከል ተወዳደርረው ሰባት አገራት ብቻ ሽልማቱን ባገኙበት መድረክ፤ በባህል ዘርፍ መልካም ሥራ ሠርታችዃል ተብለሎ ፈንድቃ የባህል ማዕከል መሸለም…

‹‹ምን ለብሳ ነበር?››

ሴትነት ጥበብ ነው! የፈጣሪ ፍጥረትን እንደ ምድር አሸዋ የሚያበዛበት ልዩ ጥበብ። የሰው ልጅም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ፤ እስከ አሁኗ ሰዓት እና ደቂቃ ድረስ በዚሁ የሴትነት ጥበብ ውስጥ ከትውልድ ትውልድ እየተቀጣጠለ ይኖራል። ይህን ጥበብ ታዲያ የዓለማችንም ሆነ የአገራችን ሕዝብ ምን ያህል ተረድቶታል?…

ዝክረ ተስፋዬ ገሠሠ

ታላቁ የጥበብ ሠው ተስፋዬ ገሠሠ የተወለዱት መስከረም 17/1929 በኢትዮጵያ የምሥራቁ ክፍል፣ ሐረር ልዩ ሥሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ ነበር። ተስፋዬ ለወላጆቻቸው ብቸኛ ልጅ የነበሩ ሲሆን እንዳለመታደል ሆኖ ገና የኹለት ዓመት ከስምንት ወር ሕጻን ልጅ እያሉ ነበር እናት እና አባታቸውን በሞት…

ሕይወት እና ጓደኝነት

‹ጓደኝነት ሕሊና ቢወረስ በክፉ ትዝታ፤ ልቦና እየሻረው በጣፋጭ ትውስታ፤ በአብሮነት ጎዳና ገስግሶ ሚያነግሠው፤ መሆኑ ብቻ ነው ጓደኛ ጓደ’ኛ ሰው፤ ጊዜ እያፈለቀ የመቻቻል ወኔ፤ ለመልካም ተግባርህ ለደካማው ጎኔ፤ በጥሩ ቀን ሞገድ፤ አግባብቶን አላምዶ፤ ላያለያየን ነው፤ ያገናኘን ፈቅዶ። አንዴ ጥፋተኝነት አንዴም ደግሞ…

የሞተውን የንባብ ባህል ዳግም ለማንሳት…

አንጋፋው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ የተማረው እስከ አራተኛ ክፍል ይሁን እንጂ እራሱን በንባብ አዳብሮ በአገራችን አሉ ከሚባሉ ቁጥር አንድ ጋዜጠኛ፣ ጸሐፊያን እና አዋቂዎች መካከል አንዱ ሊባል የቻለው ሚስጥሩ በማንበቡ እንደሆነ ይመሰከርለታል። በንባብ ራሳቸውን አንጋፋ ካስባሉ ሰዎች መካከል ሌላኛዋ ተጠቃሽ ደግሞ ሔለን…

ብሔራዊ ቴአትር በዘመናት ውስጥ

ኪነ ጥበብ የአገርን እድገት ለማፋጠን ብሎም የአገርን ችግር ለይቶ በማሳየት እንዲቀረፍ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚናን ከሚጫወቱ ዘርፎች ውስጥ አንዱ ነው። በኪነ ጥበብ የአንድ አገር ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊና ፖለቲካዊ እሴቶች በስፋት ይዳሰሳሉ። የአገራችን የኪነ ጥበብ ታሪክም እረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ…

ኅዳር ሲታጠን

የኀዳር ወር በገባ በ12ተኛው ቀን ዛሬም ድረስ ያልጠፋ እንደ ባህልም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ ባህል አለ ፤ ቆሻሻ ማቃጠል። በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬም ድረስ ኀዳር 12 ቀን ሲመጣ እንደ ከዚህ ቀደሙ ባይሆንም አሁንም ድረስ ቆሻሻዎች ሰብስቦ የማቃጠል ተግባር እየተመለክትንም…

የምሽት መዝናኛ ቤቶች መነቃቃት ከኮቪድ 19 ማግስት

አዲስ አበባ ካዛንችስ አካባቢ ከሚገኙ የምሽት ቤቶች ውስጥ በአንዱ ተገኝቻለሁ። በቤቱ ውስጥ ያሉ አገልጋይም ሆነ ተገልጋዮች ቁጥራቸው ከፍተኛ በመሆኑ፤ በእዛች የበሬ ምላስ በምታክልና የተፋፈነች ጠባብ ቤት ውስጥ የኮሮና ወረርሽኝ ጉዳይ ፈፅሞ የተረሳና ማንም ቁም ነገሬ የሚለው ጉዳይ ላለመሆኑን ምስክር ነው።…

ኮቪድ 19 የቀየረው የሠርግ ሥነ ሥርዓት

ፎቶ ግራፍ የኋለኛ ታሪክ በምስል አስድግፎ የወቅቱን ሁኔታ የማሳየት አቅም እንዳለው እሙን ነው ።በተለይም የኋላ ዘመን የነበረውን ታሪክ፣ ባሕል፣ ወግ፣ በወቅቱ የነበረው ሁኔታም ወደ ኋላ መለስ ብሎ የማሳየት ትልቅ ጉልበትም አለው።ታሪክን ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላፍም ባሻገር የዘመናትን የኪነጥበብ ህንጻ ጥበብ…

ለማ ጉያ፤ የለማዊነት ማሳያ ከ1921-2013

ሥዕል ቀደምት ታሪካዊ መነሾ ያለው የሥነ-ጥበብ ዘርፍ ነው። የሰው ልጅ ከጥንት ዘመን አንስቶ እንደመግባቢያናነትና ስሜቱን መግለጫነት ይጠቀመበት እንደነበርም ቀደምት ድርሳናትና የታሪክ ልሂቃን ያስረዳሉ። የአገራችን የሥነ-ሥዕል ታሪክም እረጅም ዘመንን ያስቆጠረ ሲሆን በሥዕል ሥራዎቻቸውም በአገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትንና…

የጥቅምት ወር ትሩፋቶች

አገራችን አትዮጵያ በአለም ላይ ብቸኛዋ የአስራ ሦስት ወር ፀጋ ባለቤት አገር መሆንዋ ይታወቃል። እነዚህም ከመስከረም እስከ ጷግሜ ያሉት አስራ ሦስቱ ወራት ታዲያ የመጠሪያ ስማቸውን በየወራቱ ካለው የአየር ሁኔታና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የተሰጣቸው ሲሆን፤ ወራቱንም አስመልክቶ በጥንት ሊቃውንቶች ዘንድ የተነገሩ፤…

የኢትዮጵያ ሲኒማ በኮቪድ ማግስት

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለማችንም ብሎም በአገራችን ላይ እያደረሰ የሚገኘው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ጫና ይህ ነው የሚባል አይደለም። በወረርሽኙ ሳቢያ ብዙኀኑ የዓለማችን አገራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ መንግሥታዊም ሆነ የግል አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ዘግተው መክረማቸውም የሚታወቅ ነው። ሰዎች ሕዝብ ከሚበዛባቸው ስፍራዎች…

ጥቅምት 2 እና የአድዋ ጉዞ

ይህ መስከረም 17 ቀን 1888 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያ በመውረር በቀኝ ግዛቱ ስር ለማዋል ማሰቡን በማረጋገጣቸው፤ በጣሊያን የወረራ ዝግጅት በመቆጣት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጦርነት እንዲዘጋጅ ያሳሰቡበት የክተት አዋጅ ነው። አዋጁም ንጉሠ ነገሥቱ በሚመሩትና በሚያስተዳድሩት የሸዋ ጠቅላይ…

የደራሲው ዕይታዎች – ከ‹ሰባት ቁጥር› መጽሐፍ ባሻገር

አሜሪካዊው ደራሲና የተውኔት ጸሐፊ ሬይ ብራድበሪ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹የአንድ አገር ባህል ለማጥፋት መጻሕፍትን ማቃጠል አይጠበቅም። ሰዎች እንዳያነቡ ማድረግ ብቻ ነው።›› መጻሕፍት የእውቀት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የማንነትና መሰል አገር የሚያክል መረጃ ተሸካሚዎች ናቸው። በአገራችንም ምንም እንኳ የንባብ ባህሉ የሚታማ ቢሆንም፣ የተሰጣቸውን መክሊት…

የመስቀል በዓል አከባበር – በዘመናት መካከል

በኢትዮጵያ በባህል፣ በሀይማኖት ወይንም በሕግ ተደንግገው፤ የሚታወሱበት ቀን እና ጊዜ ተሰጥቷቸው የሚከበሩ የአደባባይ የአንድነት በዓላት ይገኛሉ። ከእነዚህ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ የአንድነት የአደባባይ በዓላት መካከል ደግሞ በወርሃ መስከረም የእንቁጣጣሽ በዓልን ተከትሎ በመስከረም 17 ተከብሮ የሚውለው የመስቀል በዓል አንዱ ነው። በመላው ኢትዮጵያም…

የኢሬቻ በዓል ገጽታዎች

በርከት ካሉ ሺሕ ዓመት በፊት እንደሆነ የሚነገርለት አንድ አፈ ታሪክ አለ። እንዲህ ነው፤ አቴቴ ኹለት ወንድሞች ነበሯት። እነዚህ ወንድሞቿ በመካከላቸው ጸብ ይፈጠርና ይጣላሉ። አንዱም አንደኛውን ገድሎ ይጠፋል። አቴቴ ታድያ በእጅጉ ታዝናለች፤ ሟች ወንድሟ በተቀበረበት ቦታ ላይም ኦዳ ትተክላለች። ኦዳውን እየተንከባከበች…

2012 በጥበብ ዘርፎች ዕይታ

ቀን ቀንን እንደሚያድስ፣ በተመሳሳይ ሰማይና ፀሐይ ነገር ግን ሌሊትን በተሻገረ ቁጥር አዲስ ቀን እንደሚገኝ፣ አዲስ ዓመትም እነሆ መጥቷል። ከ365 ቀናት በፊት አዲስ የነበረውና በወረት የተቀበልነው 2012 አሁን አሮጌ ተብሏል። ክፉውም ደጉም አልፎበት፣ መሠረት ግን ሆኖ፣ በሌላ ተስፋ፣ በሌላ ስጋት 2013…

በዓል እና የመገናኛ ብዙኃን መሰናዶዎች

ኢትዮጵያዊያን ለበዓል ቀናት ያለን ስሜት ልዩ ነው። በተቻለን አቅም ሁሉ እለቱን በልዩ ስሜት፣ ደስታ እና በምቾት ማሳለፍ እንፈልጋለን። የዘወትር እንቅስቃሴዎችም ለበዓል እረፍት ስለሚወስዱ፣ እኛነታችን በሚያጎሉ ወግና ባህልን መሠረት ባደረጉ ስነ ስርዓቶች ታጅበን በዓላትን ከቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ ጎረቤት ጋር ሰብሰብ ብለን…

ኑሮ እና ደም-ወዝ

ሰጥቶ የመቀበል ቀመርን ዋነኛ መርህ ባደረገች በምንኖርባት ዓለም፤ የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ እልፍ አእላፍ የሕይወት ውጣ ውረዶችን ያሳልፋል። እነዚህን የሕይወቱን ውጣ ውረዶች በማቅለል ብሎም ኑሮውን የተደላደለና ምቹ ከማድረግ አንፃር ገንዘብ የሚጫወተው ሚና ይህ ነው የሚባል…

አሸንዳና ማህበራዊ ቱሩፋቶቹ

አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህላዊ ክውን ጥበባት እና ሀይማኖታዊ ስርዓቶች ባለቤት ናት። ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትርጓሜን ይዘው በድምቀት የሚከበሩ በዓላትም አሏት። እነዚህ ክዋኔዎችም በተለያየ ወቅት እና ጊዜ የሚከናወኑ ሲሆኑ በተለይ በክረምት ወራት የሚከናወኑት አሮጌው ዓመት አልፎ በአዲሱ ሊተካ የቀናቶች እድሜ መቅረቱን፤…

ቡሄ እና ባህሉ

‹‹መጣና በዓመቱ ኧረ እንደምን ሰነበቱ ቡሄ መጣ በዓመቱ ኧረ እንደምን ሰነበቱ ሆያ…. ሆዬ….!ሆ….! እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል አጋፋሪ ይደግሳል፤ ያቺን ድግስ ውጬ ውጬ ከድንክ አልጋ ተገልብጬ፤ ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ ያለ አንድ ሰው አታስተኛ፤ ሆይሻ…. ሎሚሻ መጣንልሻ፤…›› እነዚህን ስንኞች በልጆች…

የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በኢትዮጵያ

መረጃ የታሪክ የጀርባ አጥንት ነው። ይህም የሚባለው ያለምክንያት አይደለም። ታሪክን በመረጃ ቋት ውስጥ በየዘመን እና ጊዜው እየከፋፈለ ሰድሮ የትናንቱን እውነት ከዛሬው ኩነት ጋር በማጋመድ ለቀጣዩ ትውልድ የማቆየት ልዩ አቅም ስላለው ነው። የሰው ልጅ ሕይወቱን በተቃናና በቀለለ መንገድ ይመራ ዘንድ፤ በሚያደርገው…

አረፋ እንደምን አለፈ?

በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩና ልዩ ስፍራ ከሚሰጣቸው ዓመታዊ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ እና ዋነኛው ነው። ፆም፣ ጸሎትና መልካም ሥራን የሚያሳዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የሚከወኑበት ይህ በዓል የመታዘዝ፣ የመስዋዕት እና የእዝነት በዓል ተደርጎ በእምነቱ ተከታዮች…

ኮቪድ 19 እና የኪነ-ጥበብ ምሽቶቻችን

በሰው ልጅ የእለት ተእለት የሕይወት መስተጋብርና ውጣውረዱ ውስጥ ልማትና ጥፋቱን፣ ሰናይና እኩይ ሀሳቡን፣ ተግባሩንም ሳቢና ማራኪ በሆነ መንገድ መልሶ ለሰው ይቀርብበታል፣ ኪነጥበብ። በዚህም ምክንያት ክስተትን፣ ኹነትን፣ ታሪክንም ጭምር በማይጠፋ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ የማስቀረት አቅም ካላቸው ዘርፎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ሆኗል።…

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት – ከ‹ነበር› እስከ ‹ነው›

ወደ ዊንጌት በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ይገኛል፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት። ብዙዎች ‹ፓስተር› በሚል ሥም ይጠሩታል። ለዚህም ምክንያት አላቸው። ይህንንም ምክንያት በኢንስቲትዩቱ የ‹ነበር› አምድ ላይ እንዲህ ተጽፎ እናገኛለን። ከታሪክ ማኅደር በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1914 ነበር የተለያዩ የኅብረተሰብ እና የእንስሳት ጤና…

ተወርዋሪ ኮከብ -ጋዜጠኛ ካሳሁን አሰፋ

ተወርዋሪ ኮከብ ይሏቸዋል፣ ድንገት ታይተው፣ አብርተውና አድምቀው፣ ደምቀውም በቅጽብት ጥፍት የሚሉትን። ብዙ የሚጠበቅባቸውና ብዙ እንደሚሰጡ ተስፋ የታየባቸው፣ የሚያሳሱ፣ ተፈጥሮንና ፈጣሪን የምናመሰግንባቸው፣ ሙያንና ሙያተኛን የምናከብርባቸው በብዙ መልኩ ሊገለጹ የሚችሉ ሰዎች እንደ ተወርዋሪ ኮከብ በፊታችን ብልጭ ብለው ከፊታችን ተሰውረዋል። ካሳሁን አሰፋ በጋዜጠኝነቱ…

ሀጫሉ ሁንዴሳ

እኩለ ሌሊት አካባቢ ነው። ማኅበራዊ የብዙኀን መገናኛዎች ይልቁንም ፌስቡክ ግን እኩለ ቀን የሆነ ያህል ብዙዎች ሲመላለሱበት ነበር። ሁሉንም ያስደነገጠ፣ ያስጨነቀና ያሳዘነ ጉዳይ በዜና ተሰራጭቷል። ‹ውሸት አድርገው! ሕልም ይሁን!› ብሎ የሚጸልየውም ጥቂት አይመስልም። ዜናው በእርግጥም ልብ የሚሰብር ነበር። ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com