የእለት ዜና
መዝገብ

Category: የምርጫ ዜናዎች

ምርጫ ቦርድ ለኹተኛው ዙር ምርጫ የአየር ስዓት ድልድል አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር መስከረም 20/2014 በሚደረገው ምርጫ ላይ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚውል የነጻ አየር ሰዓት መደልደሉን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 28/013 ከኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር…

ለብዙኃን መገናኛ ቀደም ሲል የተሰጠው ባጅ ለኹለተኛው ዙር ምርጫ ያገለግላል ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አጠቃላይ ምርጫን መዘገብ ለሚፈልጉ ለአገር ውስጥና ለውጭ የብዙኃን መገናኛ አካላት እና ጋዜጠኞች በተለያየ ጊዜ የፈቃድ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጥሪ በማድረግ መዘገብ የሚያስችላቸውን ልዩ የዘገባ ባጅ መስጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሰኔ 14/2013 በተካሄደባቸው አካባቢዎች ከቦርዱ…

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች ምርጫ ካርድ እያወጡ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች በተዘጋጀላቸው የምርጫ ጣቢያ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ መሆኑን የሐረሪ ክልል መንግሥት አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች በተዘጋጀላቸው ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ ነው ያለው የክልሉ መንግሥት፣ በከተማ…

ፖለቲካ ፓርቲዎች ለኹለተኛው ዙር ምርጫ ወኪል እንዲያቀርቡ ቦርዱ ጠየቀ

መስከረም 20/2014 ለሚካሄደው ኹለተኛ ዙር ምርጫ የፓርቲ ወኪል ዕውቅና መታወቂያ ፍቃድ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ወኪላቸውን እንዲያቀርቡ ቦርዱ ጠይቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ቦርዱን ባቋቋመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ…

የሱማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች እንዲደገም ተወሰነ

መስከረም 20/2014 ለሚካሄደው ኹለተኛው ዙር ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተካሂዶ ነገር ግን ችግር የተገኘባቸው የሱማሌ ክልል ምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንደሚደገም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በሱማሌ ክልል እየተከናወነ በነበረው የመራጮች ምዝገባ ላይ በቀረበ ከፍተኛ አቤቱታ እና ማስረጃ መሠረት ቦርዱ ማጣራት…

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በቤኒሻንጉል ለተገደሉበት ዕጩ ምትክ ማቅረቡን አሳወቀ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ(ቦዴፓ) አባል እና በክልሉ መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት ድርጅቱን ወክለው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አይናድስ ሞላ ደንበሩ በግልገል በለስ ከተማ ሐምሌ 13 /2013 ሞተው መገኘታቸውን ፓርቲው ማሳወቁ ይታወሳል። ፓርቲው በተሻሻለው የምርጫ፣ ፖለቲካ…

ኹለተኛው ዙር ምርጫ መስከረም 20/2014 እንዲካሄድ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ኹለተኛው ዙረት ምርጫ መስከረም 20/2014 እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቀ። ድምጽ አሰጣጡ የሚከናወነው በሱማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ሲሆን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማስተማር ላይ ከተሠማሩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሔሴ 17/2013 አገር ዐቀፍ ምርጫውን አስመልክቶ በማስተማር ላይ ከተሠማሩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት ማካሄዱን ገልጿል። በሲቪክና የመራጮች ትምህርት ክፍል አስተባባሪነት ማኅበራቱ በቡድን በቡድን ሆነው በምርጫው ወቅት አሳካናቸው ስለሚሏቸው እና ተግዳሮቶች ነበሩ ስላሏቸው እንዲሁም በቀጣይ ምን…

ጳጉሜ 1/2013 ይካሄዳል የተባለው ኹለተኛው ዙር ምርጫ ሊራዘም መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ በአንድ ጊዙ ለማካሄድ አለመቻሉን ተከትሎ በኹለት ዙር ለማድረግ መገደዱ የሚታወስ ነው። በዚህ የመጀመሪው ዙር ምርጫ ሰኔ 14/2013 ተካሂዶ ኹለተኛው ዙር ምርጫ ጳጉሜ 1/2013 እንድካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ቢሆንም ቦርዱ ቀኑን ለማራዘም ማሰቡ ተገልጿል። ቦርዱ…

የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሰኔ 14/2013 በተካሄደው ምርጫ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላይ በታዛቢነት የተሳተፉ የሲቪክ ማኅበረስብ ድርጅቶች በምርጫ ወቅት የገጠማቸውን ችግር፣ የምርጫው አሳታፊነት፣ የምርጫውን ገለልተኝነት፣ የምርጫውን ተአማኒነት እና ኮቪድ 19 በምርጫው ላይ የፈጠረውን ተጽዕኖ አንስተው የልምድ ልውውጥ አድርገውል። በምርጫው ታዛቢዎችን በማሰማራት እና የምርጫ አስፈጻሚዎችን በማስልጠን የተሳተፉ ሲቪክ ማኅበረሰብ…

ቦርዱ በሱማሌ ክልል የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ አስመልክቶ ያካሄደውን የምርመራ ሪፓርት አቀረበ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሱማሌ ክልል የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ አስመልክቶ በአጣሪ ባለሙያዎች ያካሄደውን ምርመራ ሪፓርት ለፓርቲዎች አቀረበ። ነሐሴ 11/2013 በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተካሄደውን የመራጮች ምዝግባ አስመልክቶ በባለሙያዎች አጣሪ ቡድን ማጣራት ማከናወኑ ተገልጿል። በመድረኩም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ የቦርዱ…

በምርጫው ተፎካክረን ኢትዮጵያ አሸንፋለች፤ አገር ለማዳን ሳንፎካከር በጋራ ቆመን እንመክታለን

በምርጫው ተፎካክረን ኢትዮጵያ አሸንፋለች። አገር ለማዳን ሳንፎካከር በጋራ ቆመን እንመክታለን ሲሉ የተፎካካሪ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የእናት ፓርቲ ከፍተኛ ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነበረው ፉክክር ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርጓል። ኢትዮጵያን አሁን ለገጠማት የሕልውና አደጋ…

ምርጫ ቦርድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተተኪ ዕጩዎችን እንዲያሳውቁ ዕድል መስጠቱን አስታወቀ

ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ተወዳዳሪ ሆነው መቀጠል ለማይችሉ ዕጩዎች ተተኪ የሚሆኑ ዕጩዎችን ለመቀየር ፓርቲዎች ካሳለፍነው ሐሙስ ማለትም ከነሐሴ 6 እስከ ቅዳሜ ነሐሴ 8/2013 ድረስ ማመልክት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጳጉሜ 1/2013 ምርጫ በሚያካሂድባቸው…

ባልደራስ ህወሓትን ከመቃብር ለማንሳት የሚደረገውን የዓለም ዐቀፉ ሴራ መመከት እንደሚገባ ገለጸ

ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን አሁን ላለችበት ሁኔታ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማንሳት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተባበረ ክንድ መመከት እንደሚገባ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ። የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ “ትህነግ የአክራሪ ብሔርተኝነት የመጨረሻው ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል። የመንግሥት የተናጠል ተኩስ…

ድጋሚ ቆጠራ እንዲደረግባቸው የተባሉ ምርጨ ክልሎች ቆጠራ አካሄዱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋሚ ቆጠራ እንዲከናወን ባዘዛባቸው አምስት የምርጫ ክልሎች ቆጠራ መካሄዱን የቦርዱ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ ከወሰነባቸው አስር የምርጫ ክልሎች በአምስት ምርጫ ክልሎች ዳግም ቆጠራ መካሄዱ…

ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጉዳይ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ወይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አገር ዐቀፍ ምርጫውን አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር መግለጫ ካወጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። በውይይቱ አምስቱም የቦርድ አመራሮች፣ የቦርዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ኹሉም የቦርዱ የሥራ ክፍል ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብረቱካን ሚዴቅሳ ማኅበራቱ…

የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የደንብ ልብስ ለብሰው ከሚያጭበረብሩ አካላት ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ

የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ “ፖሊስ ወይም የጸጥታ አካላት ነን” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንጹሐን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የፌዴራል፣ የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው፣ ሐሰተኛ መረጃ ይዘው፣…

የድህረ ምርጫ አገራዊ ግንባታ ኹሉን ዐቀፍ ውይይት ሊዘጋጅ ነው

በድህረ ምርጫ ጊዜያት ውስጥ ባሉ አንኳር የአገር ግንባታና ሌሎች ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር በቅርቡ ኹሉን ዐቀፍና አሳታፊ አገራዊ የምክክር መድረክ እንደሚዘጋጅ “ማይንድ ኢትዮጵያ” አስታወቀ። ውይይቱም በዋናነት በድህረ ምርጫ ጊዜያት ውስጥ ባሉ አንኳር የአገር ግንባታና ሌሎች ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም…

የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የቁጫ ሠላም በር ምርጫ ክልል አሸናፊ ሆነ

የድምጽ መደመር ሒደቱ እንዲቆም ውሳኔ የተሰጠበት የቁጫ ሠላም በር ምርጫ ክልል ላይ፣ የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አሸናፊ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ክልሉ ከመነሻው ጀምሮ ቅሬታና አቤቱታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎቸ በመቅረባቸው ሊከሰቱ የሚችሉ ሥጋቶችን ለማስቀረት…

የተቋማት ቁርጠኝነት ለቀጣይ አገራዊ ሥራዎች ትምህርት የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት የሚዘጋጀው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ “ዴሞክራሲ አንድ እርምጃ፤ የስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ ምልከታዎች” በሚል ርዕሰ ሐሳብ ውይይት አካሂዷል። የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሒደት የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ግንባታ አንድ እርምጃ ወደ ፊት የወሰደ እና ለቀጣይ አገራዊ ምርጫ…

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዕጩ በመተከል ተገደለ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ(ቦዴፓ) ዕጩ ተወዳዳሪ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ላይ መገደሉን ፓርቲው አስታወቀ። በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል፣ ቦዴፓን ወክሎ ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር በዝግጅት ላይ የነበረው አይናድስ ሞላ በግልገል በለስ ከተማ ሙቶ ተገኝቷል ተብሏል።…

ኢዜማ በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደገም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በ28 ምርጫ ወረዳዎች ሰኔ 14/2013 የተደረገው ምርጫ በድጋሚ እንዲደረግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገባ። ኢዜማ ሰኔ 14/2013 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የተደረገው ምርጫ ላይ ከድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ፣ ከቀበሌ እስከ ክልል…

“ኢትዮጵያ ከምርጫው በኋላ ሲኦል ትሆናለች ያሉ አፍረዋል” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

“ኢትዮጵያ ከምርጫው በኋላ ሲኦል ትሆናለች ያሉ አገራትና 27 ዓመት ተከፋይ የነበሩ ሚዲያዎች አፍረዋል፤ አንዳንድ አገራትም አሁን ላይ ስለምርጫው እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ጀምረዋል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና…

አገራዊ ምርጫው ከመነሻው ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እንደነበር ተገለጸ

የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዝደንት ሰለሞን ታፈሰ፣ የዘንድሮውን ጠቅላላ ምርጫ ክንውን ተከትሎ የፓርቲያቸውን አቋም በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። ፓርቲው ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመነሻው ጀምሮ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ጠቅሰው፣ በሂደቱ ዴሞክራሲያዊ የክርክር መድረክ የታየበትና ሰፊ የሚድያ ሽፋን ያገኘ እንደነበር ገልጸዋል። ፓርቲዎች ተንቀሳቅሰው…

በ10 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ቅሬታን ተከትሎ በ10 ምርጫ ክልሎች የድጋሚ ምርጫ እና ውጤት ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ሰኔ 14/2013 በተካሄደው ምርጫ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ያቀረቡት ቅሬታ ከመረመረ በኋላ በ10 የምርጫ ክልሎች የተካሄደው…

አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ተጠያቂነት ላይ መሥራት እንዳለበት ተጠቆመ

አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ተጠያቂነትን ማስፈን ላይ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚጠበቅበት የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ሕግ ባለሙያ አልማው ክፍሌ(ዶ/ር) ጠቁመዋል። ከኹለት አስርተ ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ያሥተዳደረው ‘ኢህአዴግ’ መራሹ መንግሥት አገርና ሕዝብን ያላስቀደመ እንደነበር ያስታወሱት የሕግ ባለሙያው፣ ስርዓቱ ለሕዝቦች አብሮነት እንዲሁም የዜጎችን ከቦታ…

ምርጫ ቦርድ በገለልተኝነት መሥራቱ የሚመሰገን ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማከናወን የሄደበት ርቀት የሚደነቅ መሆኑን በምርጫው በዕጩነት የተወዳደሩ ፖለቲከኞች ገለጹ። ምርጫው ካለፉት አምስት ምርጫዎች በተሻለ መልኩ አሳታፊ እንደነበርም ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤት ባለፈው ቅዳሜ ይፋ አድርጓል። በመርሃ…

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ የተቺዎችን አፍ ያዘጋ ነው ሲሉ አንድ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ውጤታማ መሆኑ፣ ከተለያዩ ወገኖች ሲሰነዘሩ የነበሩት ትችቶችን በሙሉ ውድቅ ያደረገ ነው ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ላውረንስ ፈሪማን ተናገሩ። ፊሪማን ኢትዮጵያዊያን ያካሄዱት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ምን ያህል ለዲሞክራሲ መጎልበት ፍላጎት እንዳላቸው ያሳዩበት ነበረም…

የአፋር ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲደገም ወይም ሌላ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠየቁ

የአፋር ክልል ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በአፋር ክልል ሰኔ 14/2013 የተደረገው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑ ምርጫው እንዲደገም ጠይቀዋል። የፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤት ምርጫው ድጋሚ የማይደረግ ከሆነ፣ ሌላ የፖለቲካ መፍትሔ በአስቸኳይ መፈለግ አለበት ብሏል።…

በነገሌ ምርጫ ክልል ተቋርጦ የነበረው ምርጫ ተካሄደ

በነገሌ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ባሳለፍነው ሃምሌ 1/2013 ምርጫ መካሄዱ ተገልጿል፡፡ በነገሌ ምርጫ ክልል ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች ተመድበው ምርጫ ማስፈጸማቸው ተመላክቷል፡፡ በነገሌ ምርጫ ክልል ለክልልና ለተወካዮች ምክር ቤቶች ኹለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት…

error: Content is protected !!