የእለት ዜና
መዝገብ

Category: ወቅታዊ

ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑበት ደቡብ ወሎ ዞን

ዕሮብ ግንቦት 03/2014፤ በዞኑ መቀመጫ ደሴ ከተማ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እያቀኑ ነበር። ሆኖም በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች እንዳሉ ተማሪዎች እየተሳሳቁና እየቦረቁ ሰብሰብ ብለው የመሄዱን ነገር በሰፊው ሲከውኑት አይታይም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ባይሆን ብዙዎች በተሰላቸ ሞራልና ፈገግታ በራቀው ፊት…

ከስጋት ያልወጣው የኘሬስ ነፃነት

ሚዲያ ከመንግሥት እና ከተለያዩ አካላት ነፃ መሆን እንዳለበት የሚታመን ሲሆን፣ ያለ ፕሬስ ነፃነት እንዲሁ ዴሞክራሲን ማምጣት ወይም ማረጋገጥ የማይታሰብ ጉዳይ ነው። ለረዥም ዓመታት የፕሬስ ነፃነት ካልተረጋገጠባቸው አገራት ተርታ ደግሞ ኢትዮጵያ ትጠቀሳለች። ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ለፕሬስ ነፃነት ከማይሰጡ አገሮች ተርታ ትሰለፍ…

እገታና እንግልት እስከ መቼ?

ሥሙ እንዲጠቀስ አልፈቀደም፤ ታሪኩን ግን አጫወተን። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን፣ በተለያየ ጊዜ የሚያደርገውን እገታ በተመለከተ በቤተሰቡ ላይ የደረሰውን ነገረን። ታሪኩ እንዲህ ነው፤ የባለታሪካችን ወላጅ አባት በአካባቢው አሉ ከሚባሉ ምሁራን መካከል ተጠቃሽ ነበሩ። ታዲያ ፍርድ…

የፔትሮዶላር ዘመን የማብቂያው መጀመሪያ ላይ እንገኝ ይሆን?

ፔትሮዶላር ራሱን የቻለ መገበያያ ገንዘብ ሳይሆን የዓለም ድፍድፍ ነዳጅ የሚሸጥበት የአሜሪካንን ዶላር ጥቅም ላይ የማዋል ሥርዓትን የሚገልፅ መጠሪያ ነው። ይህ አገላለፅ ከፈረንጆቹ 1970ዎቹ ጀምሮ ለፖለቲካ ተፅእኖም ሆነ ለኢኮኖሚ ማብራሪያ ጥቅም ላይ ሲውል የነበረ ነው። ፔትሮዶላር እየተባለ አሁን ድረስ የሚገለፀው አሜሪካን…

ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ወቅት በክልሎችም ሆነ በመዲናዋ በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ  ሲዘዋወር ተያዘ የሚል መረጃ በተደጋጋሚ ይሰማል። ይህ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት ይልቁንም የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በተደጋጋሚ እንደሚስተዋል የተለያዩ…

ከሳዑዲ የሚመለሱ ዜጎችን በቋሚነት ለማቋቋም ምን እየተሠራ ነው?

መሠረት በቃሉ (ስሟ የተቀየረ) ከአረብ አገር ከመጣች ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ አልሆናትም። አነስተኛ ቡና ቤት ከፍታ በመሥራት ላይ ትገኛለች። በአረብ አገራት እየተዘዋወረች ስምንት ዓመታትን ብትቆይም ይኖረኛል ብላ ያሰበችውን ያህል ለፍታ ማጠራቀም አልቻለችም። ለአዲስ ማለዳ ስትናገርም፣ ‹‹አረብ አገር ያን ያህል ዓመት…

የኢትዮጵያ አርበኞች የድል ቀን ሲታወስ

ከዛሬ 86 ዓመት በፊት 1928 ጣሊያን ኢትዮጵያን በመውረር፣ በዚያው ዓመት ሚያዚያ 27 ማርሻል ባዶሊዮ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በማስወረድ የጣሊያን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቀል ማድረጉን ታሪክ ያወሳል። ጣሊያን በ1888 በተካሄደው የአድዋ ጦርነት ጊዜ የደረሰባትን አሰቃቂ ሽንፈት ለመበቀል ለአርባ ዓመታት…

የ2014 ረመዳን ወር ጾምና ድባቡ

የ2014 ረመዳን ወር ጾምና ድባቡኢትዮጵያ ልዩነታቸው አንድነታቸውን የማይነጥለው አንድነታቸው ልዩነታቸውን የማይጠቀልለው በርካታ የዕምነት ተከታይ ዜጎችን እቅፍ ድግፍ አድርጋ የያዘች አገር መሆኗ የአደባባይ ሀቅ ነው። ታዲያ ይህ ወቅትም የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የረመዳንን ጾም የቁርዓን ሥርዓት በሚፈቅደው መልኩ እየጾሙ ይገኛሉ። ከቀናት በኋላም…

አበበች ጎበና የሕፃናት ክብካቤና ልማት ማኅበር በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

አዲስ ማለዳ የፋሲካን በዓል ምክንያት አድርጋ ‹እንኳን አደረሳችሁ! እንዴት ናችሁ?› ስትል ከጎበኘቻቸው መካከል ከተመሠረተ ከአርባ ዓመታት በላይ የሆነው አበበች ጎበና የሕፃናት እንክብካቤና ልማት ማኅበር አንዱ ነው። በደጓ እናት አበበች ጎበና (ነፍስ ኄር) የተመሠረተው ይህ ድርጅት፣ አሁንም የእርሳቸውን ሕልም እውን ለማድረግ…

ትኩረት የተነፈጋቸው ቅርሶቻችን

ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ሀብቶች መገኛ እንደሆነች ይታወቃል። ሆኖም እነዚህ ሀብቶቿን ተንከባክባ እና ለቀጣይ ትውልድ እንዲሻገር ከማድረግ አኳያ ብዙ ሥራዎች ይጠበቁባታል። በተለያዩ አካባቢዎች ቅርሶቿ ላይ የተጋረጡትን አደጋዎች በትኩረት መመልከት እንደሚያስፈልግም ብዙዎች ሲያነሱ ይደመጣሉ። በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት…

መፍትሔ ያላገኘው የአንበጣ መንጋ

የአንበጣ መንጋ በታሪክ ውስጥ የሰውን ልጅ ለረሀብ እና ለስደት ከሚዳርጉ የተፈጥሮ ክስተቶች መካከል አንዱ ነው። ከ2011 ጀምሮም ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ የአፍሪካ ቀጠና የበርሀ አንበጣ መንጋ አረንጓዴ ሰብሎችን ሁሉ በስፋት እያወደመ ይገኛል። በዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰውና እንስሳትን ለረሃብ መዳረጉን እና…

ለነዋሪዎቹ ገሀነም ሆኖ የኖረው ወልቃይት ጠገዴ

የኢትዮጵያን የኻምሳ ዓመት ታሪክ የሚያወሱ የጽሑፍ መረጃዎች እንደሚሉት ወታደራዊው መንግሥት ደርግ የአገሪቱን ሥልጣን ተቆጣጠሮ ብዙም ሳይቆይ ታጣቂ ቡድኖች ተፈጥረው ሥርዓቱን ሲታገሉ ቆይተዋል። በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠሩ የብሔር ፖለቲካ ቡድኖች የኋላ ኋላ የደርግ ሥርዓት ከሥልጣን እንዲወገድ ምክንያት ሆነዋል። በ1968 ደደቢት በረሃ…

የሕገ መንግሥቱ የመሻሻል ዕድል

የአንድ አገር መተዳደሪያ ዋልታ የሆነው ሕገ መንግሥት ሲረቀቅ ኹሉንም ዜጋ በተዋረድ ማሳተፍ ይገባዋል። ነገር ግን በተቃራኒው የጥቂት ቡድንን ፍላጎት እና ዓላማ መሠረት አድርጎ አንድ ሕገ መንግሥት ከተረቀቀ የግጭት መነሻ ከመሆን ባለፈ ለአገር መፍረስ ምክንያት ይሆናል የሚሉት በዋናነት የሕግ ባለሙያዎች ናቸው።…

“ኤች አር 6600” ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?

በቅርቡ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የነበረው የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ሊያጸድቀው ይችላል የተባለው ኤች አር 6600 ረቂቅ ሕግ ነው። ረቂቁ በርከት ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በመያዝ በ12 አንቀጾች የተዘጋጀ ነው። ረቂቅ የሕግ ዐዋጁ ‹‹በኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት፣ እንዲሁም ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለመደገፍ የታሰበ፣…

የሴቶች ሚና በአገራዊ ምክክር መድረክ

‹ጤና ካለ› እንደሚባለው ኹሉ፣ ‹ሠላም ካለ› ኹሉም እንዳለ ይቆጠራል። ኹሉም ባይኖር እንኳ በተቻለ አቅም አስፈላጊው ነገር እንዲኖር ለማድረግ መንቀሳቀስ ይቻላል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት በቅድሚያ ሠላም የሚያስፈልጋቸው ለዛ ነው። ሠላም ካልቀደመ፣ መረጋጋት ከሌለ እንኳን ዕድገት ሊታሰብ ቀርቶ ከነበረውን ደረጃ ወደኋላ…

ኧረ የዘይት ያለህ!

የኑሮ ውድነት ሲነሳ አሁን ላይ በማኅበረሰቡ አንደበት ቀድሞ ሲነገር የሚሰማው ‹‹ኧረ ዘይት!›› የሚል ማማረር የበዛበት ድምጽ ነው። የዘይት ጉዳይ ምንም እንኳ የኑሮ ውድነት በተነሳ ቁጥር ከቤት ኪራይ፤ ከትራንስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተዛምዶ ሕዝቡን እያማረረ ያለ ችግር ከሆነ ቢቆይም፣…

ድርቅ የተከሰተባቸው ክልሎች ሰቆቃና ተስፋ

ከአራት ዐሥርት ዓመታት በኋላ ለከፋ ድርቅ የተጋለጡት ደቡብ፣ ኦሮሚያና ሱማሌ ክልልን ጨምሮ፣ በደቡባዊ ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶች ላይ እየደረሰ ያለው የርሀብ አደጋ አድማሱን አስፋፍቶ ቀጥሏል። በኦሮሚያ፣ አፋር እና ሱማሌ ክልል ለሦስት ተከታታይ…

የሰሜኑ ጦርነትና ሰብዓዊ አቅርቦት መስተጓጎል

የሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት መነሻውን ትግራይ ክልል አድርጎ ከተቀሰቀሰበት ከጥቅምት 24/2013 ጀምሮ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት ከአምስት ወር በላይ ማስቆጠሩን ተከትሎ፣ ጦርነቱ በተካሄደባቸው በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልል ያሉ ንጹኃን ዜጎችን ለሰብዓዊ ችግር ተጋልጠው ቆይተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች…

ሥራ ፈላጊዎችና የኤጀንሲዎች ሕገወጥ የገንዘብ ብዝበዛ

በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድና ሕጉን መሠረት አድርገው ፍቃድ አግኝተው የሚሠሩ ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አሉ። የዛኑ ያህል በአንጻሩ በሕገ ወጥ መንገድ፣ በመንግሥት በኩል እውቅና ሳያገኙ፣ ተገቢውን ዓመታዊ የሥራ ግብር ለመንግሥት አካል ሳይገብሩ በሥራው የተሠማሩ በርካታ ድርጅቶች ይገኛሉ። ዓለም ዐቀፍ ድንጋጌዎችም…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሲታወሱ!

የንጉስ ሃርቤ ውጥን አራተኛው ስኬት ፤የብዙ አባቶች ተጋድሎ በረከት፤ የብስና የባህር እንባ፤ የዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ማሰሪያ ገመድና የረጅም ዘመን ትግል ውጤትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ዘላለማዊው ቤታቸው የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ተጠርተዋል።…

ብዙዎችን የሚነጥቀው የመኪና አደጋ መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚከሠተው የመኪና አደጋ በጦርነቱ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም ሌሎች መሠል የሰውን ልጅ ላይመለስ እስከወዲያኛው ከሚሸኙ መንስኤዎች ድርብ ችግር እየሆነ ከመጣ ሰንበትበት ቢልም መፍትሔ የተገኘለት አይመስልም። የትኛውም አንቱ የተባለ ፈላስፋ፣ ተመራማሪ፣ መምህር እንዲሁም መሰል የዕውቀት ማደሪያ የሆነ ሰው፣ ጥበብን…

‹የሴቶች ቀን› መቼ ነው?

‹‹ብነግርሽ ለውጥ ይመጣል?›› አለችኝ፤ መቅረጸ ድምጹን አስተካክዬ ድምጿ ሊሰማበት በሚችልበት ርቀት ላስቀምጠው ስሰናዳ። በቅርበት የሚያውቋት ሰዎች ከደረሰባት ችግርና ካሳለፈችው በመነሳት ነበር እንዳናግራት የጠቆሙኝ። ያሳለፈችው ነገር እጅግ የሚያሳዝን ነው። ታሪኳን መግቢያ አድርጌ የማዘጋጀው ጽሑፍ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ሲነበብ፣ አንባቢ ሰውነቱን አስታውሶ…

ዓባይ ለገጠሩ ብርሃን ያመጣ ይሆን?

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታው የተጀመረው መጋቢት 24/2003 ሲሆን፣ ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመንግሥትም ሆነ በግል ሥራ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ከገቢያቸው ቀንሰው ቦንድ በመግዛት ለተከታታይ ለ11 ዓመት የበኩላቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡ ግድቡን ለመገንባት ከታሰበበት ወቅት ጀምር አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ብዙ መስዋዕትነት እየተከፈለበት…

ልመና በሕፃናት ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳ

ህይወት ንጋቱ የአንድ ልጅ እናት ሲሆኑ፣ ልጃቸውን የሚያሳድጉት ጎዳና ላይ ላስቲክ ዘርግተው በሚያገኙት ሳንቲም እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ልጃቸውን አስከትለው በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዩ ጎዳናዎች የዕለት ምግብ ፍለጋ ሲባዝኑ የሚውሉት ህይወትን አዲስ ማለዳ ያገኘቻቸው አራት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡ ቤት ብለው…

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ማን ናቸው?

የካቲት 14/2014 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ለተቋቋመው አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ11 ኮሚሽነሮችን ሹመት አጽድቋል። የኮሚሽነሮቹ ማንነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ መስፍን አርአያ(ፕ/ር) መስፍን አርአያ(ፕ/ር) በቅርቡ የተቋቋመው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ መስፍን ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ሲሆን፣ በተለይ በሕክምና ዘርፍ…

የካቲት 12 በኢትዮጵያ ታሪክ ሲታወስ

መላ አፍሪካውያን በቅኝ ገዥዎች እጅ በወደቁበት ዘመን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሥር ላለመውደቅ ብርቱ ተጋድሎ ያደረገችና ነጻነቷንም አስጠብቃ የዘለቀች ብቸኛ አፍሪካዊት አገር ናት። በ1888 ከጣሊያን ጋር የተደረገው ጦርነት በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ተመልሶ ቢመጣ ከመጀመሪያው በበለጠ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ80 ዓመት ጉዞ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ታሪክ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ በመንግሥት ባለቤትንት የሚተዳደር የፋይናንስ ተቋም በመሆን በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት የሚሰጥ ባንክ ነው። የ80 ዓመት ዕድሜ ያለው ባንኩ፣ ዕድሜ ጠገብ ከሆኑ የመንግሥት ድርጅቶች ተርታ የሚሰለፍ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት ይቻላል። በ1935 እንደተቋቋመ…

ዳያስፖራው ምን አለ?

ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭም የሚደርስባትን ጫና ለማርገብ ከተጠቀመችባቸው ዘዴዎች አንዱ በውጭ የሚኖሩ ኢትጵያውያን ወደ አገራችሁ ግቡና ሕዝባችሁን በኢኮኖሚ ደግፉ፣ የዓለም ማኅበረሠብም ስለኢትዮጵያ የያዘውን የተዛባ አመለካከት በመቀልበስ ዕውነታውን አሳዩ የሚል ነበር። በዚህም፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀስቃሽነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው…

ከሥራ የታገዱ የአዲስ አበባ ሊስትሮዎች እጣ ፈንታ ምን ይሆን?

ርብቃ ወልደኪዳን ይባላሉ። በአዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከመስቀል አደባባይ ወደ መገናኛ በሚወስደፈው ጎዳና ባምቢስ መሻገሪያ ላይ በሊስትሮ (ጫማ በማጽዳት) ሥራ ከተሠማሩ ዘጠኝ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ርብቃ ለድፍን ዘጠኝ ዓመታት ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት ከሊስትሮ ሥራ በሚያገኙት ገቢ ነው። ባለቤታቸው ‹‹የሚጥል በሽታ›› ስላለባቸው…

እስከ መቼ ወደጓዳ?

አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባን ለማዘጋጀት ሽር ጉድ እየጨረሰች ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊትም አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራዎችን ለመቀበል በብዙ ስትደክም ነበር። በዚህ መካከል ግን ጎዳናዎቿ ላይ ጥግ ጥግ ይዘው የሚሠሩ ጫማ በመጥረግ፣ ጥቃቅን ሸቀጦችን በመሸጥ የሚተዳደሩ ሰዎች የእንግዶችን መምጣት ተከትለው ለቀናት…

error: Content is protected !!