በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑት ውስጥ 78 በመቶ ሲያልፉ 22 በመቶ የሚሆኑት ውጤታቸው ከ50 በታች መሆኑ ተገለጸ

0
390

ዓርብ ሐምሌ 05 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የ2016 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይፋ መሆኑን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከተፈተኑት 85 ሺህ 219 ተማሪዎች 67 ሺህ 903 የሚሆኑት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማግኘት ችለዋል።

በዚሁ መሰረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን ተወስኗል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ውጤትም በቅርቡ እንደሚለቀቅ ቢሮው ገልጿል።

የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ

https://aa.ministry.et/#/result

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here