የእለት ዜና
መዝገብ

Category: ሰሞነኛ

<ግራጫ> አበባ

ሰሞኑን መነጋገሪያ ከሆኑ አገራዊ ጉዳዮች አንዱ አዲስ አበባ ቀለሟ ግራጫ እንዲሆን መወሰኑ ነው። አበባ የተባለች ከተማ ግራጫ ትሁን መባሉ ምን ዓይነት ግራጫ አበባ ቢያውቁ ነው በሚል ሐሳቡ ለትችት ተዳርጓል። ከተማዋ ካሏት ሕንፃዎች አብዛኞቹ ግራጫ ስለሆኑ ሌሎቹም እንደነሱ ይምሰሉ በሚል፣ ከግማሽ…

አጋቹ ማን ነው?

ካለፈው ሳምንት ቀደም ብሎ የአንድ የመገናኛ ብዙኅን ባለሞያ የሆነ ጋዜጠኛ <መታሰር> ጉዳይ በማኅበራዊ ሚድያው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የጋዜጠኛ መታሰር እንግዳ ነገር አይደለም፤ ግን በስውር <ታግቶ> ነው የተወሰደው መባሉ የብዙውን ትኩረት ስቧል። ጋዜጠኛውን ማን እንደወሰደው፣ የት እንደተወሰደና ማን እንደመለሰው ሳይታወቅም ነው…

የመካሪዎች ምስጋና

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ የኢድ አልፈጥር በዓል በተከበረበት ወቅት ያልተጠበቀ ክስተት ተፈጥሮ ብዙዎች እንዳዘኑ ተመልክተናል። የበዓሉ ታዳሚ በደስታው ቀን ወደ ረብሻ እንዲያመራ ያደረገው ምክንያት በተለያዩ ወገኖች እየተጠቀሰ ቢሆንም፣ የሚመለከተው አካል አጣርቶ በቶሎ እንዲያሳውቅ ኹሉም በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል። አንድ ፌደራል ፖሊስ አስለቃሽ…

‹የሃይማኖተኞች› ዝቅጠት

ሠሞኑን ብዙዎችን ያስደነገጠ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው የመጠፋፋት አዙሪት ውስጥ ተገብቷል። በቀላሉ ሊበርድ ይችል በነበረ አለመግባባት ሳቢያ በተፈፀመ ድርጊት እስከ አሁን ብዙዎች መሞታቸው በርካታ ንብረትም መውደሙ እየተነገረ ይገኛል። ሃይማኖታዊ ጥቃቶችም ሆኑ የእርስ በርስ መጠፋፋቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ ተጠናክረው…

የአባት አገር ሩስያ ዘመቻ

ሠሞኑን አነጋጋሪ ከሆኑና ብዙዎችን ግራ ካጋቡ ክስተቶች መካከል በሳምንቱ መጀመሪያ የሩስያ ኤምባሲ በር ላይ የነበረ ሠልፍ አንዱ ነው። ለቀናት ያለማቋረጥ ሠነድ የያዙ ኢትዮጵያዊያን ከወትሮው በተለየ በብዛት ተሰልፈው የተመለከቱ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ጉዳዩን ለማጣራት ሞክረው ነበር። ሩስያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለችውን…

የአጋላጭ ተጋላጭነት ድራማ

ከሰሞኑ መነጋገሪያ ከነበሩ የአገሪቱ ጉዳዮች መካከል ሙስናን የተመለከተው በዓይነቱ ለየት ያለ ነበር። ፀረ ሙስና የወራት የፀረ ሙስና ዘመቻ እጀምራለሁ እያለ የሚሰርቁ ተቆጥበው እንዲጠብቁት ይሁን ተዘጋጅተው እንዲያቋርጡ ባይታወቅም፣ ማስጠንቀቂያ አዘል እቅዱን ለሕዝቡም ለሙሰኞቹም ሲያስተጋባ የነበረበት ወቅት ነው። በሳምንቱ መጀመሪያ ሰሞን አንድ…

ጠያቂ፣ ጥያቄና ተጠያቂ

ባሳለፍነው ማክሰኞ (ሚያዝያ 27/2014) በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቀረበ አንድ ቃለመጠይቅ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ነበር። ጠያቂው የፋና ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን፣ ተጠያቂው ደግሞ የባልደራስ ፓርቲው እስክንድር ነጋ ነበሩ። ሰፋ ደግሞ ቆይቶ ጠበብ፣ ከፈት ደግሞ መልሶ ዘጋ፣ ደግሞ ከፈት የሚል የሚመስለው መደበኛው የመገናኛ…

የአውራ ጎዳናው ውዝግብ

አውራ ጎዳና ሲባል ዋና መንገድ እንደሆነ ነበር አብዛኞቻችን የምናውቀው። ከሠሞኑ ግን አውራ ጎዳና የምትባል አነስተኛ ከተማ መኗሯን እየሠማን እንገኛለን። ይህች ቀበሌ መነጋገሪያ የሆነችው የኢትዮጵያ ኹለቱ ትልልቅ ክልሎች የሚቃረን መረጃን አካባቢዋን በተመለከተ ካወጡ በኋላ ነበር። መጀመሪያ ስለቦታው የተነገረው በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ…

አስኮራጅ ያልፈቀደው የሹመኞች ኩረጃ

ባሳለፍነው ሳምንት መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ባለሥልጣናት በደረሰ ሰብል መካከል ጠረጴዛ ተዘርግቶላቸው፣ ወንበር ተደርድሮላቸው የተካፈሉት ማዕድ(ውኃ) ነው። ይህ የሹመኞች ስብስብ በራሱ ቁጣን ባያስከትልም፣ አንድ አካባቢ ድርቅ ሁኖ፣ ሌላው በረሃብና ጦርነት እየታመሰ ባለበት በዚህ አስከፊ ወቅት እህል አስረምርመው ነው ወይስ አስነስተው…

‹ጠብ ለኩሱ› ግብዣ

ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኀንና ማኅበራዊ ሚድያዎችንም ሳይቀር በብዙ እንድንታዘብ ያደረጉን ክስተቶች ባሳለፍናቸው ጥቂት ወራት ውስጥ አልፈዋል። በሚድያው ዘርፍ ፊተኞችና ኋለኞች ናቸው ብለን እንገምታቸው የነበሩ ዓለማቀፍ ተቋማት፣ የኢትዮጵያን የጦርነትና አለመረጋጋት ጉዳይ የዘገቡበትን መንገድ ስንመለከት ‹ውይ! እንዲህ ኖራችኋል ለካ!› ብለን ብዙዎቻችን አዝነንባቸው ነበር።…

ዘይትና ዳቦ

ሠሞኑን መነጋገሪያ ከሆኑ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ለቀልድና ለቧልት ምቹ የነበሩት፣ የዘይት ዕጥረቱንና የዳቦ መጀመርን የተመለከቱ ወሬዎች ናቸው። ዘይት አንድ ሺሕ ብር ገባ ተብሎ ብዙዎች በኑሮ ውድነቱ ሲማረሩ ነበር። የሕዝብ መማረርን ከቁብ ያልቆጠሩት አስተያየት ሰጪዎች ሲሳለቁ የቆዩ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ…

የአገራት ውግንና

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እየተጋጋለ ተሳታፊዎችንም እያበዛ በመጣበት በዚህ ሠሞን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሩሲያን እናውግዝ የሚል ጥሪ አቅርቦ፣ የዓለም አገራትን በተወካዮቻቸው አማካይነት በአስቸኳይ እንዲወስኑ አሜሪካና ግብረአበሮቿ ጫና አሳድረው ነበር። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሩሲያን ለማግለል የተጠራውን ጉባዔ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላት…

የሥጋ ቤቶች ወግ

ሠሞኑን ቅበላ ነው፤ በክርስትና ዕምነት ታላቅ የሚባለው የሁዳዴ ጾም መያዣ ነው። ታድያ ጾሙ ከመግባቱ በፊት የጾም መያዣ ምግቦች ሁሉ እረፍት አያገኙም። ሥጋ ቤቶችም ‹ጾም ከገባ በኋላ ብዙ እንቅስቃሴ ስለማይኖር ቶሎ ቶሎ እንሥራ› ብለው የኃምሳ አምስት ቀናት ሒሳባቸውን ከወዲሁ በቅበላ ለማካካስ…

የጎጃሙ መስመር ዕልቂት

ባለፉት ሳምንታት መነጋገሪያ ከነበሩ አንኳር ጉዳዮች መካከል ከአዲስ አበባ-ባህርዳር-ጎንደር መስመር ጋር በተገናኘ መንገደኞች ላይ ሲፈፀም የቆየ ግድያ አንዱ ነው። የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ከመሀል አገር የሚያገናኘውን መስመር በተደጋጋሚ እንዲዘጋ ያደረገው የሠላም ዕጦት መንስዔ በአካባቢው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መግባት እንደሆነ ይታወቃል። መንግሥት…

የቅርስ ምዝበራ

የኢትዮጵያ ቅርሶች መመዝበር የጀመሩት ቅርስ ይጠበቅ ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝቶ እንክብካቤ ሳይደረግ በፊት ነው። በግራኝ የወረራ ዘመን ተዘርፈው የኦቶማን ቱርኮች መቀመጫ ወደሆነችው የአሁኗ ቱርክ የሔዱት ቅርሶችና ሀብቶችን በዘረፉ አረቦች ጭምር ተፅፎ የሚገኝ ነው። በ16ተኛው ክፍለዘመን ‹የዓባይን ምንጭ› ፍለጋ…

የጥሪው ጥሪ

በባህላችን ድግስም ሆነ የትኛውም ግብዣ ቦታውና ሠዓቱ ተጠቅሶ ለተጠሪ ይላካል። ተጋባዡም ሆነ በጉባዔው እንዲካፈል የተጠራው ወገን ቦታውም ሆነ ሠዓቱ ይቀየርልኝም ሆነ እዚህ ቦታ ይሁን ብሎ የጠሪዎቹን መርሃ-ግብር ሠርዞ የራሱን አቅዶ የጥሪ ጥሪ ማቅረብ አይቻለውም። ተጠሪ ሠዓቱም ሆነ ቦታው ካልተመቸው ይቀራል…

በይደር የቆው የፍፃሜ ውድድር

ሠሞኑን መነጋገሪያ ከነበሩ አገራዊ አጀንዳዎች መካከል እግር ኳስን የተመለከተው የተለየ ነበር። ውድድሩ የዋንጫ ሲሆን፣ የተደረገው ደግሞ በወረዳና በከተማ መካከል ነው። በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ውስጥ ባሉት ሳንኩራ ወረዳና በቅበት ከተማ አስተዳደር መካከል የተካሄደው የዋንጫ ውድድርን በርካቶች ሲጠብቁት የነበረ ነው ተብሏል።…

የሰንደቅ ትንቅንቅ

ሠሞኑን የበዓል ወቅት እንደመሆኑ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየውም ከአውድ ዓመቱ ጋር ግንኙነት ያለው የሠንደቅ ዓላማ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከመነጋገሪያነት አልፎ መጎዳጃ መሆን ከጀመረ ጥቂት የማይባሉ ዓመታት አልፈዋል። ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ መውጣቱን ተከትሎ ለዘመናት የቆየውና በየስርዓቱ መለያ ሲጨመርበት የነበረው የሠንደቅ…

በመስቀል አደባባይ ላይ የተነሳ አምባጓሮ

ሠሞኑን ከመነጋገሪያነት አልፈው በቃላት መሸነቋቆጫ ከሆኑ ጉዳዮች ቀዳሚው በመስቀል አደባባይ ላይ የተነሳው አምባጓሮ ነው። በቀደመው መንግሥት አብዮት አደባባይ ሲባል የኖረውና በኢሕአዴግ ዘመን ወደ ሕጋዊ ባለቤቱና ስሙ እንደተመለሰ የሚነገርለት አደባባይ፣ ኃይማኖትና ዘር ሳይለይ የአዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን መገልገያ ሆኖ…

ለማኅበራዊ ፍትሕ የታገለ ወይስ ሥደተኛን ያገለለ?

በሣምንቱ መጀመሪያ ሰሞን መነጋገሪያ ከነበሩ ጉዳዮች አንዱ፣ ከደቡብ አፍሪካ አንድ የማኅበረሰብ አንቂ ወጣት ኢትዮጵያ ገባ ተብሎ በባለሥልጣናት ጭምር አቀባበል ተደረገለት የመባሉ ጉዳይ ያስነሳው ውዝግብ ነው። ግለሰቡ የ37 ዓመት ወጣት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ምንም ዓይነት መንግሥታዊ ሥልጣን የሌለው መሆኑ የአቻ ላቻ…

ጉንፋን ወይስ ኮሮና?

ባለፈው ሳምንት ውስጥ ጉንፋን መሠል ሕመም ያልደረሰበት ቤተሰብ የለም ማለት እስኪቻል ድረስ ብዙዎች ታመው ታይተዋል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ በርካቶች ምን መሆኑ ባልታወቀ፣ ነገር ግን ጉንፋን ሳይሆን አይቀርም በተባለ ከባድ በሽታ ተጠቅተው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ኦሚክሮን የሚባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ እንደጉንፋን…

ኢትዮጵያ 20 ቦታ የተሸነሸነችበት ካርታ

ሠሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ብዙዎችን አነጋግሮ የነበረው፣ አዲሱ ኢትዮጵያን ለማካለል የቀረበ ኃሳብ በሚል ይፋ የተደረገ ካርታ ነበር። ብዙዎች አስተያየታቸውን በትችትም መልክ ይሁን በድጋፍ ከሰጡ በኋላ በወሰን አጣሪ ኮሚቴ የቀረበ አይደለም ተብሎ እንዲጣጣል ተደርጓል። አዲሱ የአከላለል መንገድ ተብሎ የቀረበው በአማካሪ አካላት እንጂ፣…

ዘራፊው ያለየበት ዝርፊያ

ሠሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል፣ ንብረት ተዘረፈ የሚልና ዘራፊው ማንነት ላይ ያነጣጠረ በዘመቻ መልክ የተካሔደ የቃላት ምልልስ ዋናው ነበር። ወሎ ድጋሚ ተዘረፈች ከሚሉ አንስተው፣ የደሴ ከተማ ባለሀብቶች ንብረት ተዘርፎ ተወሰደ የሚሉ ንግርቶች የብዙዎችን ትኩረት ወስደው ነበር። ከተማውን ወሮ…

ዘራፊው ሌላ ተከልካዩ ሌላ!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ጊዜ አንስቶ አንድ ጊዜ አልቻልኩም፤ አንድ ጊዜ መኪኖቼ ቀሩ እያለ ዕርዳታ መስጠቱ እንደተስተጓጎለ ሲናገር መቆየቱ ይታወሳል። የሰብዓዊ ዕርዳታዎችን ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለማድረስ የማደርገው ጥረት ተስተጓጎለ እያለ፣ የተለያየ አካላትን ተጠያቂ…

የአሜሪካ ጩኸትና ኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት

ኢትዮጵያ በገጠማት ችግር ላይ አባባሽ ኹኔታዎችን ለmፍጠር፣ መሬት ላይ ካለው በተቃራኒ ቆመው ውሸትን በማራገብ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሚፈልጉ አካላት በየአቅጣጫው ጫና በሚደረስባት በዚህ ወቀት፣ የሰሞኑ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ተግኝተው መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መመስከራቸውና ከኢትዮጵያ ጎን መሆናቸውን ማረጋጋጣቸው…

የኖቤል ሽልማቱ እንደ ማሰሪያ!

የኖቤል ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች መሰጠት ከተጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል። በእነዚህ ዓመታት በሳንይስም ሆነ በተለያዩ ዘርፎች አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች ከሚሰጠው የዕውቅና ሽልማት በላይ፣ የብዙዎችን ትኩረት የሚይዘው ለሠላም ላበረከቱት አስተዋጽኦ እየተባለ በየዓመቱ ሽልማቱ የሚሰጣቸው ግለሰቦች ናቸው። ኔልሰን ማንዴላን ለመሳሰሉ ዕውቅ ሰዎች መርጠው…

ወዳጅ ሲከዳ…!

ሰው ወዳጅና ጠላቱን የሚለየው በችግሩ ጊዜ ነው ይባላል። ምርጥ ጓደኛ ወይም ወዳጅ ችግሩን አብሮ ይጋፈጣል። ጥሩ የሚባል ዓይነት ወዳጅ ችግርን አብሮ ባይጋፈጥ እንኳ <አይዞን! ከጎንህ ነኝ፤ ከአጠገብሽ አልለይም> ይላል። እንደው ወዳጅነቱ የለብ ለብ የሆነ እንደሆነ ችግር ሲገጥም አልሰማሁም አላየሁም ብሎ…

የዐይን ያወጣው ጣልቃ ገብነት!

ሠሞኑን መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የምዕራባውያን በተለይም የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትን የተመለከተ ነው። ጣልቃ መግባት የሚለው ቃል እስኪያንስና እኛ በአገራችን ጉዳይ ጣልቃ የገባንባቸው እስኪመስላቸው ድረስ ማስፈራሪያ መሰንዘርና ማዕቀብ መጣል ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በግድቡም ሆነ በጦርነቱ ምክንያት በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ…

የ‹አጎዋ› ማስፈራሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በተደነገገበት በዚህ ሳምንት አሜሪካ ስታስፈራራ የነበረበትን የአጎዋ አባልነት እግድን ተግባራዊ ማድረጓ ለብዙዎች አስተያየት ምክንያት ሁኗል። ምርታቸውን በነጻ ያለግብር ወደ አሜሪካ እንዲያስገቡ ፈቅዳላቸው ከነበሩ የአፍሪካ አገራት ተርታ እንዳትወጡ ይህን አድርጉ እያለች፣ የዕርዳታ ድጋፍን እጅ ለመጠምዘዣ ተጠቀመችበት ሲሉ የነበሩ…

የጦር አውሮፕላኖቹ ከፍታ

ሠሞኑን መነጋገሪያ ከነበሩ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ አየር ኃይል ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ አደረግኳቸው ያላቸውን ድብደባዎች ተከትሎ የተሰነዘሩ ሐሳቦች ናቸው። አየር ኃይሉ ጀቶችንና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተጠቅሞ ለህወሓት ታጣቂ ቡድን መሠረታዊ የሆኑ የመሣሪያና ሎጀስቲክስ ማከማቻ፣ የማሰልጠኛና መሰል ካምፖችን በቦንብ ማጋየቱን…

error: Content is protected !!