መዝገብ

Category: ወፍ በረር ዜና

ልማት ባንክ ከ 900 ሚሊዮን ብር በላይ አተረፈ

ልማት ባንክ ከኪሳራ በመውጣት በ 2012 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ብቻ ከ951 ሚሊዮን ብር ማትረፉን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ። ባንኩ በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት ኪሳራ በማገገም፣ በአጠቃላይ በስድስት ወሩ ብር 951 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 483 በመቶ ሊያተርፍ…

በአማራ ክልል ከ720 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም ተያዘ

በአማራ ክልል ከ720 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም መያዙን የአማራ ክልል የእፅዋት ዘርና ሌሎች ግብርና ግብዓቶች ጥራት፣ ቁጥጥር እና ለይቶ ማቆያ አስታወቀ። የክልሉ የእፅዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ቁጥጥር እና ለይቶ ማቆያ ባለሥልጣንና የሜዳ ፕሮጀክት ትብብር፥ በአደገኛና መጤ…

በባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብቻ የተቀነባበረ አልበም ገበያ ላይ ዋለ

‹ኃይለ ጊዜ› የተሰኘ በባህላዊ ሙዚቃ መሣሪያዎች ብቻ የተቀነባበረ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 14/2012 ለገበያ ሊቀርብ ነው። በመሶብ የባህል ሙዚቃ ተጫዋቾች ቡድን የተዘጋጀው አልበሙ፣ በባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብቻ የተቀነባበረ ሲሆን 10 ሙዚቃዎችን ይዟል። ሰባት የሙዚቃ ባለሙያዎችም የተሳተፉበት ነው። ቡድኑ ከዚህ…

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫው እንዲራዘም ጠየቀ

የኢትዮጽያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫ 2012ትን በተመለከተ በሰጠዉ መግለጫ ምርጫዉ እንዲራዘም መወሰኑን አስታወቀ። ምክር ቤቱ “ከምርጫ የአገር ህልዉና ይቅደም” በሚል ርዕስ አርብ የካቲት 13/2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባደረጉት ዉይይት ምርጫዉ መራዘም አለበት ሲሉ በአብላጫ ድምፅ…

ድንበር ላይ የሚደረጉ ተደጋጋሚ ፍተሻዎችን የሚያስቀር አሰራር ሊተገበር ነው

በኢትዮጵያና በሌሎች የጎረቤት አገራት ድንበር ላይ የሚደረገዉ ፍተሻ ተገልጋዮችን የሚያጉላላ እና ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ የፍተሸ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የጉምሩክ ኮሚሽን እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገራት በአንድ የሚያልቅ የፍተሻ አገልግሎት ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፣…

ጎንጂ ቆለላ ቆሬ አዲስ ዓለም የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ሊጀመር ነው

የጎንጂ ቆለላ አዲስ ዓለም መንገድ በአስፓልት ደረጃ ለማስገንባት ከተቋራጮች ጋር ውል መፈፀሙን የፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ። ይህ መንገድ ጠቅላላ 10 ነጥብ 74 ኪሎ ሜትር ርዝመት ኖሮት በአስፋልት ደረጃ የሚገነባ ሲሆን፣ በገጠር በአማካይ 10 ሜትር ስፋት ሲኖረው በከተማው 21 ነጥብ 5…

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀው አዋጅ ፀደቀ

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ23 ተቃውሞና በኹለት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት እንደተከራከረ የተገለፀ ሲሆን፣ በ23 ተቃውሞና በኹለት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁን ከፓርላማ የተገኘ…

በጥር ወር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል

የአስራ አምስት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ንብረት የሆኑ 30 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የመንግሥት ንብረት፣ ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ። ለሽያጭ ከቀረቡት 30 ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የ10 ፌዴራል ተቋማት የሆኑ 21 ተሸከርካሪዎች፣ ከመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረቡባቸው 13 ተጫራቾች…

በጥር ወር 150 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተይዟል

የጉምሩክ ኮሚሽን በጥር ወር ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃ እና ሕገ ወጥ ገንዘብ መያዙን አሰታወቀ። ይህም ከገቢ 121 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ከወጪ ደግሞ 31 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 152 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል። በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ…

ከሕግ ውጪ ሲያስተምሩ የተገኙ ስድስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘጉ

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በ25 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ጉብኝት የእውቅና ፍቃድ ሳያገኙ እና ከተፈቀደላቸው የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብለው ሲያስተምሩ የተገኙ ስድስት የግል ከፍተኛ ተቋማት መዘጋታቸውን አስታወቀ፡፡ ከተዘጉት ተቋማት መካከል ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ካምፓስ፣ ኢትዮ ስማርት…

የፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ እንዲሻሻል ሊደረግ ነው

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግሥት ድጎማ በማድረግ ከውጪ እያስገባ ለኅብረተሰቡ ሲያሰራጭ የነበረው ፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ መሻሻሉን አስታወቀ። ፓልም የምግብ ዘይት መንግሥት የዋጋ፣ የአቅርቦት እና የስርጭት ቁጥጥር እያደረገባቸው ከሚገኙ መሠረታዊ ሸቀጦች መካከል ተጠቃሽ ነው። ሆኖም ዘይቱ በውስጡ ካለው የስብ…

ፍርድ ቤቶች ትርጉም ለሚፈልጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች አገልገሎት እየሰጡ አይደለም ተባለ

በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ተገልጋዮች በሚግባቡበት ቋንቋ ተርጉመው እያቀረቡ አለመሆኑ ተገለፀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትኅ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሦስቱ ፍርድ ቤቶች ላይ ባደረገው የመስክ ምልከታ፣ በየጊዜው ከኅብረተሰቡ የሚመጡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ፍርድ ቤቶች ጥረት እያደረጉ…

በአማራ ክልል 200 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

አማራ ክልል በ421 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 200 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ከ2010 ጀምሮ ከተያዙ 118 ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል 89ኙ እስከ ቀጣዩ መጋቢት 30 2012 ድረስ ይጠናቀቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል። በዚህ ዓመትም 200…

የበረሃ አንበጣን ለመከላከል 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊደረግ ነው

በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ኹለት ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች አንድ ሚሊዮን 300 ሺሕ ዶላር ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ። የገንዘብ ድጋፉንም ለማድረግ የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት /FAO/ እና ከአሜሪካ ዓለም ዐቀፍ የልማት ኤጀንሲ /USAID/ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ቃል…

ኮካ ኮላ አዲስ ከአልኮል ነጻ መጠጥ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ ሽቴፕስ (Schweppes Novida Pineapple) የተሰኘ ከአልኮል ነጻ መጠጥ ለኢትዮጵያ ገበያ ሊያቀርብ ነው። መጠጡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለ ሲሆን፣ በአናናስ ጣዕም የቀረበ ከአልኮል ነጻ ማልት ነው። ምርቱ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መምጣቱ የአልኮል ተጠቃሚ ላልሆኑ ደንበኞች የተሻለ…

ለሴፍቲ ኔት ፕሮግራም 75 ሺሕ ቶን ስንዴ ሊገዛ ነው

በግብርና ሚኒስቴር ስር ለሚከናወነው ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 75 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዢ ለማከናወን ‹ፕሮሚሲንግ› ከተሰኘ ድርጅት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ። ግዢው የዓለም ባንክ ለግብርና ሚኒስቴር የሴፍትኔት ፕሮግራም ባደረገው 24 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ…

ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች በማቆያ ክፍል እንዲቆዩ ሊደረግ ነው

ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን በመለየት በማቆያ ክፍል እንዲቆዩ ለማድርግ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ። የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ማእከልም በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተቋቁሟል። በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ከሌላው መንገደኛ ጋር ሳይቀላቀሉ የሙቀት ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ከቻይና…

የገናሌ ዳዋ ግድብ ኃይል ማመንጨት ሊጀምር ነው

የገናሌ ዳዋ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግድብ ጥር 26/2012 ኃይል የማምረት ሥራውን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። ግድቡ 2 ነጥብ 57 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ነው። የፕሮጀክቱን የሲቪል እና የኤሌክትሮ…

ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ የ14 ሚሊዮን ዶላር ማስፋፊያ አደረገ

ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ በሚገኘው ፋብሪካው ላይ የ 14 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የማስፋፊያ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ። ማስፋፊያዉ ፋብሪካው በሰዓት 32 ሺሕ የማልታ ጊነስ መጠጦችን እንዲያመርት የሚያስችል እንደሆነ ፋብሪካው አስታውቋል። በሌላ በኩል የዲያጆ ኩባንያ አካል የሆነው ሜታ…

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ካሳ ያልተከፈለበት መሬት ለግጭት ምክኒያት እንደሆነ ገለፀ

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 250 ሄክታር መሬት በመኖሩ የተቋሙን ወሰን ማስከበር አለመቻሉን እና ይህም ለሰላማዊ የትምህርት ሂደት እንቅፋት እየሆነ መምጣቱን አስታወቀ። መሬቱም ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት 1999 ጀምሮ የተጓተተና ካሳ ያልተከፈለበት 250 ሄክታር መሬት በመኖሩ ወሰኑን ማስከበር አለመቻሉንና ይህም ለሰላማዊ መማር ማስተማር ስራው እንደ…

የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ መከላከል ተጀመረ

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወደ ሀገር እንዳይገባ ለመከላከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መገባቱን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21/2012 ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ክልል የተከሰተ መሆኑን አሳወቋል። በቫይረሱም የ17 ሰዎች ሕይወታቸው…

ያገለገሉ ንብረቶችን በማስወገድ ከ32 ሚሊዮን ብር ተገኘ

የመንግሥት ንብረት ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት በስድትስት ወራት ውስጥ ያለገሉ ንብረቶች በማስወገድ ከ32 ሚሊዮን 699 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ለአዲሰ ማለዳ አስታውቋል፡፡ ከተወገዱት ንብረቶች መካከልም ከሃያ መሥሪያ ቤቶች 65 ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ28 ሚለየን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ የ6 መሥሪያ ቤቶችን…

የወመዘክር አዳራሽ ከኹለት ሳምንት በኋላ ተጠናቆ ለአገልገሎት ክፍት ይሆናል

በ1.3 ሚሊዎን ብር በእድሳት ላይ የቆየዉ ወመዘክር አደራሽ ከሁለት ሰምንት ብኋላ ተጠናቆ ለአገልገሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለፀ። የእድሳት ስራው ከአሜሪካን ኤምባሲ በተገኘ 1ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በነሀሴ ወር ተጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር እንደመሚጠናቀቅ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም በአጋጠሙ የዲዛይን ችግሮች ስራው…

ታፍ ኦይል የአዉሮፕላን ነደጅ ማከማቻ ሊያስመርቅ ነው

ታፍ ኦይል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጽያ አየር መንገድ ግቢ ውስጥ ያስገነባውን የአዉሮፕላን ነደጅ ማከማቻ በቀጣይ ማክሰኞ ጥር 19/ 2012 ሊስመርቅ ነዉ፡፡ ታፍ ኦይል ኢትዮጽያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሆነ እና ትልቅ የአዉሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ከነሙሉ አገልግሎቱ…

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ስድስት አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ በስድስት ወራት ውስጥ 22 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ተቋሙ የእቅዱን 104 በመቶ ያሳካ ሲሆን፣ ገቢው ከባለፈው በጀት ዓመት…

ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት ሊያከብሩ ነው

ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ጥር 8 ቀን 2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። አገራቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በሚያከብሩበት ጊዜ የ50 ዓመት…

ገቢዎች ሚኒስቴር በታኅሳስ ወር 18.1 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በታኅሳስ ወር ከ18.1 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ። በታኅሳስ ወር መሥሪያ ቤቱ 18 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል። በተመሳሳይ ወርም ከአገር ዉስጥ ገቢ 8.59 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ከቀረጥና ታክስ 9.5 ቢሊዮን…

በዘንድሮው ጉዞ አድዋ 60 ተጓዦች ይሳተፋሉ ተባለ

የአድዋን ድል ለመዘከር የሚከናወነው ጉዞ አድዋ ሰባተኛ ዙር ተጓዦች ጥር 9/2012 ከአዲስ አበበ በመነሳት 1 ሺሕ 10 ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው ለማቆራረጥ መዘጋጀታቸው ተገለፀ። ለሰባተኛ ጊዜ በሚደረገው ጉዞ አድዋ፣ ከአዲስ አባባ ተነስቶ እስከ አድዋ ድረስ 1 ሺሕ 10 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን…

በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በታሰሩ አመራሮች በጌታቸዉ ወድሻ (ዶ/ር) እና በጌታሁን መርጋ ላይ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ተገለፀ። አመራሮቹን ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑንና የቤንሻንጉል ክልል ምክር ቤት የፋይናንስና ገንዘብ ቋሚ…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢን ለማሳደግ የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢን ለማሳደግና ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የማማከር ሥራ ለማከናወን ኤ ኤፍ ሜርካዶስ እና ኤ ኤፍ ኮንሰልት (AF-Mercados and AF Counsult) ከተሰኙ የስፔን ኩባንያዎች ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የ68 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ የተካሄደው ከገቢ ማሳደግና…

This site is protected by wp-copyrightpro.com