መዝገብ

Category: ትንታኔ

ምርጫና ኢትዮጵያ ከመዛግብት ዓለም

ኢትዮጵያ በነበራት አቅም ኃያል፣ በሥልጣኔ ደግሞ ገናና የነበረችበት ዘመን በየታሪክ መዛግብቱ ሰፍሮ ይነበባል። በሥልጣኔ የዓለም አገራትን የቀደመችበት፣ እንዲሁም በቀሪው ዓለም የመጣውን ሥልጣኔ በፍጥነትና በራሷ መንገድ ተቀብላ ያስተናገደችበት ጊዜም ጥቂት እንዳይደለ የሚመሰክሩ ብዙ እውነቶች አሉ። ሉላዊነትን ተከትሎ የመጣው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሰምሮ…

የዐሥር ዓመታት የትንቅንቅ ጉዞ

ዐስር ዓመታትን የኋሊት ተጉዘን መጋቢት 3/2003 ላይ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አዝማችነት ነበር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ በተባለ ስፍራ ላይ ዕውን የመደረጉ ዜና በዓለም ላይ የናኘው። ‹‹አባይ ማደሪያ የለው፤ ግንድ ይዞ ይዞራል›› መተረቻው፣ ‹‹የዓባይን…

ከመጋቢት እስከ መጋቢት

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ታሕሳስ 2012 መጨረሻ ጀምሮ ቫየረሱ ከየት መጣ? ገዳይነቱስ ምን ያህል ነዉ? በግዑዝ ነገሮች ላይስ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ክትባቱስ መቼ ያጀመር ይሆን? ምን ያክል ገዳይ ነው? መቼ መፍትሄ ይገኝለታል? የሚሉትና ሌሎቸ አነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለወራት በብዙዎች ዘንድ…

ምርጫ 2013 – ሴቶች የት አሉ?

በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች ተሳትፎ ዙሪያ ውይይት ከተነሳ፣ ‹የሴቶች የመሪነት ተሳትፎ ወርቃማ ዘመን› ተብሎ የተቀመጠ የሚመስልና የሚነሳ ኹነት አለ። ይህም ወደኋላ መቶ ዓመታትን ተጉዞ እቴጌ ጣይቱ እና ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱን የሚያወሳ ነው። ያንን ወቅትና በጊዜው በነበረው የፖለቲካ አሠራር ውስጥ የነበሩ ሴቶች…

የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማነቆዎች

ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌደራል እና ለክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች እንዲሁም ለአዲስ አበባ እና ለድሬዳዋ መስተዳድር ምክር ቤቶች ግንቦት 28 እና ሰኔ 05 2013 እንደሚያደርግ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥርዓተ-ፆታ አካታችነትን በተመለከተ…

አሁንም የኮቪድ 19 ጉዳይ ቀልድ አይደለም

ቦታው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። ለቀሪው ቤተሰብ ስንል በትክክል ሰፈር እና መንደሩን ከመግለጽ ተቆጥበናል ምክንያቱ ደግሞ ይዘን የቀረብነው ታሪክ በእጅጉ የሚያሳዝን እና የኮቪድ 19 አስከፊውን ገጽታ የሩቅ አገር ታሪክ አለመሆኑን የሚያስጨብጥ ስለሚሆን በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ አይተነው የምናልፈው ሳይን ጉያችን ውስጥ…

የትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈት

የትምህርቱ ዘርፍ የተማረ ትውልድን በማፍራትና በተለያዩ ዘርፎች ችግር ፈቺ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ያለው ሚና ቀላል የሚባል እንዳለሆነ መናገር ይቻለል። ከዚህ በተጨማሪም የተማሪዎች እንቀስቃሴ በራሱ አንዱ የአዲስ አበባ ድምቀት መሆኑን ለወትሮው ጭርታና ዝምታ የሚታይባቸው አካባቢዎች ዛሬ ላይ ምስክር ናቸው ማለት ይቻላል።…

ኮቪድ 19 እና ‹መልካም› አጋጣሚው – በጤና አገልግሎት

የ53 ዓመቷ ዝናሽ አየለ ከሳምንቱ አራቱን ወይም አምስቱን ቀናት ሆስፒታል ማሳለፍ ግድ ካላቸው ጥቂት ዓመታት አልፈዋል። እንደ ባለሥራ ማልዶ ሆስፒታል መሄድና መመለሱን ሰለቸኝ ብለው አያውቁም። ኮቪድ 19 ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከመሰማቱ ኹለት ሳምንት ቀደም ብሎ ያደረጉት የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምናም፣…

ኮቪድ 19 እና የአዕምሮ ጤና ጉዳይ ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ››

በኤርሚያስ ሙሉጌታ ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በ50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ  በሰባት ሐይቆቿ ታጅባ በምትገኘው ሞቃታማዋ የቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ነው። የባለ ታሪካችን የመኖሪያ አድራሻን እና ትክክለኛ ስም ከመጠቀም በመቆጠብ አዲስ ማለዳ ከስፍራው በመገኘት የሰበሰበችውን እና ታዘበችውን ግን እንደሚከተለው ለማድረስ ሞከራለች።…

ትግራይን መልሶ የማቋቋም ቀጣይ ሥራ

በሕወሓት የቀድሞ አመራር ሥር አባል የነበሩት እና ከአገራዊው ለውጥ በኋላ ወደ አገር ተመልሰው የትግራይ ትብብር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴት)ን አቋቁመው በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲ እየመሩ ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ አረጋዊ በርሄ(ዶ/ር) ሕወሓት ሲመሰረት ለመልካም አላማ ነበር ይላሉ። በዚህ ሂደት ግን ሥልጣን መንበሩን…

አገረ ሰላም የት ነው?

አንድ ወር ሊሞላው በቀናቶች ልዩነት የተጠናቀቀው እና በፌደራል መንግሥት በኩል የተካሔደው የሕግን የማስከበር እንቅስቃሴ በርካታ አዳዲስ ጉዳዮችን ሲያሰማን እና ሲያሳየን ሰነባብቷል። ከተፈጠረው የሰሚን ጆሮ ጭው ከሚያደርገው በሰሜን ዕዝ ላይ ከተሰነዘረው ጥቃት እስከ ማይካድራ ብሔር ተኮር ጭፍጨፋ ድረስ ምን አይነት ጉድ…

ያልተፈታው የትራንስፖርት ችግር

ጉዳዩ መነገር የጀመረው ዛሬ አይደለም ፤በተለያየ ዓመት እና ዕለት በጣም በተደጋጋሚ ሲወራበት የምንሰማውም ነው- የትራንስፖርት ችግር ። አዲስ ማለዳም በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግራለች። ካነጋገረቻቸው መካከል አዲስ ዓለም ስንታየሁ ትገኝበታለች። አዲስ ዓለም በአዲስ አበባ ከተማ ተወልዳ ማደጓን በመግለጽ ከትራንስፖርት ችግር…

የግጭቶች በአድሎአዊ ዘጋቢዎች

መረጃን ያለ ገደብ ከግለሰብ እስከ ማኅበረሰብ ያለ ቦታ ገደብ ለማድረስ የመገናኛ ብዙሃን ፋይዳ ከፍተኛ ነው። የሰው ልጆች ስለሚኖሩበት ማኅበረሰብም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለሚከሰቱ ሁነቶች ለማወቅ ካለው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ አይን እና ጆሮውን ጣል የሚያደርግበት የመረጃ ምንጭ ይሻል። ለዚህም ይመስላል…

የሰንደቅ ዓላማ ክብር እና የአገር ፍቅር

«በባንዲራ!! በባንዲራ!! በባንዲራችን!! በሕግ ቁም ብዬሃለሁ!!» ትለዋለች፤ እየተከተለች አዲስ አበባ ውስጥ፣ ወደ ቀጨኔ መድኃኔዓለም በሚወስደው መንገድ፣ ድልድዩ አጠገብ፣ ከአባ ሀብቴ ቤት አጠገብ ነው ሴትየዋ ጠላ ሻጭ ናት ሰውዬው እግረ መንገዱን ሲያልፍ ጠላ ሊጠጣ ይገባና ሳይከፍል ይወጣል እሷ እንዳለችው ኹለት «ምኒልክ»…

ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ መበራከት

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ቁጥራቸው የበዛ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ሲያዙ እና አዘዋዋሪዎችም በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ ለመጣው ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ደግሞ የሕግ አካላት ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን ቁጥጥር ሲያደርጉ ይስተዋላሉ። ይህ ጉዳይ ደግሞ በተለይም…

የመምህራን ተጽእኖ በግል ትምህርት ቤቶች

የኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች በትምህርቱ መስክ በሰፊው ተሰማርተው ይገኛሉ።እነዚህ ትምህርት ቤቶች ጥንትም የነበሩና ደርግ ወርሷቸው እንደነበር ከደርግ ውድቀት በኋላ 1983 አመት እንደአዲስ እንዳንሰራሩ ይነገራል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሲመሰረቱ መንግሥትን ከማገዝ አንፃር ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወቱ ታስቦ እንደነበር በተባለውም…

ቀለም የቆጠሩ ሥራ አጦች

ፉአድ ሚፍታ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል አካባቢ እርሱን ጨምሮ ከአምስት የቤተሰብ አባላቱ ጋር የሚኖር ዕድሜው በሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ወጣት ነው።ከዛሬ ኹለት ዓመት በፊት ከአድማስ የኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ሲመረቅ እርሱም ሆነ ጓደኞቹ በተለይም ቤተሰቦቹ የነበራቸው ደስታ ወደር የነበረው አልነበረም። የእርሱ ደስታ በተማረበት…

የላዳ ታክሲዎች እጣ ፋንታ

ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ነው የስድስት ልጆችም አባትም ናቸው ካሳሁን ማንደፍሮ፤ የሚተዳደሩት በታክሲ ሥራ ነው ። የላዳ ታክሲ ማለታችን ነው። አዲስ ማለዳም ካሳሁንን ሥራ እና ሕይወት እንዴት ነው? ብላ የጥያቄዎቿን መጀመሪያ አደረገች። ካሳሁን ማደፍሮም በቁጭት እና በምሬት ‹‹ሥራው በጣም ተበላሽቷል…

እምቦጭን በአንድ ወር ዘመቻ

የእምቦጭ አረም የጣና ሐይቅ ላይ መታየት ከጀመረበት 2004 ጀምሮ እምቦጭን ለማጥፋት የተደረጉ በርካታ እንቅስቃሴዎችእንደነበሩ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ውጤታማነታቸው እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ሐይቁን ግን በጥቂቱም ቢሆን በነብስ እንዲቆይ ያደረገው ነበር። ይህን መጤ አረም ግን ከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ ለአንድ…

የበረሃ አንበጣ አስከፊ ጉዳት ከአርሶ አደር ማሳ

ተሾመ ላቀው ወጣት አርሶ አደር እና የሦስት ልጆት አባት ነው። ተሾመ ኗሪነቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብ ውሃ ቀበሌ ነው። አዲስ ማለዳ በአማራ ክለል በተወሰኑ ወረዳዎች ተከስቶ የአርሶ አደሩን ሰብል በከፍተኛ ሁኔታ አያወደመ የሚገኘውን የበረሃ አንበጣ…

የምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት አሃዞች ሲፈተሹ

እንግዲህ የ2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባ በሳምንቱ መጀመሪያ ተካሂዷል።ስድስተኛ የሆነ የፓርላማ ዓመት ስብሰባ ሲካሄድ ያሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ማለትም በዘመነ ኢሃዴግ ከዛም ብልፅግና ሀገሪቱ መተዳደር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ።ከመደበኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ…

መንግሥት በአምበጣ መከላከል ላይ ምን ድረስ ሄዷል?

መንግስት ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እያሳየ ያለበት ሁኔታ መሻሻል ቢኖረው በየዘርፉ ትክክክለኛውን አቅጣጫ ማስቀመጥ መለመድ አለበት በማለት መንግስት ተዘናግቷል የሚሉት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መስከረም አበራ ናቸው ፡፡አሁን ላይ እንደዚህ ከመራገቡ በፊት በአንበጣ ዙርያ ተደጋጋሚ ጥቄዎች እና ቅሬታዎች ጥቆማዎች ሲነሱ መንግስት…

የኮቪድ-19 መከላከያ መመሪያ ሲፈተሸ

ዓለም የተፈተነችበት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ከግስጋሴያቸው የገታ ብርቱ ቀበኛ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ግንኙነቶች እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብሮችን በእጅጉ ገድቦ ቁጥጥር ስር ያዋለ ውረርሽኝ ነው። በአገረ ቻይና ውሃን ግዛት በወርሃ ታህሳስ 2012 መከሰቱ በግልጽ ለዓለም ህዝብ ይፋ ሆነ። ባልተገመተ እና ከአውሎ ንፋስ…

በመረጃ የመጥለቅለቅ አደጋን በኃላፊነትና በተዓማኒነት መጋፈጥ

ከመንግሥትና ከሕዝብ መካከል ሆኖ እንደ ዐይን ደግሞም እንደ ጆሮ የሚያገለግለው የብዙኀን መገናኛ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ተገኝቷል። እንደውም የሚፈተንበት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱ ደግሞ ሁሉም ያሻውን በአጭር ፍጥነት ለብዙዎች ማድረስ የሚችልበት አውድ በተፈጠረበት ዘመን፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር…

90 ዓመታት የአልበገር ባይነት ጉዞ

አገር በዜጎች ይገነባል። ዜጎቿ በየትኛውም አስተሳሰብ ደረጃ እና ንቃተ ሕሊና ቢሆኑ ለአገር ግንባታ እና ለአገር ማቆም ሁሉም እኩል ባለቤትነት እና ደርሻ ይኖራቸዋል። በዜጎች መፈቃቀድ እና መደጋገፍ ላቅ ሲልም መወቃቀስ አገር ከዘመመችበት ትቃናለች፤ ከወደቀችበት ትነሳለች፤ በከፍታም ላይ ከሆነች ከፍ ብላ ልዕልናዋን…

 የዋስትና መብት መነፈግ በህግ ባለሙያዎች እይታ

የሰሞነኛው የአገራችን የፍርድ ቤት ውሎን በተመለከተ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው እንግዳ መሳይ ክስተቶች መካከል ዳኞች ግራ ቀኙን ተመልክተው  ተከሳሽ ተጠርጥሮ የተያዘበትን ጉዳይ ካመዛዘኑ ፍርድ ቤት የሚሰጧቸው የዋስትና መብቶች ተፈፃሚነት በፖሊስ መደነቃቀፉ ነው፡፡ ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን የዋስትና መብት ተጠቅመው የተጠየቁትን የዋስትና ማስያዣ…

የጎርፍ መጥለቅለቅና የተጎጅዎች ድጋፍ እጥረት

በኢትዮጵያ በዘንድሮው ክረምት ዝናብ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመጣሉ በተለይም በአፋር፣ በጋንቤላ እንዲሁም በአማራ ክልል በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በርካታ የግብርና ስብል ልማቶች ወድመዋል። ጎርፍ መጥለቅለቅ ባጋጠመባቸው አንዳንድ ቦታዎች እስካሁን ድረስ መሰረታዊ አስቸኳይ እርዳታ እየተደረገ አለመሆኑን ተጎጅዎችና ተፈናቃዮች…

የዲዛይን ችግር የሚያንገላታው የአማራ ብልፅግና ፓርቲ

ብልጽግና ፓርቲ ኢሕአዴግን መተካቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደተሻለ መስመር ይወስዳል የሚል ተስፋ ሰጥቶ እንደነበር በማውሳት የሚጀምሩት መስከረም አበራ፤ የቀደሙ ፓርቲዎች ሥማቸውን ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንደሚቀየሩ ይጠበቅ ነበር ብለዋል። በአንጻሩ ይልቁንም የቀድሞው ብአዴን አሁን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቀውንም ሆነ ቃል የገባውን ለውጥ…

የፈረቃ ትምህርት እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች

በአገራችን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ጉዳይ በሚመለከት መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከማወጅ ጀምሮ ረጅም መንገዶችን ተጉዟል። ይህ የሆነበትም ምክንያት የአኗኗራችን ዘዬ እና የበሽታው ፀባይ በእጅጉ የማይጣጣም በመሆኑ ከፍተኛ ዕልቂት በአደጉት አገራት ላይ እንዳደረሰው እኛም ጋር እንዳያደርስ ለማድረግ በመታሰቡ እና ከአደጉት…

የዐቢይ መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Abiynomics) “ስኬቶች”

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ዓለም የተለያዩ ችግሮችን በስፋት አስተናዳለች። የምጣኔ ሀብት ጉዳይም በዚህ የፈተና ወጀብ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ በዚህም ካደጉ አገራት ይልቁ ጫናው በደሃና አዳጊ አገራት ላይ ሊበረታ እንደሚችል ገና በማለዳው ነበር ሲተነበይ የነበረው። ሽመልስ አረአያ (ዶ/ር) ይህን የኢትዮጵያን…

This site is protected by wp-copyrightpro.com